2015-12-16 16:02:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. 49ኛው የሰላም መልእክት፦ በሰው ልጅ ብቃት ተስፋ ማድረግ


የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 49ኛ ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት ግድ የለሽነትን በማሸነፍ ሰላምን ባለ ድል ማድረግ የሚል ሃሳብ ማእከል ያደረገ መሆኑ የፍትህና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሶን በመሩት ጋዜጣዊ መግለጫ አማካኝነት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በይፋ መቅረቡ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፦ ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን ግድ የለሽነት የተለያየ መልክ እንዳለው በማብራራት ለእግዚአብሔር ግድ አለ መስጠት ለሰው ልጅ ለጎረቤትና ለተፈጥሮ ግድ ላለመስጠት መንስኤ መሆኑ አበክረው፦

በሰው ልጅ ብቃት ላይ ያለ ተስፋ

የሰው ልጅ ደግነት በክፋት ላይ ድል እንዲነሳ የማድረግ ብቃት የታደለ ነው፣ ስለዚህ ከዚህ አኳያ ሲታይ በተለያየ ማኅበረሰብአዊ ሁነት የሚታየውን ግድ የለሽነትን ማሸነፍ የሚቻል መሆኑ አያጠራጥርም፣ በመሆኑም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰላም መልእክት ግድ የለሽነትን ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ አማካኝነት በሰው ልጅ ብቃትና ዓቅም ላይ ተስፋ ማድረግ ያለው አስፈላጊነት ጭምር የሚያበክር ነው። ለግድ የለሽነትና ምንም ነገር ለማድረግ አይቻልም ለሚለው ቀቢጸ ተስፋነት እጅ ካለ መስጠት ከእግዚአብሔር ከባለንጀራና ከተፈጥሮ ጋር ሰላም እንዲኖር በሰላም ግንባታው ሂደት የራስ አስተዋጽኦ ማቅረብ። ይኸንን ተስፋ ለማቀብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመልእክቱ ፍቅር ተቆርቋሪነት መሃሪነት ለዚያ በሰማይ እንዳለው አባታችሁ እናንተም መሃሪያን ሁሉ በማለት ጥሪው ለሚያቀርብልን ጌታ ተገቢ መልስ በመስጠት ተጨባጭ የሕይወታችን ጥረት ማድረግ እንደሚግባን ያሳስባሉ።

ግድ የለሽነት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሥልጣናዊ ትምህርት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ቀዳሜው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በላምፔዱዛ በማድረግ እዛው ግድ የለሽነት ዓለማዊ ትሥሥር ለበስ መሆኑ በማብራራት፣ የሰው ልጅ ከዚህ ዓይነት እግዚአብሔርንና በሰው አማካኝነት ለሚገለጠው ጌታ ግድ ካለ መስጠት ፈተና እንዲላቀቅ ያቀረቡት ጥሪ በ 2015 ዓ.ም. ዓቢይ ጾም ምክንያት አስተላልፈዉት በነበረው መልእክት፣ “እኔ በተመቻቸ ሕይወት የምኖር ሲመስለኝ ባልተደላደለና ባልተመቻቸ ሕይወት የሚኖረውን እዘነጋለሁ” በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ ያስታውሰናል፣ ይኽ ዓይነት ዓለማዊ ትስስር ለበስ እየሆነ በምጣት ላይ ያለው ስግብግብነትና ግድ የለሽነት ለክርስቲያን አቢይ ግርግር የሚፈጥር መሆኑ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የፍትህና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ፍላሚኒያ ጆቫነሊ ገልጠዋል።

ምኅረት በግድ የለሽነት ላይ ድል ይነሣል

ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት አባል ቪቶሪዮ አልበርቲ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ፦ ግድ የለሽነት በምኅረት መታየት አለበት፣ ይኽ ሲባል ደግሞ ፓልሚራ ሲወድም ሙስና በዓለም ደረጃ መስፋፋትና የሚያስከትለው ችግር በማየት ነገሮችን መቀየር አልችልም እየተባለ እጅ ማጣመር መፍትሔ አይሆንም፣ ስለዚህ ሁሉም አቅሙንና ኃይሉን በማስተባበር ነገሮችን መቀየር እንደሚችል ማመንና መታመን አለበት። ምኅረት ግብረ ገባዊ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ያስተሳሰብና የቀልብ ጉዳይ የሚመለከትም ነው። ስለዚህ የሓሳብ ነጻነት የሚመለከት ይሆናል። በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሰላም መልእክታቸው ባህላዊና መንፈሳዊ ግድ የለሽነት ለመዋጋት ብሎም ለማሸነፍ ምን መደረግ እንደሚገባ ቁልፍ የሆነው ሃሳብ ያቀርባሉ ብለዋል።

ምስክርነት

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሰላም መልእክት ላይ በማስደገፍ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በኢጣሊያ ሲቺሊያ ክፍለ ሃገር የሞንሪያለ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሚከለ ፐኒዚ፦ ወንጀለኛ ላይ የሚበየነው ፍርድ ከፍትህ የመነጨና ወንጀል እንዳይፈጸም የሚያንጽ ሰብአዊነት የሚያድስ መሆን አለበት ሲሉ፣ በኢጣሊያ የወጀል ቡድኖች ተግባር የሚያጋልጥ ለሰው ልጅ ህዳሴ የሚታገለው ማኅበር መስራች አባ ልዊጂ ቾቲ በበኩላቸውም ሰላም ሲባል ጽሞና ወይንም በገዛ እራስ ባለው ሰላም ላይ ተረጋግቶ መኖር ማለት አይደለም እውነተኛው ሰላም ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኝ መንፈሳዊ ንቃት ማለት ነው እንዳሉ ሎሞናኮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.