2015-12-21 17:19:00

ለበዓለ ልደት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምስለ ሕፃነ ኢየሱስ ባረኩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከበረው የጌታችን ኢየሱስ በዓለ ልደት ምክንያት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደ የቤተ ክርስቲያን ልምድና እንዲሁም በተገባው የምህረት ዓመት ጋር በተያያዘ መልኩ ለሚከበረው የቤተ ክርስቲያን አባላት ወጣቶችና ሕፃናት ኢዮቤልዩ ቀን ምክንያት ጭምር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሚገልጠው ግርግም የሚቀመጠውን የሕፃን ኢየሱስ ምስሎችን መባረካቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት ምዕዳን፦ ውድ ሕፃናትና ወጣቶች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መግለጫ ግርግም ፊት ስትጸልዩ እኔ እንደማስባችሁ እናንተም በጸሎታችሁ አስቡኝ” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አያይዘው፦ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ከተለያዩ የሮማ ቁምስናዎች የተወጣጡ ጧት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ሊቀ ካህናት የአገረ ቫቲካን ኅየንተ የቅዱስ ጴጥሮስ ተግባራዊ ሙያ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ በባዚሊካ ቅዱስ ጴጥሮስ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ የተሳተፉት  በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለተሰባሰቡት የቤተ ክርስቲያን ታዳጊና ወጣቶች ማኅበር አባላትን ሁሉ ሰላምታን አቅርበው በዓለ ልደት መንፈሳዊና ሰብአዊ ኅዳሴ ይጸግው ዘንድ መማጠናቸው አስታውቀዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ ባሰሙት ስብከት እንደ አብነት የማድረ ተረዛ ዘካልኵታ ተክለ ሰብነት ጠቅሰው፣ ያ ሕፃን ኢየሱስ ኃይልና ቡራኬ እንደሆናቸውና በዚያ ድኽህነት ጉስቁልና በሚታይበት ጎዳና በመሄድ በችግር ላይ የሚገኙትን ለመንከባከብ እንዳበቃቸው አብራርተው፦ ያንን ኃይል ማድረ ተረዛን የሰጠው ያ እናንተ ሕፃናት የምታመልኩት በበዓለ ልደት ምክንያት በየቤታችሁ የምታኖሩት ቅዱስ ሕፃነ ኢየሱስ ነው። ይኽ ቅዱስ ባህል ለቤተ ክርስቲያን ያወረሰው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ መሆኑም ዘክረው፣ ቅዱስ ቪንቸንዞ ደ ፓውሊና እናቴ ብፅዕት ተረዛ የመንፈሳዊነትና ያገልግሎት ማእከል ያደረጉት የቅድስት ድንግል ማሪያም ልጅ ሕፃነ ኢየሱስ ነው እንዳሉ ታማሮ ገለጡ።

የሮማ የቁምስናዎች ቤተ ጸሎት ማኅበር የተቋቋመበት 70ኛው ዓመቱ በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት ያ ማኅበር ሕፃናትና ወጣቶች በተገባ መንፍሳዊና ሰብአዊ ሕንጸት ያስደናዳ በማሰናዳት ላይ የሚገኝ ማኅበር ነው። ታዳጊዎችና ወጣቶች ቅዱስ እምነት ማእከል የሚደረገ የወዳጅነትና የጓደኝነት ሥፍራ ሲኖራቸው እንዴት ደስ ያሰኛል፣ ይኸንን የታዳጊዎችና የወጣቶች ማኅበር በቁምስናዎች ተቋቁሞ በዚሁ ዘርፍ የሚያገለግሉት ሁሉ እናመሰግናለን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አስታወቁ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.