2015-12-26 10:46:00

ብ.ር. ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቼስኮስ፦ “በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አዬ”


እዚህ  ሮም ላይ  በየዓመቱ  እንደሚሆነው ሁሉ  ዛሬ  ዛሬ  በጎርጎሩዮስ  የቀን  ቀመ የ2015 ልደተ ኢየሱስ  ክርስቶስ  ከፍ ባለ  ድምቀት እና ሽብርተኝነት ስለ ተሰጋ በከፍተኛ  ጥበቃ  እየተከበረ ነው ።
ይሁን እና በጥንታዊት  ሮም ከተማ  ከአስራ ሁለቱ  የክርስቶስ ሐዋርያት  ሁለቱ  ጰጥሮስ ወ ጳውሎስ  የሰማዕትነት አክሊል  የደፉባት እና መቀብሮቻቸው  የሚገኙባት  ከተማ  ከመሆንዋ  የሥነ ጥበቦች ማእከልም  በመሆንዋ   የአማንያን  መስህብ  መግሆንዋ  ይታወቃል።
ይሁን እና   ከአንድ ሳምንት  ጀምሮ  ለክብረ በዓሉ  አሻብርቃ  ትገኛለች ።
በተለይ ከደቡባዊ ጀርመን  ከባየርን  ክፍለ ሀገር  ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን  የተለገሰው በቅዱስ  ጰጥሮስ  አደባባይ  የተተከለው  33 ሜትር ቁመት ያለው   ግዙፍ የገና ዛፍ  እጅግ ይማርካል ።
በዚሁ  የገና  ወይም የልደተ ክርስቶስ ዛፍ  ግርጌ  ኢየሱስ ሕጻብ ሲወለድ   የሚያንጸብራቅ  በረት  የእንስሳት  መመገብያ  ኢየሱስ  መወለዱን  የሰሙ ሰብአ ሰገል  ከምስራቅ ክፍለ ዓለም በኮከብ ተመርተው  ህሕጻኑን   ለመየት እና ለመጐብኘት  እጅ መንሻ   ዕጣን  ከርቤ እና ወርቅ  ይዘው ሕጻኑን ሲገበ`ኙ  የሚያመልክቱ  ማራኪ  ምስሎች ይታያሉ  ።
 በውዳሴ  ማርያም መሰረት  ዕጣኑ  አምላክ   ከርቤ  መድኀን  ወቅ ንጉስ ስለ  ሆነ ነው ። ሮማውያን እና የሀገር  ጐብኝዎች   በብዛት  የቅዱስ ጰጥሮስ  አደባይ  ሲጐበኙ ይስተዋላሉ። 
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ  ትናንትና  ምሽት  የኩላዊት ቅድስት   ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ፍራንሲስ  በብጹዓን  በካርዲናሎች  እና ጳጳሳት   ተሸንተው  በቅዱስ  ጰጥሮስ  ባሲሊክ  የልደተ   ክርስቶስ  ሥርዓተ ቅዳሴ  መርተዋል ።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት  በቅድስት መንበር ማለት በቫቲካን  የተመደቡ አምባሳደሮች  እና በብዙ ሺ  የሚገመት ህዝብ   የዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ  ተሳታፊ   ሁነዋል ።ርእሰ  ሊቃነ ጳጳሳቱ   ሥርዓተ ቅዳሴ   ባሳረጉበት ጊዜ  ባሰሙት ስብከት  ወንጌል ላይ እደጠቀሱት  

ብ.ር. ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቼስኮስ በትላንትናው ምሽት በመንበረ በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስትያን የገናን በዓል ለማክበር ለተገኙት ምዕመናን ባሰሙት ስብከተ ወንጌል ላይ እደጠቀሱት  “በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አዬ” ”የእየሱስ መወለድ ለሁላችንም ታልቅ ብርሃን፣ ደስታንና በረክትን አመጣልን” ብለው ከነብዩ ኢሳያስ ከምዕራፍ 9፡ 2 ከጠቀሱ ቡኋላ፣ የሰማነው የእግዚአብሔር ቃል ወቅታዊ እና ተክክለኛ ነው፣ ይህንን ጊዜ በመናፈቅ እና በመጓጓት ስንጠባበቀው በመሰንበታችን አሁን ደግሞ ያ በጉጉት የጠበቅነው ጊዜ እና ሰዓቱ በመድረሱ ልባችን በታልቅ ደስታ እና እርካታ ተሞልቷል በለዋል።

አሁን ያገኘነው እውነተኛ ደስታ እና እርካታ የሚያሳየው ትክክለኛ እርካታ እና ደታን የሚሰጥ በዚህ ምሽት የተገለጠው ታላቁ የእግዚአብሔር ሚስጢር ቢቻ በመሆኑ ያለምንም ጥርጥር እውነተኛ ደስታ እና እርካት የሚገኘው ከእግዚአብሔር ዘንድ ቢቻ ስለሆነ ማንኛንም ጥርጣሬ አስወግደን በእግዚአብሔር  መተማመን ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሕፃኑ ኢየሱስ በዛሬ ዕለት የሚወለደው ሀዘንን በሙሉ ልያስወገደ በመሆኑ ቸልተኝነትን ከልባችን አስወግደን እንዳንዋደድ የሚያደርጉንን ነገሮችን ሁሉ ትተን ሕፃኑ ኢየሱስ ባመጣልን በደስታ እና በፍቅር በተሞላ ልብ ልንተካው ይገባል በለዋል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮስ።

