2015-12-11 14:54:00

የምህረት ዓመት ምክንያት በኢጣሊያ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሓውፆተ ኖልዎ መርኃ ግብር መሸጋገር


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ የሚላኖ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በተገባው ኢዮቤልዩ ቅዱስ የምህረት ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው የሐዋርያዊ መርሃ ግብር መጨናነቅ ምክንያት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ቢሮ የተሰጣቸው መግለጫ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን  እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚላኖ ሊያካሂዱት ታቅዶ የነበረው የሐውፆተ ኖልዎ መርሃ ግብር ወደ 2017 ዓ.ም. መሸጋገሩ በይፋ ማሳወቃቸው የሚላኖ ሰበካ የዜናና ኅትመት ቢሮ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.