2015-12-28 16:03:00

የክርስቲያኖች ሰማዕትነት


እ.ኤ.አ. በዚህ ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀረው 2015 ዓ.ም. ስፍር ቁጥር የሌላቸው ማኅበረ ክርስቲያን ለስደት መዳረጋቸውና የሚደርስባቸው ግፍና በደልም እጅግ የሚዘገንን ሆኖ እያለ መረሳታቸውና ብዙ የማይነገርላቸው እንደሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ትዊተር በተሰየመው ማኅበራው ግኑኝነት ድረ ገጽ ዘንድ ባለው አድራሻቸው አማካኝነት በአፍሪቃ በመካከለኛው ምስራቅና በተለያዩ  የዓለማችን ክልል በማኅበረ ክርስቲያን ላይ የሚጣለው አደጋ፣ የሚፈጸመው አድልዎና ቅትለት ዙሪይ መልእክት በማስተላለፍ በአሁኑ ወቅት በክርስቲያኖች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃትና የሚፈጸመው በደል አድልዎ ከሚነገረውና ከሚታሰበው በላይ መሆኑ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰየመው ዓለም አቀፍ የግብረ ሰናይ ማኅበር በኢጣሊያ ለሚገኘው ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ማርታ ፐትሮሲሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው በደልና ግፍ ማኅበረ ክርስቲያን የሚያጋጥመው አድልዎና ስደት ከዓመት ወደ ዓመት እጅግ ከፍ እያለ ቢሆንም ቅሉ የሚያጋጥማቸው ችግር መፍትሔ ከማፈላለግ ይልቅ ጸረ ክርስቲያኑ ተግባር ልሙድና ቅቡል እየሆነ በመምጣቱ ምክንያት እየተረሱ ናቸው ብለዋል።

ቦኮ ሃራም ሲል ገዛ እራሱን የሰየመው እስላማዊ የሽበራው ኃይል ወደ የናይጀሪያ ጎረቤት አገሮች እየተስፋፋ ያለው በናይጀሪያ ለብዙ ክርስቲያኖች እልቂትና ስደት ምክንያት መሆኑ ገልጠው፣ እስላማዊው አገር በማለት ገዛ እራሱ የሰየመው በሶሪያ በኢራቅ በሊቢያና በጠቅላላ በመካከለኛው ምስራቅ ጸረ ክርስቲያናዊ እንቅስቃሴ እያረማመደ ያለው እስላማዊው አክራሪው ኃይል በአለፖ አቢያት ክርስቲያንን በማውደም በክልል የነበረው 150 ሺሕ የክርስቲያን ብዛት ወደ 50 ሺሕ እንዲጎድል ማድረጉና ሁኔታው በእንዲህ ከቀጠለም በመካከለኛው ምስራቅ የማኅበረ ኅልውና አስጊ እንደሚሆን ነው፣ በእስያ በፓኪስታን በኢንዶነዢያ ያለው የማኅበረ ክርስቲያን ሁኔታ አስጊ በመሆኑም፣ በገዛ አገር ክርስቲያን ሆኖ ክርስትናን በነጻነት መኖር አስጊ እየሆነ መጥተዋል ብለዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ የማኅበረ ክርስቲያን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው፣ ማኅበረ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ ይኖርባቸው በነበሩት አገሮችና እንዳውም ሌላ ሃይማኖት ከመስፋፋቱ በፊት የክርስቲያን አገር ተብለው ይታወቁ በነበሩት እንደ ኢራቅ በመሳሰሉት አገሮች የክርስቲያን ኅልውና ላደጋ ተጋልጦና እነዚያ አገሮች አለ አንድ ክርስቲያን ለመቅረት አደጋ ተጋልጠዋል። የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸንን ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ ባስቸኳይ ካልተጋ ብዙ አገሮች አለ ማኅበረ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን አለ ንኡሳን የኅብረተሰብ አባላት ጭምር እንደሚቀሩ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.