2015-12-23 14:55:00

ህንድ፦ ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ በዓለ ልደት የምኅረት በዓል ነው


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. የምህረት ቅዱስ ዓመት ምክንያት የሙምባይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦስዋልድ ግራሲያስ በህንድ ባንዳራ ከተማ የሚገኘው በደብረ ማርያም ባዚሊካ ቅዱስ በር የመክፈት ሊጡርጊያ ፈጽመው ባደመጡት ስብከት፦ በዓለ ልደት የእግዚአብሔር ዓቢይ የምህረት ጸጋ ነው። ስለዚህ የአንድ አቢይ አብዮት በዓል ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሕረት ዓለም የሚለውጥ ነው። እውነተኛው የሚለውጥ አቢዮት የጌታ ምህረት ነው እንዳሉ የሼያን ኔውስ የዜና አገልግሎ አስታወቀ።

የሚከበረው በዓለ ልደት በተገባው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ምክንያት አቢይ ትርጉም በእጥፍ ይስተጋባል፣ ብፁዕ ካርዲናል ጋርሲያ በዓለ ልደትና የምህረት ዓመት በማጣመር ባስደመጡት ስብከት፦

ምኅህረት የወንጌል ማእከላዊ መልእክት ነው

በዓለ ልደት ስናከብር ልባችንን ለምህረት እግዚአብሔር እንከፍታለን፣ ምህረት የወንጌል አንኳር መልእክትና ተግባር ነው። ያንን በብሉይ ኪዳን የሚገለጠው እግዚአብሔር በሙላት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ገልጦልናል፣ ይኽ ደግሞ የምህረት ግልጸት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅርና የድህነት ትስብእት ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ ገለጠ።

ሁላችን ምኅረት ያስፈልገናል

የቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊን በመክተል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይነት ተልእኳቸው አንኳር የእግዚአብሔር ምኅረት የሚል ነው። ምኅረት ጥልቅ ፍቅርና የግዚአብሔር ፍቅር ቀጣይነት ዘለዓለማዊነት ማለት ነው። ስለዚህ እያንዳንዳችን ምኅረት ፈላጊዎች ነን፣ ምኅረት የማያስፈልገው ማንም የለም፣ የእግዚአብሔር ምኅረት ለመቀበልና ተቀብለንም ለሌሎች ለማካፈል እንድንችል ልባችንን ለምኅረቱ እንክፈት፣ ይኽ ደግሞ የመኃሪው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ያደርገናል በተግባር ይገልጣል። የእግዚአብሔር ፍቅር ለባለንጀራ በመመስከር መፈቀራችንን መኖር፣ ይኽ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰከረው የምኅረተ አብዮት ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.