2015-12-11 15:04:00

ማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ፦ ሰላም በማነቃቃቱ ረገድ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽዖ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ ያካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት የባንጉይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዲየውዶነ ንዛፓላኢንጋ ቅዱስ አባታችን እንደ መንፈሳዊ ነጋዲ ማእከላዊት አፍሪቃን በመጎብኘት ሁሉንም የአገሪቱ ዜጋ ለሰላም አነቃቅተዋል። ካሁን በኋላ የቀረው የገሪቱ ዜጋ በገዛ አገሩ የሰላም ነጋዲ የመሆን ቁርጥ ፍቃድ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕነታቸው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በማእከላዊት ሪፕበሊክ አፍሪቃ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱት ቀቅት ያስደመጡት ምዕዳን የለገሱት ስብከት ባካሄዱዋቸው ግኑኝነቶች ያስደመጡት ንግግር በጠቅላላ ክንዋኔው ሰላም ማእከል ያደረገና ሁሉም የሰላም መሣሪያ እንዲሆን ያነቃቃ መሆኑ ገልጠው፣ የቅዱስ አባታችን ምዕዳን በመከተልም በአገሪቱ ሊካሄድ በተቃረበው ሕዝባዊ ምርጫ የቀድሞ ርእሰ ብሔር ፍራንሱዋ ቦዚዘ በእጩነት ለምርጫ እንዳይሳተፉ የተላለፈው ውሳኔ በመቃወም ባንጉይ በሚገኘው የምስልምና ሃይማኖ ተከታይ በብዛት በሚኖርበት ፒከይፋይፍ ሰፈር የተቀሰቀሰው ግጭት እዲወገድና ሰላም ለማነቃቃት ወደዚያ ክልል ወጣቶችን በማስከተል መሄዳቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ብፁዕ አቡነ ንዛፓላይንጋ በሙስሊሞች ክልል የሰላም መልእክተኛ

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ብፁዕነታቸው በእግራቸው በዚያ ውጥረት በሚታይበት ሰፈር ከወጣቶች ጋር የሰላም ጉዞ በሚል ስያሜ በመዘዋወር ከሁሉም ነዋሪዎች ጋር በመገናኘት አንተ እኔ የሚለው ለግጭት የሚገፋፋው ለያይ አጥር እንዲፈርስ ሁሉም የሰላም መሣሪያ ሆኖ እንዲገኝ ጥሪ አቅርበዋል። እርስ በእርስ መከባበርና መቀባበል ያለው አስፈላጊነት በመመስከር በተለይ ደግሞ ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ይቀር መባባል መማማር እርቅ ለሰላም ወሳኝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በባንጉይ ለምህረት ዓመት ቅዱስ በር በመክፈት በለገሱት ስብከት ያሰመሩበት ቃል ያስተጋባ የሰላም ጉዞ ነበር እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አማካኝነት የተጸገወው መልካም መንፈስ በአገሪቱ እያስተነፈሰ ነው

ቅዱስ አባታችን ያካሄዱት ጉብኝት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ማኅበረ ክርስቲያንን ብቻ ሳይሆን እንዳውም የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ቅዱስነታቸው ሲጎበኙን እንዴት መታደል ነው በማለት ሰላም እንጂ ጦርነትን አንፈልግም ሲሉ አቅርበዉት በነበረው የሰላም ጥሪ ድምጻቸውን በማስተባበር እያስተጋቡ ነው። የፒከይፋይፍ ሰፈር ነዋሪ ወጣቶች ከወጣት ክርስቲያኖች ወንድሞቻቸው ጋር በመገናኘት ስለ ሰላም እያካሄዱት ያለው ቅስቀሳ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአገሪቱ የለገሱት መንፈስ በሁሉም ዜጋ ልብና በአገሪቱ ጭምር እያስተነፈሰ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.