2015-12-14 17:31:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት ፍራንሲስ የቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራን ካተድራል ቅዱስ በር ከፍተዋል


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናንት እዚህ ሮም ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራን ካተድራል ቅዱስ በር ከፍተዋል። ቅድስነታቸው ካተድራሉ ውስጥ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። ኮሶውስት ሺ በላይ ምእመናን ሥርዓተ ቅዳሴ እና የቅዱስ በር የመክፈት ሥነ ሥርዓቱን ተከታትለዋል።

ቅድስነታቸው ቅዱስ በሩን እንደከፈቱ ዓመቱ የምህረት ዓመት እና የእግዚአብሔር ህልውና የምናስብበት ግዜ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ግዜው የምህረት ግዜ እና የምህረት መሳርያ የምንሆንበት ግዜ እንደሆነ አውስተው በዚህ በእግዚአብሔር ፊት እንፈረዳለን ብለው የተወደዳችሁ ምእመናን የእግዚአብሔር በር የፍትሕ በር መሆኑ መዘንጋት አያገባንም ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢአታችን ሁሉ ሰርዞ በመካከላችን ለመኖር ወስነ ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፋራንሲስ ትናንት ሶውስተኛ ሰንብተ ምጽአት እንደሆነ ዘክረው ልደተ እግዚእነ ወ መድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ መቃረቡ የሚያመለክተን ግዜ መሆኑ ስብከታቸውን በማያያዝ አስገንዝበዋል።

ምጽአተ ኢየሱስ ክርስቶስ ልባችንን በደስታ የሚሞላ እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈተጠረውን ፍጥረት ሁሉ እንዲድን የሰራው ሚስጢር መሆኑ አውስተው ልባችን ለእምነት ክፍት መሆን አለበት ብለዋል።

ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ጠቅሰው በችግር እና በስቃይ ግዜ መድኅን አጠገባችን መሆኑ መዘንጋት የለብንም እግዚአብሔር ለፈጠረው ሰው እንደሚንከባከብ መረዳት ያሻል ብለው በዓለም ዙርያ ያሉ ካቶሊካውያን አድባራት የተከፈቱ ቅዱሳን በሮች ለደስታእና ለምህረት የሚጋብዙን ናቸው ብለዋል።

በቅርቡ በቤተ ክርስትያን የተከፍተው ኢዮቤልዩ የምህረት ዓመት የእግዚአብሔር ህልውና እንደገና የምናገኝበት እና የምናረጋግጥበት እንደሆነ ጠቁመው የንቀየርበት ንስሐ የምንገባበት ከከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር የምንታረቅበት ምህረት እንደተቀበልን የሚሰማን ግዜ እንደሆነ አሳስበዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ህዝቡ ምን እናድርግ ብሎ ሲጠይቀው ፍትሔኛ መሆን እና ርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ርዳታ መስጠት ብሎ ያለው አሁንም ወቅታዊ እንደሆነ አመልክተዋል ፓፓ ፍራንሲስ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናንት እሁድ በቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ ካተደራል ቅዱስ በር በከፈቱበት ግዜ እና ያሰሙት ስብከት በማያያዝ ቅዱስ በርን ተሻግረን ቤተ እግዚአብሔር ስንገባ የምህረት መሳርያዎች እንድንሆን እንጠየቃለን የተጠመቀ ሁሉ ያለውን መንፈሳዊ ሐላፊነት መሸከም እንዳለብን አሳስበዋል።

በጌታችን መድኀኖታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሚስጢረ ጥምቀት የተቀበለ ሁሉ የተላበሰው ሚስጢር ዘለዓለማዊ መሆኑ መገንዘብ እንዳለበት እና ከጌታ በጌታ መኖር እንደሚጠበቅበት እንደ ጌታ መሀሪ መሆን እንዳለበት ቅድስነታቸው አስገንዝበዋል።

ቅድስነታቸው በማያያዝ የተወደዳችሁ ህዝበ ክርስትያን የእግዚአብሔር ምህረት መጨረሳ እንደሌለው ምህረቱ እና ጸጋው እንዲሰጠን መጸለይ ማስተንተን እንዳለብን ከሁሉም በላይ ከሱ ጋር መታረቅ እንዳለብን ከቶ መዘንጋት የለብንም በማለት ስብከታቸውን አጠቃልለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.