2015-12-21 17:27:00

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


በተባበሩት መንግሥታት አመሪካ በዓለ ልደት ምክንያት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መልእክት ማስተላለፋቸው ሲር የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ ብፁዓን ጳጳሳቱ የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ኩርትዝ ፊርማ የተኖርበት መልእክት አማካኝነትም፣ በአሁኑ ሰዓት አክራሪያንና ጽንፈኞች እያረማመዱት ያለው ስጋትና ፍርሃት የአገሪቱ ሕዝብ አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት በጽናትና በአድነት እንዲጋፈጠው በማሳሰብ፣ አመጽ ጥላቻ በቆራጥነት መንፈስ ሊገጠም ይገባዋል እንዳሉ አስታወቀ።

ክርስቲያኖች የተስፋ መልእክተኞች ይሁኑ

የብፁዓን ጳጳሳት መልእክት በቅርቡ በካሊፎርኒያ ለ 14 ንፁሓን ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነው እስላማዊው አገር የተበቀለው የሽበራው ጥቃት በማስታወስና በማውገዝም በዚህ በአሁኑ ወቅት ቀቢጸ ተስፋነትና ልዩነት በሚያንዣብበት ዓለም ማኅበረ ክርስቲያን የተስፋ መልእተኞች እንዲሆኑ አደራ በማለት፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ለማክበር ቤተ ክርስቲያን በምትከናውነው መንፍሳዊና ሰብአዊ ቅምደ ዝግጅት በመሳተፍ እንዲመሰክሩት ጥሪ ማቅረባቸው ሲር የዜና አገልግሎት ጠቁሞ፣ በእግዚአብሔር ስም ሰውን ለሞት መዳረግ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚቃወም ጸረ እግዚአብሔር ተግባር መሆኑ በማብራራት ለፍቅር ለሰላም ለፍትህ እንትጋ ማለታቸውንም አስታውቀዋል።

ስለደተኛው የሚያስተዳድረው ሕግ ሰብአዊነት እንጂ ፍርሃት የሚወልደው እንዳይሆን

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ጸጥታና ደህንነት ለአደጋ የማያጋልጥ ሰብአዊነት ማእክል የሚያደርግ እንጂ ፍርሃት መሠረት ያደረገ የስደተኛው የማስተዳደሪያ ሕግ እንዳይወጠን አደራ በማለት፣ ፍርሃት ላይ የሚጸናው ፖሊቲካ አክራሪነትን የሚያበረታታና ለአክራሪነት ለም መሬት በመሆን የመከፋፈልና የልዩነት አጥር የጸናበት ፍርሃትና መከፋፈል የሚነግሥትበት መጻኢ እንዲከወን ያደርጋል። ስለዚህ ስደተኛው የመተዳደሪያው ሕግ አድልዎ ለማስወገድ የሚያግዝ ሁሉንም የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራ ሰላማዊት አገር ለመገባንት ፈር የሚያስዝ መሆን ይገባዋል እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ብፁዓን ጳጳሳቱ ከተለያዩ ግጭትና አድልዎ ከሰፈነባቸው አገሮች ለሚሰደደውና ለሚፈናቀለው ዜጋ፣ ለአካልና ለአምሮ ስንኩላን ሁሉ ቅርበትና ደጋፍ በማረጋገጥ፣ መንግሥታት ለጸረ ሰብአዊ አደጋ የሚጋለጠው ሁሉ ትብብር በማቅረብ የተረጋጋ መጻኢ ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት በመደገፍ የሰላም መሣሪያ ሆነው እንድገኙም በማሳሰብ እ.ኤ.አ. 2016 አዲስ አመት ለመቀበል የሚደረገው በዓል ሰብአዊነት ልክ ያለው እንዲሆን አደራ ማለታቸውንም ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.