2015-12-19 14:22:00

ቅዱስ አባትችን ፍራንሲስ በእማሆይ ትሬዛ አማልጅነት የተፈፀመውን ተአምር አፀደቁ


ቅዱስ አባትችን ፍራንሲስ ብፁዕ እማሆይ ትሬዛን ለቅድስና የሚያበቃቸውና በእርሳቸው አማላጅነት የተፈፀመውን ተአምር በይፋ ተቀበሉ። በትላንትናው ዕለት በካርዲናል አንጀሎ አማቶ የቀረበላቸውን ሰነድ ቅዱስነታቸው ተቀብለዉ ከመረመሩ ቡኋላ በብፁዕት እማሆይ ትሬዛ አማላጅነት እ.አ.አ 2008 በብራዚል በአንድ ስሙ ባልተጠቀሰ በጠና አዕምሮውን በአደጋ ምክንያት ታሞ የነበረ ሰው በሚያስገርም ሁነታ ከህመሙ በመፈወሱ ይህ ተአምር ለቅድስናቸው የሚያበቅቸው በመሆኑን ቅዱስነታቸው ተቀብለው አፅድቀዋል ሲል አሌሳንድሮ ካርሎስ ዘግቡአል።

እ.አ.አ በመስከረም 10.1948 በቀድሞ የሎሬቶ የማህበር ስማቸው ማርያ ትሬዛ፣ በህንድ ሀገር በካልካታ እና ዳርጄልንግ ግዛቶች መካከል በባቡር በሚጓዙበት ወቅት፣ በመንገድ ላይ በመከራ እና በስቃይ የማቀቁ ሰዎችን በተመልከቱ ጊዜ በጣም በማዘናቸው ገና በሰላሣ ስምንት ዓመታቸው በቀጣይነት በፈፀሙት በጎ ሥራቸው በዓለም ላይ ጎልተው እንዲወጡ አስችሏቸዋል። ለዚህም ብፅዕት እማሆይ ትሬዛ እንደ ምክንያት የሚገልፁት ደግሞ “ ይህንን ታልቅ የሰው መከራ ባየሁበት ምሽት ላይ አይኖቼን በጣም ለሚሰቃዩ ሰዎች በመክፍት የጥሪዬን ባህሪ በጥልቀት እንድረዳ አስችሎኛል” ካሉ ቡኋላ “በእርጋታ የምኖርበትን የማህበር ሕይወት በመተው የሚሰቃዩትንና በየመንገዱ የተበታተኑትን ድኾች እዳገለግል ጌታ እየጠራኝ መሆኑን በመረዳቴ እና ጌታ የሚያቀርብልኝ ጥሪ ወይም ጥያቄ ቢቻ ሳይሆን ቀጥተኛ ትዕዛዝ መሆኑንም በሚገባ በመረዳቴ ለዚህ የጌታ ትእዕዛዝ ደግሞ መልስ መስጠት እናዳለብኝ በሚገባ ተረድቻለው” በማለት ለዚህ ታላቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ሕይውታቸዉን አሳልፈው ሰተዋል።

ከስልሳ አመት ቡኋልም እ.አ.አ. በመስከረም 10.2008 አንድ ብራዚላዊ የምህንድስና ሠራተኛ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ አደጋ መክንያት እራሱን በመሳት ወደ ሆስፒታል ለቀዶ ህክምና በገባበት ወቅት ባለበቱ እና የቅርብ ወዳጆቹ ከአንድ ካህን ጋር በሆስፒታሉ ፀሎት ቤት በመሆን በተለይም ደግሞ እማሆይ ትሬዛ እርሷን እና ባለቤቷን በእርሳቸው አማላጅነት እግዚአብሔር እንዲፈውሳቸው አጥብቀው ይፀልዩ በነበረበት ወቅት ብዙም ሳይቆይ የቀዶ ህክምናው ሀኪም ለቅድመ ዝግጅት ከቀዶ ህክምናው ክፍል ለጥቂት ደቂቃዎች ወጣ ብሎ በሚመለስበት ጊዜ በሽተኛውን በአልጋ ላይ ተቀምጦ እናዳገኘው በመግለፅ በሽተኛውም “እዚህ ምን እየሠራው ነው?” ብሎ ሀኪሙን እንደጠየቀ እና በቅጣይነትም በተደረገለት ምርመራ ከነበረበት በሽታ ሁል መዳኑን እና ምንም አይነት የጤና እክል እንደ ማይታይበት፣ በአደጋ ተጎድተው የነበሩት የጭንቅላት ክፍሎቹ ሙሉ በሙሉ መዳናቸውንና ሙሉ በሙሉ ከበሽታው መፈወሱን ሀክሞች በማረጋገጣቸው፣ የዝህን ዓይነት ታአምርም በህይዎታችው አይተውት የማይውቁት ከሞት እንደ መነሳት የሚቆጠር ታምር በመሆኑ ለበሽተኛ የጤና ማረጋገጫ ወረቀት በመስጠት አሰናብተውታል።

የዚህ አዓነቱ “የመጀመሪያ ደረጃ ተአምር” በቅዱሳን አማላጅነት ሲፈፀም የመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ይህንን ተአምር ለየት እንድምያደርገው፣ ለቅዱስ አባታችን በቀረበው ሪፖርት ላይ ተገልፆ፣ በአብዛኛው እና የተለመደው በቅዱሳን አማላጅነት የሚፈፀሙት ታአምራት ግን “በሦስተኛ ደረጃ” የምጠቀሱ ማለትም በቆይታ ለውጥ የሚያሳዩ ታአምራት በምሆናቸው ይህንን ታአምር ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.