ዛሬ የዓለም አዳኝ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ፣ የሰውን ተፈጥሮ ተጋርቶ በመወለዱ ሁሉንም ነገር ቀይሮታል ካሉ ቡኋላ በተለይም ደግሞ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ አድርጋ ለኛ በመስዋዕትነት ስላቀረበችልን እውነትኛ ብርሃን ሕይወታችንን ልያበራ እና ከሓጥያት ጨለማ ሊያወጣን በመምጣቱ በታልቅ ደስታ ልንቀብውል ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም ዛሬ ማን መሆናችንን የተረዳንበት ቀን ነው ምክንያቱም ወደ ፍፃሜያችን የሚመራን መንገድ በሕፃኑ ኢየሱስ ተገልጦልናልና ካሉ ቡኋል ፍርሃትንና ጥርጣሬን አስወግደን የተገለጠልንን የብርሃን መንገድ በመከተል ወደ ሰማያዊቷ እየሩሳሌም መጓዝ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በስንፍና ምክንያት በፍፁም ወደ ሁኋላ ማለት የለብንም ያሉት ቅዱስ ርዕሰ ጳጳስ ፍራንችስኮስ ወደ ፊት በመጓዝ የደስታችን እና የእርካታች ሁሉ ምንጭ የሆነውን በበረት የተኛውን ኢየሱስን በመመልከት “ሕፃንም ተወለደልን ለኛም ተሰጠን” የሚለውን የነብዩን ኢሳያስን እወጃ በማስታወስ፣ ጉዞአችንን በታማኝነት ወደፊት በመቀጠል ለሁለት ሺህ ዓመት ያህል በዓለም ውስጥ ሲመላለስ የነበርው ኢያሱስ የመጣው የሰዎችን ልብ በደስታ እና በእርካታ በመሙላት የእርሱን ተልዕኮ በማስቀጠል በዓለም ውስጥ ውጤታማ የሰላም መልዕክተኞች ልያደርገን በመሆኑ   የድርሻችንን ልንወጣ ያስፈልጋል ብለዋል።

በማከልም ይህንን የልደት በዓል በጥሞና ሕፃኑን ኢየሱስ እዲናገረን በመጋበዝ ልናከብር ይገባል ብለው ሕፃኑ ኢየሱስ የሚናገረንን በጥሞና በማዳመጥ እና በማሰላሰል ወደ ልባችን ቃሉን ልናስገባ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ በርሱ በመባረክም ዘላለማዊ የሆነውን የልብ ሰላም እንዲሰጠን ልንጋብዘው ያስፈልጋል ብለዋል።

ምንም የማረፊያ ቦታ በማጣቱ ለከብቶች ማደርያ በተዘጋጀ በረት ውስጥ ሕፃኑ ኢየሱስ መወለዱ በሕወታችን በጣም ጠቃሚ ነገር ያስተምረናል ያሉት ቅዱስ አባታችን የምያስገርመው እና የምያስደንቀው ነገር ደግሞ ከዚህ ደሃ ሕፃን የወጣው ታላቅ ብርሃን ለዓለም ሁሉ ብርሃን መሆኑ ሲሆን ይህ ታላቅ ብርሃን ደግሞ ለብዙዋቹ ቅን ልብ ላላቸው ሰዎች ሁሉ የመዳን ምንጭ በመሆኑ እኛም ኢየሱስን የምናገኘው ትሁት እና እራሳችንን ዝቅ ስናደርግ ቢቻ ነው ብለዋል።

በሕፃኑ ኢየሱስ ፊት ላይ የሚታየው መልካምነት፣ ምህረት እና የእግዚአብሔር ፍቅር የሚያስተምረን እኛም የእርሱን አብነት በመከተል ሓዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቲቶ በምህራፍ 2፡ 12 ላይ እንዳሳሰበን “ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ እራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እውነታኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር” ያሳስበናል እና በዚህ የገና ወቅት ለእርሱ የተገባ ሕይወት እንዲኖረን ያስፈልጋል ብለዋል።

በማከልም በዚህ በግዚያዊ ደስታ ላይ ኑሮውን መሰረት ያደረገና ሀብት በማባከን እና በእራስ ወዳድነት የመመረዘ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለደው ሕፃኑ ኢየሱስ በተረጋጋ እና ቀላል በሆነ ቋንቋ ሕይወታችንን በተርጋጋ እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የሌሎችን ፍላጎት ባማከለ እና ባገናዘበ መልኩ በተገቢው ሁኔታ እንድንኖር ይጋብዘናል ብለዋል።

በስተመጨረሻም በዚህ ለደካሞች ምህረት የለሽ እና ለሓጥያት ምህረት የማድረግ መንፈስ እየቀነሰ በመጣበት ዓለማችን፣ የሓጥያትን መንገድ አስወግደን በምትኩም የፍትህን መንገድ በመከተል እና ወደ እግዚአብሔር ሀሳብ በመከተል እና  በመምረጥ፣ የግዴለሽነትን ባህል በማስወገድ ለራሳችን ቢቻ ማሰብ ትተን በምትኩም ታማኝ፣ በምህረት የተሞላን፣ አዛኝ፣ ምህረት አድራጊዎች እና በተለይም ደግሞ በፀሎት የተደገፈ ሕይወት እንዲኖረን ያስፈልጋል ብለዋል። በኢየሩሳለም እንደነበሩ እረኞች እኛም የኢያሱስን ድንቅ ብርሃን እና ታዐምር እንድናይና ልባችን በታልቅ ደስታ ተሞልቶ ልክ ዳዊት በመዝሙሩ በምዕራፍ 85፤7 “እግዚአብሔር ሆይ ምሕረትህን አሳይን ማዳንህንም ስጠን” እናዳለው እኛንም እግዚአብሔር በምሕረቱ እንዲጎበኘን የምንፀልይበት ወቅት ሊሆን ይገባል ሲሉ ስብከተ ወንጌላቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.