2015-12-23 14:52:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መንፈሳዊ ብርታት ወጌላውነት ባህርይ ያለው ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በየዓመት እንደሚደረገው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የተለያዩ ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርትና የቅዱሳት ማኅበራት ኅየንተዎችን አገረ ቫቲካን በሚገኘው ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው ለበዓለ ልደት የመልካም ምኞች መግለጫ መልእክት ለማስተላለፍ ባሰሙት ሥልጣናዊ ምዕዳን የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሊከተለውና ሊኖረው የሚገባው ባህርይና የመልካም ጠባይ ዝርዝር በመተንተን ይኽ ደግሞ የተገባው ቅዱስ የምኅረት ዓመት በሚገባ ለመኖር የሚደግፍ መሆኑ አስምረውበታል፣ ከዚሁ ጋር በማያያዝም የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካላት መዋቅሮች ያልተገቡ ባህርዮችና ግድፈቶች በዝርዝር በማስቀመጥ የሰጡት ማብራሪያ ዙሪያ የቲዮሎጊያ ሊቅ የሶፊያ መንበረ ጥበብ ተቋም ሊቀ መንበር ዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት አባል አባ ፒየትሮ ኮዳ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ይላሉ እንደ ተለመደው በትክክልና ካላቸው እረኛዊ ዓቢይ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተመክሮና ባላቸው የማመዛዘን መፍንሳዊነት ብቃት በትክልል ማኅበረ ክርስቲያን ልብ ውስጥ ያሉት ጥያቄዎች አስተሳሰብና አስተያየት ሁሉ የሚወክል ተጨባጭ ምዕዳን በማቅረብ አንድ ሰው ወንጌላዊ ልክነት ያለው ሕይወት እንዴትና ለምን መኖር እንዳለበት አስረድተዋል።

ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በቅድሚያ ወንጌላዊነት ለበስ ሕይወትና ከቃለ ለወጌል ጋር የማይጋጭ ሕይወት መኖር እንደሚገባውና ከዚህ ጋር በማያያዝም የፈጠራ ብቃትና ሰብአዊ ለበስ መሆን አለበት የሚል ነው። የሚበሰረው ወንጌል ስኬታማነቱ አገልጋዮች ወንጌላውያን ጥልቅ ሰብአዊነት የሚኖሩ ባህላዊ ብቃት ያላቸው ወንጌላዊ ሕይወት በቃልና በተግባር የሚኖሩ ሆነው ሲገኙ ነው።

ገርነት አክባሪነትና አምልኰ ወደ የእግዚአብሔር ልብ የሚመሩ ተግባሮች ናቸው፣ ስለዚህ ለተልእኮና ለአገልግሎት ከልበ እግዚአብሔር ጋር መገናኘት ያስፈልጋል። ይኽ ደግሞ ያንን እግዚአብሔር በአንድ ልጁ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የገለጠው መሆናዊ መኖር ያለው አስፈላጊነት የሚያበክር ሃሳብ ነው። እግዚአብሔር በእኛ ሰብአዊነት ድካም የማይወሰን ነው፣ ሆኖም የእኛ ዕለት በዕለት በወንጌላዊነት ሕይወት ማደግ ይሻል።

እርግጥ ነው ሰብአዊ ድካምነት የለም መኖር የለበትም የሚል ምዕዳን አይደለም፣ ሰው በባህርዩ ደካማ ነው፣ ሆኖም ደካሞች ነን እየተባለ ነገሮች ባሉበት እንዲቀጥሉ ሁሉን ነገር እያዩ እንዳላዩ ሆኖ መኖር መስተካከል እንደሚገባው የታወቀ ሆኖ እያለ ነገር ግን ተመሳስሎ ለመኖር እየተባለ በዝምታ ማለፉ ነቀርሳ ይሆናል፣ እንዳላዩ ሆኖ ማለፉ ቀስ በቀስ ሁለ መናን ይበክልና ለሞት ይዳርጋል፣ ስለዚህ እውነትና መንገድ የሆነውን ኢየሱስ መከተል ያለው አስፈላጊነት በስፋት ገልጠዋል ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.