2015-12-14 19:27:00

ሊብያን ትኩረት የሰጠ ጉባኤ ሮም ውስጥ ተካሄደዋል


በጣልያን መንግስት በዩኤስ አመሪካ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሐሳቢነት እና ዝግጅት የሊብያን ትኩረት የሰጠ ጉባኤ ሮም ውስጥ ተካሄደዋል። ሊብያ ውስጥ አንድ ትሪፖሊ ውስጥ ሌላው ጦብሩክ ላይ ሁለት መንግስታት እንዳሉ የሚታወስ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸው አጥብበው አንድ ብሔራዊ መንግስት የሚያቆሙበት ጉባኤ እንደተካሄደ የጣልያን መገኛ ብዙኅን አስታውቀዋል።

የትሪፖሊ እና ጦብሩክ ተወካዮች የዓረብ ሀገራት ዲፕሎማቶች በዚሁ ሮም ውስጥ በተካሄደ ጉባኤ ትሳታፊ መሆናቸው መገናኛ ብዙኀኑ አስታውቀዋል።

ሊብያ ውስጥ ብሔራዊ የአንድነት መንግስት እንዲቆም የሚቃወሙ ቡድኖች በዚሁ ጉባኤ መሳተፋቸው በዚሁ ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወኪል ማርቲን ኮብለር አስገንዝበዋል።

የሮሙ ሀገራት አቀፍ ጉባኤ ዳዔሽ የተባለው ራሱ እስላማዊ መንግስት ያወጀው ቡድን የሊብያ ሲርተ ከተማ ሙሉ በሙሉ እንደሚቆጣጠራት እና ሀገሪቱን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት በአስቸኳይ ለመግታት በሚቻልበት ሁኔታ መምከሩም ተገልጠዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.