2015-12-24 10:33:00

ቅ.ዩሓንስ ፓውሎስ 2ኛ፣ የመጀመሪያውን የቫቲካን የመረጃ መረብ ቫቲካን.ቫ የዛሬ 20 አስጀመሩ


እ.አ.አ በታህሳስ 25. 1995 ቅዱስ ዩሓንስ ፓውሎስ ሁለተኛ፣ የመጀመሪያውን የቫቲካን የመረጃ መረብ ማለትም ቫቲካን . ቫ በማስጀማራቸው፣ ቫቲካንን አድስ በመረጃ መረብ የታገዘ አገልግሎት እንዲኖራት አስችለው፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ይህንን ዘመናዊ የማህበራዊ የመረጃ መረብ አገልግሎት በመጠቀም የወንጌል አገልግሎቷን በመላው ዓለም በተቀላጠፈ እና በተፋጠነ መልኩ እንድታስተላልፍ በመረጃ መረብ ዓለም ውስጥ ቤተ ክርስትያንን በመቀላቀላቸው በታሪክ ስወሱ ይኖራሉ ሲል አለሳንድሮ ጊዞቲ ዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ ከጋዜጠኞ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ የሰጡት የቫቲካን የመረጃ መረብ ኋላፊ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሉቺዮ ሀድሪያን ሩሁዝ እንደገለፁት የዛሬ 20 ዓመት ቫቲካን.ቫ የሚለውን የመረጃ መረብ በመክፈት ቤተ ክርስትያን ዘመናዊ በሆነ መልኩ የወንጌል አገልግሎቷን እንድታከናውን በእንግልዘኛ ምፃረ ቃል WWW ወይም (World Wide Web) እንድትሳተፍ እና ተክኖሎጅ ባፈራው ዘመናዊ የአሠራር ባህል ውስጥ በመሳተፍ ክርስቶስን መመስከር እድትችልና ክርስቶስ ሁል ጊዜ ከሰዎች ጋር እንደሚጓዝ ሁል ቤተ ክርስትያንም ከሰዎች ጋር መራመድ እንድትችል ስላስቻሏት ቅዱስ ዩሓንስ ፓውሎስ ሁለተኛ ሁል ጊዜም ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ብለዋል።

ቅዱስ ዩሓንስ ፓውሎስ ሁለተኛ በፃፉት ቀጣይነት ያለው ልማት በእንግልዘኛው Rapid Development በሚለው ሰነዳቸው ላይ እንዳሰፈሩት “ማሀበራዊ ግንኙነት በተለይም ደግሞ የመረጃን መረብ በመጠቀም የሚደረግ ግንኙነት ቤተ ክርስትያንን በተሻለ መልኩ መንፈስዊ አገልግሎቷን እንድትወጣ ስለ ሚያስችላት አጠናክራ ልትቀጥል ይገባል” ብለዋል።

በመንበረ ጵጵስና ላይ በነበሩበት ወቅት “አትፍሩ፣ የቤተ ክርስትያንም በሮችዋን ለሁሉም ትክፈት” በሚለውን የሳቸዉን መሪ ቃል ቤተ ክርስትያን ለሁሉም ተደራሽ መሆን እንዳለባት በማሳሰብ፣ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የመረጃ መረብን መጠቀም አስፈላጊ ነዉ በማለታቸው እና በቅርቡም ደግሞ ቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ “የቤተ ክርስትያንን በር ክፈቱ የጠፉትንም ለመፈለግ ውጡ” በማለት እንዳሳሰቡት ቤተ ክርስትያን ያላንዳች ፍርሀት እና መሸበር በሮቿን ከፍታ ለሎችን ለምፈለግ በምታደርገው ጥረት ውስጥ የምህበራዊ መረብን መጠቀም አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም ብለዋል።

ቅዱስ አብታችን ፍራንችስኮስ “ እኔ የምፈልጋት ቤተ ክርስትያን ከሁሉም ጋር የምትጓዝ እና በሰዎች ልብ ውስጥ የምትቀር ቤተ ክርስትያን እንጂ በርዋን እንደታመመ ሰው ዘግታ የምትቀመጥ በተክርስትያንን አይደልም“ እናድሉት የምህበራዊ የመረጃ መርብ ተደራሸነቱ ከፊተኛ በመሆኑ ለቤተ ክርስትያን መንፈስዊ አገልግሎት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ የመረጃ መረብ በአብዛኛውን የቤተ ክርስትያንን ተኩረት የሳበ ሲሆን በተለይም ደግሞ ይህ የመረጃ መረብ ሁሉንም የሰው ልጆች በቀላሉ የሚየጋናኝ በሆኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ቁሳዊ በሆኑ እሴቶቹ ቢቻ ላይ ተመርኩዞ ሳይሆን በተቃራኒው ሰዎችን በማቀራረብ እና አቅፎ በመያዝ አንድ ዓለማቀፋዊ መንደር በመመስረት ሰዎች ስለ ማሀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስለ ፖለቲካዊ ህይወታቸው በመውያየት ለችግሮቻቸው መፍትሄ የሚፈልጉበት እና የሚቀራረቡበት ቦታ በመሆኑና በተጨማሪም ይህንን የምህበራዊ የመረጃ መረብ በመጠቀም የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሰዎች ሁሉ በቀላሉ ማዳረስ ስለሚቻል በመሆኑ ጭምር ትኩረት ይሰጠዋል ብለውል።

በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ሉቺዮ ሀድሪያን የማሀበራዊ የመረጃ መረብ እንደ አንድ የመገናኛ ቦታ ሊታይ ይገባል ካሉ ቡኋል በተለይም ወጣቱ ትውልድ የተለያዩ መረጃዎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ፎቶውችን፣ ሀሳቦችን እና መልዕክቶችን የሚለዋወጥበት አገናኝ ቁስ በሆኑ የሰዎች የመገናኛ ስፍራ ሆኖ የምያገለግል ስለሆነ ቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ “ማሀበራዊ የመረጃ መረብ ሰዎችን የሚያገናኝ እና የሚያቀራርብ በመሆኑ “ከእግዚብሔር የተሰጠ ስጦታ” ነው እናዳሉት ሁሉ ይህንን የማህበራዊ የመገናኛ መረብ በመጠቀም ክርስትያኖች ስል ህይወታቸው፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ማህበራዊ እድገታቸው በሚገባቸው ቋንቋ እንዲገናኙ ስለሚያደርጋቸው ቤተ ክርስትያን አስፈላጊነቱን በማመን በአግባብ ክርስትያኖች እንዲጠቀሙ ታበረታታለች።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሉቺዮ ሓሳባቸውን ስያጠቃልሉ በዚህ በያዝነው የምህረት ዓመት የመረጃ መረቦችን ክርስትያኖች እግዚአብሔርን ምህረት አባት መሆኑን በመግለፅ እርስ በርሳቸው ይቅርታን በመባባል፣ ፈቅርን በመስበክ፣ ገንቢ የሆኑ ሓሳቦችን በመለዋወጥ ክርስትያናዊ የሆነ መረብ በመዘርጋት በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ምህረትን እስከ ዓልም ዳርቻ በማወጅ እና ማሰራጨት ላይ ያተኮረ አጠቃቅውም እንዲኖራቸው በመምከር ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.