2015-12-18 16:34:00

ቅዱስ አባታችን፦ ኢየሱስን የምንገናኘው በድኾች ነው


በካሪታስ ለሚጠራው ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ሮማ በሚገኘው የማኅበሩ ቅርንጫፍ ሥር የሚተዳዳረው ድኾችን የጎዳና ተዳዳሪዎች የሕክምና የመጠለያ አገልግሎትና የምግብ እርዳታ የሚቀርብበት ማእከል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ሓውጾተ ኖልዎ በማካሄድ በመጠለያው ጣቢያ በሚገኘው የድኽች ማእድ ቤት የሚገኘው አቢይ በር በዚህ በተገባው የምኅረት ዓመት ምክንያት ቅዱስ በር ብለው በመሰየም ቅዱስ በር የመክፈት ሥነ ስርዓት መፈጸማቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኒና ኦአዘልት ገለጡ።

ሮማ ለሚገኘው የካሪታስ ቅርንጫፍ አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ኤንሪኮ ፈሮቺ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምህረት ቅዱስ አመት በማወጅና በትህትና ማስጀመራቸው በሁሉም ዘንድ አግርሞት አሳድረዋል። እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን በሚከበረው በዓለ ንጽሕት ድንግል ማርያም ቀን በይፋ ቅዱስ በር በመክፈት የምኅረት ዓመት በይፋ አስጀምረዋል። ቅዱስ በር ለሁሉም ክፍት ነው። የጌታ ምህረት ለሁሉም ነው። የሮማው የድኾች መጠለያ ማእከል ውስጥ ያለው የድኾች ማዕድ ቤት ዋናውን የመግቢያው በር በመክፈት ቅዱስ አባታችን ቅዱስ በር የመክፈት ሥነ ስርዓት ፈጽመዋል።

በዚያ አዳራሽ በየቀኑ ለ 500 የጎዳና ተዳዳሪዎች የማእድ እርዳታ የሚቀርብ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው በዚያ አዳራሽ ተገኝተው የድህነት ማእድ የሆነውን ከተለያዩ ሃይማኖት የተወጣጡ ተረጅ ድኾችና የዚያ የተራድኦ ማእከል አገልጋዮች የበጐ ፈቃድ አባላት ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። የድህነት ማእድ ለሁሉም።

በዚያ የእርዳታ መስጫ ማእከል የጎዳና ተዳዳሪዎች የምግብ የህክምና እርዳታ እንዲሁም የማደሪያ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ሲታወቅ፣ ይኽ ማእከል እ.ኤ.አ. በ 1987 ዓ.ም. በዚያኑ ወቅት የሮማው የካሪታስ ቅርንጫፍ አስተዳዳሪ በነበሩት በአባ ልዊጂ ዲ ሊየግሮ ለጎዳና ተዳዳሪዎች መጠለያ ምግብ አቅርቦት መርህ በማድረግ የተመሰረተ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኦአዘልት በማስታወስ፣ የምኅረት ዓመት የልብ በር ለድኻው ክፍት በማድረግ በድኻው ቅዱስ በር አማካኝነት ወደ ኢየሱስ መግባት የዘንድሮው የካሪታስ መንፍሳዊ መርሆ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ፈሮቺ አስታውሰው ከቫቲካን ረድዮ ጋር ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.