2015-12-28 16:00:00

የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በላቲን ሥርዓት የቅዱስ እስቲፋኖስ ሰማዕት ዓመታዊ በዓል ምክንያታ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ከሚገኘወ ከሐዋርያዊ መስኰት ሆነው በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ የዕለቱ ምንባብ ዙሪያ በሰጡት አስተምህሮ፦ በምህረት የክፋት መንፈስን እናሸንፋለን፣ ጥላቻን ወደ ፍቅር በመለወጥ የምንኖርበት ዓለም እናነጻለን፣ ቂም ይዞ መኖር እንዴት ያስፈራል፣ ይቅርታ መስጠት፣ ይቅር ማለት ሰው ወደ እግዚአብሔር ቅርብ ያደርጋል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ምህረትና ይቅር ማለት ይፈውሳል፣ ልብን ዳግም ኅያው ያደርጋል፣ ይኸንን ሰው ወደ እግዚአብሕር ቅርብ የሚያደርግ ይቅር ማለትንና ይቅርታን የመስጠት ተግባር ለመኖር የሚደግፍ ሁነት አለን፣ ከእግዚአብሔር ምህረት ነው የተወለድነው፣ በእያንዳንዷ ቀንና ሰዓት ይቅር ስንባባል ልባችን ዳግም ይወለዳል፣ ዳግም ኅያው ይሆናል። በእምነት ወደ ፊት ለማለትና ለማደግ ከፈለግን በቅድሚያ የእግዚአብሔር ምሕረት መቀበል፣ ሊምረን ዝግጁ ከሆነው አብ ጋር መገናኘት፣  እርሱ ዘውትር እኛን ለመማርና ይቅር ለማለት ዝግጁ ነው፣ የእርሱን መለኰታዊ ምህረት ከመለመን አንቦዝን፣ እርሱ በመማራችን ልባችንን ይፈውሳል፣ ፍቅርን እንድንኖር ያደርገናል፣ ስንማር ብቻ ነው መማርን የምናውቀውና የምንችለው እንዳሉ ሎሞናኮ ገለጡ።

ምህረት ከጸሎት ይወለዳል

ይቅር ማለትና መማር ሁሌ ከባድና አስቸጋሪ ነው፣ ታዲይ እንዴት ኢየሱስን ለመሰል እንችላለን? ዕለት በዕለት ትልቅም ይሁን ትንሽ ለሚፈጸምብን በደልና ግፍ ይቅር ለማለት ከምንና ከየት እንጀምራለን? የሚጀመረው ከልብና በልብ ነው። ተግዳሮትን ሁሉ በጸሎት በመግጠም በመጸለይ የበደለንን ለጌታ ምህረት እናወክፋለን፣ ጌታ ሆይ ስለ እርሱ ወይንም ስለ እርሷ ምህረትን እለምንሃለሁ። ይኽ ውስጣዊ ትግል ውስጥነታችንን ከክፋት ያነጻል፣ ጸሎትና ፍቅር እንደ የሰንሰለት ቀለበት እየተያያዘ ለሚሄደው ቂም ይዞ ከመኖር ነጻ ያወጣናል።

እውነተኛው የኢየሱስ ምስክር እንደ ኢየሱስ ይጸልያል ያፈቅራል ገዛ እራሱን ይሰጣል ይምራል

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ እያለ ይምራል፣ ሰማዕት እስቲፋኖስም ኢየሱስን በመምሰል ይኖራል፣ እስቲፋኖስ አባት ይሆ ይቅር በላቸው ብሎ ከጸለየላቸው ከወጋሪዎቹ ውስጥ አንዱ ሳውል የሚባል ሰውም ነበር፣ ሳውል የቤተ ክርስቲያን አሳዳጅ፣ ጥቂት ቆየት ብሎ ጳውሎስ የሆነው፣ በጌታ ጸጋ የአሕዛብ ሐዋርያዊ ለመሆን የበቃው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ጸጋና ከእስቲፋኖስ ጸሎት ወደ እግዚአብሔርና በእግዚአብሔር የተወለደ ሆነ። ይቅርታን ከመስጠትና ከሰማዕትነት የተወልደ። እውነተኛው የኢየሱስ ምስክር ይጸልያል ያፈቅራል ገዛ እራሱን አሳልፎ ይሰጣል ከሁሉም በላይ ደግሞ ይቅር ይላል፣ ምክንያቱ ምህረትና ይቅር ማለት ገዛ እራሱ አሳልፎ የመስጠት ተግባር የላቀ የኢየሱስ ተከታይ መሆን ይመሰክራል እንዳሉ ሎሞናኮ አስታወቁ።

ዛሬ የፍቅር ጮራ ቦግ ብሎ ይታያል

በበዓለ ልደት ምክንያት የእግዚአብሔር መሃሪው ፍቅር አስተንትነናል፣ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ እስቲፋኖስ ሰምዕትነት በምታከብርበት ዕለት ደግሞ የኢየሱስ ተከታይ የሚኖረው ቃልና ተግባር ያጣመረ ታማኝ ሕይወትና ገዛ እራስ አሳልፎ የመስጠት አብነት እናስተነትናለን፣ አዳኛችን በዚህች ምድር መወለዱና ዛሬ ደግሞ የእርሱ ምስክር የሆነው ሐዋርያ በሰማይ መወለዱን እናከብራለን፣ ዛሬ እንደ ጥንቱ ጭለማም ለሕይወት እምቢ የማለቱ ተግባርና ምርጫ ይታያል፣ ሆኖም ያ ጥላቻን ድል የሚነሳው አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት የፍቅር ብርሃን ጎልቶ ይታያል።

ማሪያም ጸሎትን መስመር ታስይዛለች

ምህረት ለመቀበልና ለመስጠት ቅድስት ድንግል ማርያም አብነት ነች፣ ዕለት በዕለት ስለ እምነታቸው የደም ሰማእትነት የሚቀበሉት ብዙ ናቸው፣ እነዚህ ሰማዕታት ለማርያም እናወክፍ የወቅቱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰማዕታት ለእርሷ አማላጅነት እናወከፍ፣ እርሷ ምህረትን ለመቀበልና ለመስጠት የምናሳርገውን ጸሎት ትመራለች በማለት የለገሱት ስልጣናዊ አስተንትኖ ማጠቃለላቸው ሎሞናኮ አስታወቁ።
All the contents on this site are copyrighted ©.