2015-12-18 16:38:00

ሰላም በቅድስት መሬት


በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፍዋድ ትዋል በዚህ እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. የሚከበረው የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ በዓለ ልደትና እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ የተገባው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ምክንያት በማድረግ ለቅድስት መንበር ለካቶሊክ ምእመና ሐዋርያዊ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ ያጠናቀሩት ዘገባ ይጠቁማል።

ብፁነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በቅድስት መንበር ለበዓለ ልደት ምክንያት ዓለም አቀፍ ውሳኔ እንዲከበርና የእስራኤልና የፍልስእጤም የሰላም አስተንፍሶ እንዲደመጥ አደራ መባሉንም የብፁዕነታቸው ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዊሊያም ሾማሊ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ከባለፈው ጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም. ወዲህ በክልሉ አዲስ ውጥረት የተቀሰቀሰ ሲሆን፣ ከፍልስጥኤም ለሚሰነዘረው ጸረ እስራኤላውያን ጥቃት እስራኤልም የግብረ መልስ ጥቃት በመሰንዘር የሚታየው ሁነት በክልሉ ያለው ውጥረት መባባሱ ምስክር ነው፣ ፍልስጥኤማውያን ሰማእትነት ብለው የሚገልጡት ጥቃት እስራኤል የሽበራ ጥቃት በማለት ትገልጠዋለች፣ ይኽ እልባት ያጣው ግጭት የሚፈታው በመግባባት በመወያየትና ለክልሉ የዓለም አቀፍ ውሳኔ እግብር ላይ እንዲውል በማድረግ ነው ብለዋል።

ግጭቱ በፍልስጥኤም የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች አል አቕሳ በአይሁዶች የቤተ መቅደስ ተራራ በማለት በሚጠራው ክልል የሚታይ ነው። በዚህ ክልል አንዳንድ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ሦስተኛው የአይሁድ ቤተ መቀደስ እንዲገነባ የሚያቀርቡት ሃሳብ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ፍልስጥኤማውያን እንደማይቀበሉት ነው። የውጥረቱ አንዱ መንሳኤም እርሱ ነው፣ ሌላው ምክንያትም ሁለት ሉአላውያን ጎረቤት አገሮች የሚል ፍልስኤም እንደ አገር እውቅና የሚያሰጥ ፖለቲካዊ የመፍትሔ ውሳኔ ገቢራዊ የማድረጉ ፍላጎት እየዘገየ በመምጣቱም ነው ብለዋል።

ዘንድሮ የሚከበረው የዓለም መድህን የሆነው የጌታ ልደት በዚያ ክልል የሰላም ጸጋ የሚያፈስ እንዲሆን የክልሉ ማኅበረ ክርስቲያን ጸሎትና አስተንፍሶ ነው። ተስፋ የሆነው የተስፋ ምልክት በክርስቲያኖች እንዲመሰከር ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ትዋልም በበኩላቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ በዓለም የሚታየው ግጭት ጠንቛሽ የጦር መሣሪያ እምራች ኢንዳስትሪዎች መሆናቸውም ጭምር በተለያየ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚናገሩት ቃል ሰላም እንሻለን የሚሉት አገሮች ሰላም እንዲረጋገጥ በተለያየ የሰላም ውይይት መድረክ ተወናያን አገሮች አስመሳይ መሆናቸው የሚያጋልጥ ነው። የሶሪያው ግጭት የኢራቁ ግጭት ለመፍታት ይወያያሉ ዞር ተብሎም ለጦር መሣሪያ አቅርቦት ሲራወጡ ይታያል፣ ሰላም ከጌታ ነው፣ ሰው የሰላም መሣሪያ ብቻ ሆኖ መገኘት ነው የሚጠበቅበት። የዓለም መንግሥታት በአንደኛው እጃቸው ለሰላም ይዘረጋሉ ሌላኛው እጃቸው ለጦር መሣሪያ ንግድ አቅርቦት ያውሉታል፣ ብለው ዘንድሮ በሚከበረው የዓለ ልደት ዋዜማ በፓሪስ በበይሩት በደማስቆ በአለፖ በጠቅላላ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች ባሸባሪያን ጥቃት ለሞት የተዳርጉት ሁሉ እንምደሚዘከሩም ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.