2015-12-16 13:35:00

እውነተኛን የቤተክርስትያን ሀብት ድሆች ናቸዉ።


እ.አ.አ በታህሳስ 15.2015 ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ ቤተክርስትያን ባደረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ በስብከተ ወንጌል እንደገለፁት፣ ቤተክርስትያን በእግዚአብሔር ፊት ትሁት፤ ድሃ እና ታማኝ ለትሆን ይገባል ብለዋል። የቤተክርስትያን ብፅዕና ሊለካ የሚገባዉ አሉ ቅዱስ አባታችን በድህነቷ ስሆን ሃብቷ ልሆን የሚገባዉ ደግሞ ድሆች እንጂ ገንዘብ ወይም የዓለም ሥልጣን ሊሆን አይገባም ብለዋል ሲል አሌሳንድሮ ጊዞቲ ዘግቧል። ቤተክርስትያን አሉ ቅዱስ አባታችን ሲቀጥሉም፣ ቤተክርስትያን ትሁት እንጂ በስልጣን የምትመካ መሆን የለባትም።

ትልቁ ጥያቄ፣ አሉ ቅዱስ ርዕሰ ጳጳስ ፍራንሲስ፣ ቤተክርስትያን እንዴት ለጌታ ታማኝ ልትሆን ትችላለች የሚለዉ ነው? ካሉ ቡሃላ ቤተክርስትያን ከእግዚአብሔር የተሰጣትንን አላፊነት ለመወጣት ትሁት፤ ድሃ እና በእግዚአቤር ፀጋ የምትተማመን ሊሆን ይገባል ብለዋል። 

ቤተክርስትያን በምድራዊ ሀይል የምትመካ ሳይሆን በትህትና በትጋት በተለይም ድሆችን  ማገልገል ይጠበቅባታል። ትህትናን መልበስ ልፍስፍስ ወይም ግድ የለሽ መሆን ማለት ሳይሆን ሓጥያተኛ መሆኗን መገንዘብ ማለት ነዉ ብለዋል።

በመቀጠልም ቅዱስ አባታችን “አንድ ሰዉ እራሱን እንደ ፃድቅ የምቆጥር ከሆነና ሌሎችን ደግሞ እንደ ሓጥያተኛ የምመለክት ከሆነ ትሁት አይደለም ማለት ነዉ ካሉ ቡኋላ እኛ ሁል ጊዜ በሌሎች ላይ ስህተትን ቢቻ የመመልከት ልምድ አዳብረን ከሆነ፣ የሌሎች ፈራጅ ሁነን እንቀራልን ማለት ነዉ ሲሉ አደገኛነቱን አስምረዋል።

ቅዱስ አባታችን ሓሳባቸውን ስያጠናክሩም፣ ቤተክርስትያን ሀብቷ ሊሆን የሚገባው ድኾች እንጂ ምድራዊ ሀብት እና ገንዘብ መሆን የለበትም ካሉ ቡኋላ ድኽነት አንዱ የቤተክርስትያን በገለጫ ሊሆን እንደሚገባው በማሳሰብ በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት ቁጥር ሦስት የሚገኘውን “በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው” የሚለዉን በመጥቀስ ቤትክርስትያን ሀብቷ እግዚአብሔር ቢቻ ሊሆን ይገባል ብለዋል። በማከልም ገንዘብ ቢቻ የምታስብ እና ገንዘብን ለምግኘት የምትተጋ ቤተክርስትያን አሉ ቅዱስ አባታችን፤ ክርስቶስ የሚፈልጋት ዓይነት ቤተክርስትያን ሳትሆን ገንዘብን ቢቻ የሚፍልጉ የቤትክርስትያን አገልጋዮች መሰብሰብያ ትሆናለች ማለት ነው በማለት አደገኛነቱን በማስመር፣ ክርስቶስ የሚፈልጋት ቤተክርስትያን ድሀ እና ለድኾች የቆመች ልትሆን ይገባል ብልዋል።

በመጨረስሻም ቅዱስ አባታችን ስያሳስቡ ቤተክርስትያን በማያሳፍራት እግዚአብሔር ላይ እምነቷንና ተስፋዋን በመጣል  በታላቅ ትህትናና ታዝዞ ለተጠራችበት ዓላማ በመቆም፣ ሀብቷን እና ልቧን የክርስቶስ በማድርግ፣ በእግዚአብሔር ፀጋ በመተማመን፣ በተለይም በዚህ የስብከተ ገና ወቅት ጌታ ትሁት እና ድሀ የሆነ ልብ እንድሰጠንና፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በእርሱ የሚተማመን ልብ እንድሰጠን በፍፁም ለማያሳፍረን ጌታ አትብቀን ልንፀልይ ይገባል  ሲሉ ቃለ ወንጌላቸዉን ደምድመዋል። 

 
All the contents on this site are copyrighted ©.