2015-12-16 16:05:00

ሚሥጢረ ተክሊል ማእከል ያደረገ ዓውደ ጥናት በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ


የቤተ ክርስቲያን የሕግ ጠበቃዎች ቀን ምክንያት ለዝክረ ብፁዕ ካርዲናል ኡርባኖ ናቫረተ በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን አማካኝነት ሚስጢረ ተክሊል ርእስ ዙሪያ የሰጡት የኅዳሴ ውሳኔ ማእከል ያደረገ ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

የተካሄደው ዓውደ ጥናት በማስደገፍ በኢጣሊያ ፒዛ ከተማ ለሚገኘው መንበረ ጥበብ መምህርና የአገረ ቫቲካን የጠበቃዎች ማኅበር አባል ፕሮፈሰር ፓውሎ ሞነታ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው የህዳሴ እቅድ መሠረት በሕገ ቀኖና ምስጢረ ተክሊል በሚመለከተውን ዓንቀጽ የቅዱስ ጴጥሮስ የተከታይነት ሥልጣል መሠረት እንዲታከል ያደረጉት እርሱም ብዙ ምእመናን ባሰሩት ምስጢረ ተክሊላዊ ሕይወት በሚያጋጥማቸውና በሚኖሩት አሉታዊ ገጠመኝ ተሸንፈው ቃል ኪዳን አፍርሰው የሚኖሩት ከቤተ ክርስቲያን ጋር ምሉእ ሱታፌ እንዲኖራቸው ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ ነው። በርግጥ የቤተ ክርስቲያን ምስጢረ ተክሊል ይፈታል ለማለት ሳይሆን የተሰራላቸው ምስጢረ ተክሊል ይፈታልኝ በማለት በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ የሚያቀርቡ ምእመናን ፍርድ ለመስጠት ማለትም መልስ ለመስጠት የሚፈጀው የተንዛዛው ረዥም ያሠራር ሂደት እንዲወገድ የሚያደርግ ነው። ስለዚህ በዚህ ርእስ ዙሪያ የሰጡት ውሳኔ የላቲንና የምስራቅ ሥርዓት ለሚከተሉት የካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን የሚመለከት ነው ብለዋል።

እኚህ የቤተ ክርስቲያን ሕገ ቀኖና የምስጢረ ተክሊል የሚመለከትን ዓነቀጽ ኅዳሴ ለሚከታተለው ልዩ ድርገት አባል በመሆን ያገለገሉት የሕግ ሊቅ ፕሮፈሰር ሞነታ ኅዳሴው ይላሉ ወቅታዊው ቤተሰብ የተጋረጠበት ማኅበራዊ ሰብአዊና መንፈሳዊ ችግር ሁሉ ግምት የሰጠ ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን አንድ የታሰረው ምስጢረ ተክሊል ይፈታ ብላ ለምትሰጠው ውሳኔ ያሰራር ሂደት የሚያድስ እንጂ ምስጢረ ተክሊል የአንቀጸ እምነት ክፍል መሆኑ የሚሽር አይደለም፣ ስለዚህ የታሰረ ቃል ኪዳን አይፈታም ብለው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የወሰኑት ምስጢረ ተክሊል የሚመለከተው ሕግ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እግብር ላይ እንደሚውል ገልጠው፣ በዚሁ ርእስ ዙሪያ የሚከናወነው የፍርድ ቤት ችሎት ምስጢረ ተክሊል ይፈታልኝ ባይ እለ ምንም ወጪ ጥያቄው በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት አለ ምንም ክፍያ ጉዳዩ በማጤን ተገቢ ፍርድ ይሰጥበታል፣ ይኽ አሰራር የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የዛሬ 15 ዓመት በፊት ጀምሮ የሚከተለው አሰራር መሆኑ አስታውሰው በዚሁ አንቀጽ ዙሪያ እያንዳንዱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሚኖረው ሥልጣን ጭምር ታድሰዋል፣ በግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የተካሄደው ዓውደ ጥናት በኅዳሴው ዙሪያ የተሰጡት አወንታዊና አሉታዊ አስተያየቶች ጭምር መጤኑ ገልጠው ያም ሆኖ ይኽ ህዳሴው የቤተ ክርስቲያን ባህል በጽናት የሚከተል ህዳሴ በቀጣይነት የሚል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.