2015-12-17 11:03:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንሲስ የሰባ ዘጠነኛ አመት ልደታቸዉን አከበሩ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንሲስ እ.አ.አ ታህሳስ 17.2015 የሰባ ዘጠነኛ ዓመት ልደታቸዉን አከበሩ።

ከዓለም ዙርያ በሙሉ የእንኳን አደረሳችዉ መልዕክት የደረሳቸዉ ቅዱስ አባትችን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባብይ የተሰበሰቡ ምዕመናን “እንኳን አደረስዎት” (Happy Birthday) የሚለዉን መዝሙር በመዘመር ደስታቸውን ገልፀውላቸዋል።

በበዓሉ ሥነ ስረዓት ላይ የተገኙት ካርዲናል አብሪሊ ካስቴሎ እንደገለፁት “ለብፁዕ አባታችን እዚህ ተገኝተን እንኳን አደረሶዎት ለማለት እና አብረን ለመፀለይ ስለበቃን እግዚአብሔርን እያመሰገንን፣ እግዚአብሔር ቀሪውን እድመያቸውን እንዲባርክላቸውና ይህንን እየተወጡ ያሉትን ከባድ እና አስቸጋሪ የሆነውን የቤተ ክርስትያን ተልዕኮ በአግባቡ በእግዚአብሔር እርዳታ እና በጣም በሚተማመኑባት በእናታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት እየተወጡ በመሆናቸዉ እኛም ደግሞ እያከናወኑ የምገኘውን ታላቅ ተልዕኮ በፀሎት ልናጅበው እና ልናግዛቸው ይገባል” ብለዋል ሲል ሰርጆ ቼንቶፋንቲ ዘግቧል።

በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች እንደ ሚመሰክሩት ከሆነ ብፁዕ አባታችን በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማልጅነት ላይ ከፍተኛ የሆነ መተማመን እንዳላቸው መስክረው፣ ማንኛውንም ዓይነት ሥራ ከማከናዎናቸው በፊት እና ከአከናወኑ ቡኋላ በተለይም ደግሞ ወደ ውጭ ሀገር ለመንፈሳዊ ተልዕኮ ከመሄዳቸው በፊት እና ከተመልሱ ቡኋላም በቅድስት ድንግል ማርያም ፊት ተንበርክከው የምስጋን ፀሎታቸውን እንደሚያደርሱ እና ይህም እውነታ የሚያሳየው በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ላይ ያላቸውን ታላቅ መተማንን ቢቻ ሳይሆን ለሳቸዉ መንፈሳዊ ጥንካረም ቅድስት ድንግል ማርያም ከፍተኛ ቦታ እናዳላት ያሳያል በማለት ገልፀዋል።

በተያያዘም ዜና ቅዱስነታቸው በልደታቸው ቀን እንኳን አደረሶት ለማለት ለተሰበሰቡ ወጣቶች የሚበዙባቸው ምዕመናን እንደገለፁት “እንኳን አደረስዎት” ለማለት ምዕመናን በመሰብሰባቸው፣ ምዕመናን አመስግነው “ትክክለኛ የህይወት ጉዞ ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ ጉዞ ነው” ካሉ ቡኋላ ወደ እግዚአብሔር መጓዝ ማለት ደግሞ አሉ ቅዱስ አባታችን “የክፋትን መንገድ ትተን በመልካም መንገድ ላይ መጓዝ እና የበቀልን መንገድ ትተን በይቅርታ መንገድ ላይ መጓዝ ነው ካሉ ቡኋላ በተጨማሪም የግጭትን መንገድ ትተን የሰላምን መንገድ በመፈለግና እራስ ወዳድነትን በማስወገድ የአንድነትን መንገድ መከተል ይገባናል ሲሉ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

 
All the contents on this site are copyrighted ©.