2015-12-28 16:09:00

51ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. 51ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ አስተጋጅ የፊሊፒንስ ከተማ ሰቡ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኾሰ ፓልማ ቅድመ ዝግጅቱ በማመልከትና የ51ኛው ቁዱስ ቁርባን ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ክንዋኔ ምን እንደሚመስል ሮማ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ከጥር 25 ቀን እስከ ጥር 31 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚካሄድ መሆኑ አስታውሰው፣ 10 ሺሕ ተጋባእያን ከ 71 አገሮች የተወጣጡ 8,500 ልኡካን መመዝገባቸው ገልጠው፦

የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው (ቈላሲስ, 1,27)

እ.ኤ.አ. 1937 ዓ.ም. በማኒላ ከተማ 33ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 11ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ዘመን መካሄዱ ብፁዕነታቸ በማስታወስ ይኽ እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. በሰቡ ከተማ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በፊሊፒንስ ሲካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ገልጠው፣ የ2016 ዓ.ም. ጉባኤ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ያለው የሕይወትና የታሪክ ፍጻሜ ትርጉም የሚያብራራ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በምህረት ዓመት መንፈስ

የ2016 ዓ.ም. የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ከተገባው የምህረት ዓመት ጋር የተጣመረ በመሆኑ ለሁሉም ካቶሊክ ምእመናንና ኣቢያተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነትና ገዳማውያን የጥልቅ ኅዳሴ ምንጭ እንደሚሆን ብፁዕ አቡነ ፓልማ ገልጠው፣ ኅዳሴው በተስፋ ላይ ያነጣጠረ ከመሆኑም ባሻገር ተስፋና ምህረት ማእከል ያደረገ እንደሚሆን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ታግለም ባስደመጡት ንግግር እንዳሰመሩበት የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አያይዞ በአሁኑ ወቅት ዓለማችን ሰብአዊነት እጅግ የተጠማ ነው፣ ይኽ ደግሞ የፍቅርና የምህረት ጸጋ የሚመለከት ሁነት ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ቦ ልዩ የቅዱስ አባታችን ልኡክ

በዚህ በሰቡ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወክለው ንግግር በማስደመጥ ጉባኤውን የሚያስጀምሩ በቢርማንያ የያንጎን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማኡንግ ቦ ሲሆኑ፣ የኒው ዮርክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቲሞትይ ዶላን የሎስ አንጀሎስ ረዳት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሮበርት ባሮን የናይጀሪያው ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆን ኣናየካን የቦምባይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦስዋልዶ ጋርሲያስ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።       
All the contents on this site are copyrighted ©.