2015-12-21 17:23:00

የሊባኖስ ርእሰ ብሔር ምርጫ


የሊባኖስ ርእሰ ብሔር የመምረጡ ሂደት እ.ኤ.አ. ከ 2014 ዓ.ም. ወዲህ ለምሻነት አጋጥሞት ይኸው አገሪቱ እስካሁን ድረስ አለ ርእሰ ብሔር እንዳለች የሚታወስ ሲሆን፣ የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ሰልፎችና እንዲሁም መጻኢ ለተሰየመው የፖለቲካ ሰልፍ መሪ ሳአድ ሃሪሪ ጭምር ሱለይማን ፍራንጃሀ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመን እንደሚሹ ይፋ ሲያደርጉ፣ አንዳንድ ታዛቢ አካላት እንደሚሉትም ፍራንጃህ የመምረጡ ፍላጎት ውድቅ እየሆነ

መምጣቱ ቢናገሩም፣ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ርክስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል በቻራ ቡትሩስ ራይ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ከ 2015 እስከ 2016 ዓ.ም. የሥራ መባቻ ምክንያት ባስደመጡት ንግግር፦ ሱለይማ ፍራንጃህ የመምረጡ ፍላጎት አቢይ ግምት ሊሰጠው የሚገባውና አገሪቱ አለ ርእሰ ብሔር ያስቀራት አለ መግባባት እልባት እንዲያገኝ የሚያደርግ ፍላጎት ነው። በመሆኑም ሁሉም የፖለቲካ ሰልፎች ይኸንን እድል ውድቅ እንዳያደርጉ መማጠናቸውና ሊባኖስ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እንዲሁም በጸጥታና ደህንነት ጉዳይ ጭምር ለአደጋ እያጋለጣት ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ የፖለቲካ አካላት አቢይ ግምት በመስጠት ፍራንጃህ ለርእሰ ብሔር የሚለው ሃሳብ ትኩረትና አወንታዊ መላሽ ሊሰጡበት ያፈልጋል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.