2015-12-14 09:44:00

የ3ኛዉ የስብከተ ገና ሣምንት ቃለ እግዚአብሔር በአባ ደረጀ በቀለ


የተከበራችሁና የተወደዳችሁ ዉድ የእግዚሃቢሓር ቤተሰቦች

የእግዚአብሔር ጸጋ እና ሰላም ሁል ጊዜ ከናንት ጋር ይሁን አሜን።

የእግዚአብሔር አባታችን በጎ ፊቃድ ሆኖ ያለፈዉን ሳምንት በምሕረቱ እና በቸርነቱ ጠብቆን ይዛረዉን ዕለተሰንበት እኛን ልጆቹን በአንድ ልብና በአንድ ሓሳብ እንድናከብረዉ እና እንድናመልከዉ በስሙ ስለሰበሰብን ለእግዚብሔር አባታችን ከብርና ምሳጋን ይሁን።

የዛሬ ሰንበት መፀጉዕ አስተምሮ ይባላል። የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል የምያተኩረዉ እግዚአብሔር እዉሩን፣ ማየት የተሳነዉን የሚፈዉስ እና የምያድን እዉነትኛ አዳኝ መሆኑን ነዉ። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር የሰዉ ልጅ እርዳታ እና ፈዉስ የምያገኝዉ ከእግዚአብሔር ብቻ ነዉ ይለናል።

“እናንት የሰዉ ልጆች እስከመቼ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? ከንቱን ነገር ለምን ትዎዳላቺዉ? ሓሰትንስ ለምን ትሻላችሁ? እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተገለጠ እወቁ”። ስለዚህ ሰዉ ሰለ ሓጥያቱ፣ ሰለበደሉ፣ ሰለክፋቱ እና ስለደነደነዉ ልቡ የእግዚአብሔር ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ፍፁም አምላክ እና ፍፁም ሰዉ ሆኖ የሰዉን ልጅ ከሓጥያት ለመፈወስ እና አድስ ሕይወት ለምስጠት ወደ መድር መምጣቱን ቅድስት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ታስተምረናለች።

ቅዱስ ዳዊትም በእግዚአብሔር ምህርት እና ቸርነት በመተማመን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እና ወዳጅነትን ስናቋርጥ ንስሓ በመግባት ልባችንን ወደ እግዚአብሔር በማንሳት ሳናቋርጥ ከእግዚአብሔር ጋር በፀሎት መኖር እናዳለብን ያሳስበናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር መሓሪ እና ይቅር ባይ አምላክ ስለሆነ። እግዚአብሔር የሰዉን ችግር፣ ዉጣ ዉረድ፣ መከራዉንና ሰቆቃዉን አይቶ ፍቅር እና ምህረት የሚያድርግለት አምላክ እና አባት ነው። ቅዱስ ጳዉሎስ 1ቆሮ. 2፡1-16 ሲናገር “በእግዚአብሔር በመተማመን የሚገኘዉ እዉቅት እና ጥበብ እግዚአብሔርን ያስደስታል ለሰዉ ልጅም ልዩ ክብርና ህልዉና ያመጣል ይለናል። ስለዚህ ከእግዚአብሔር የሚገኘዉን ጥበብ እና እዉቀት እግዚአብሔርን እና ወንድሞቻችንን ማየት የምያስችል ብርሃን ይሰጠናል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ይለናል። ለዚህም ነዉ ማየት የተሳነዉን የሰዉ ልጅ ብርሃን ለመስጠት ሰዉ ሆኖ የመጣዉ። የሰዉ ልጅ በእየሱስ ብርሃን ታግዞ የበለጠ ማየት እንዲችል እና የበለጠ እግዚአብሔር ልቦናዉን እንድያበራለት እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚለዉን አምላክ መከተል ለህይወቱ ልዩ ፀጋን እና ደስታን ያጎናፅፈዋል፣ ህሊናዉንም በአዲስ መንፈስ ይሞላዋል።ትንቢተ ሕዝቄል በምዕራፍ 36፣26 ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ስያስተምር እና ሲመክራቸዉ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ በአዲስ ሕይወት እንዲኖሩ አዲስ ልብ እሰጣችዋለሁ አዲስ መንፈስም በዉስጣችሁ አኖራለዉ ይላል እና ይህ የእግዚአብሔር የፈዉስ እና የንስሓ ጥሪ መቀበል አስፈላጊ ነዉ። ዛሬም የሰዉ ልጅ የእየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ያስፈልገዋል። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ እዉር ሆኖ የተወለደዉን የፈወሰዉ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እዲገለፅ ፈልጎ ነዉ።

ቅዱስ አጎስጢኖስ የክርስቶስ ብርሃን በእናቱ በቅድስት ሞኒካ ታልቅ እምነት እና ጸሎት አማካይነት እንደበራለትና እንደተገለፀለት፣ ሕይወቱን እንደለወጠ፣ እምነቱ እንደበረታ ይህንን የክርስቶስ ብርሃን ከተለማመደም ቡሀላ አንተ የኔ ፈጣሪ መሆንህን አውቃለዉ ነገር ግን ነፍሴ ባንት እረፍት እስካላገኘች ድረስ እርፍት የለኝም በማለት በእግዚአብሔር ላይ ያለዉን ከፍተኛ መተማመን መስክሯል።

ስለዚህም ዛሬም የሰዉን ልጅ እረፍት የሚነሱት ብዙ ነገሮች በየዕለቱ በሕወቱ ዉስጥ ይከሰታሉ። ለመፈዎስ እና ወደ እግዚአብሔር ምህረት ለመምጣት ወደ እግዚአብሔር ብንሄድ ፣እግዚአብሔር እጆች ዛሬም ተዘርግቶ ይጠብቀናል።

ይህንን ዕለት ሰንበት ስናከብር ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ምሕረት እና ቸርነት የሚለዩንን ብዙ ነገሮች ምንድንናቸዉ ብለን እራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል።ብጽዕት እማሆይ ትሬዛ “ከእግአብሔር መለኮታዊ ፍቅር የሚለየን ሓጥያት ነዉ” ይሉ ነበር። የድሆች እናት የሆኑት እና ብዙ ድሆችን ማገልገል የቻሉት በእግዚአብሔር መለኮታዊ እርዳታ እና ሚስጢራትን በማዘዉተር ነው።

ሁላችንም እንደ ምናዉቀዉ ይህ ዘመን እ.አ.አ. ከታህሳስ 8 2015- ታህሳስ 2016 ድረስ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ቅዱስ ፍራንሲስ “ቅዱስ የምህራት አመት” በመባል ተሰይሟል። ዓላማዉም ሁሉም እግዚብሔር ልጆች የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ምህረት በመተማመን ወደ ንስሓ በመምጣት፣ በአዲስ አስተሳሰብ፣ በአዲስ ሕይዎት እና በአዲስ ልብ ከእግዚአብሕሔር አግኝተዉ በእግዚአብሔር ታልቅ ደስታ፣ እረፍት፣ ሰላም እና በረከት ተሞልተዉ፣ ይህንንም ደስታ ለሌሎች ወንድሞቻቸው እና እህቶቻችዉ ምሕረትን እና ሰላምን መስጠት እንዲችሉ ለማስቻል ጭምር ነዉ።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ “እኔ የሕይዎት እንጄራ ነኝ”፣ በማለቱ ክቡር ሥጋውን እና ክቡር ደሙን በመቀበል ማየት የተሳኑትን መፈዎስ እንድንችል ክርስቶስ ለሁላችንም ፀጋዉን ያብዛልን። አሜን።            
All the contents on this site are copyrighted ©.