2015-12-07 16:09:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምዕዳን ለካቶሊክ ኣቢያተ ትምህርት


የካቶሊክ ኣቢያተ ትምህርት ወላጆች ማኅበር ዝክረ 40ኛው ዓመት ምሥረታ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ተቀብለው፦ የካቶሊክ ኣቢያተ ትምህርት ለሁሉም ክፍትና ተማሪዎችን አለ ምንም ርእዮተ ዓለም፣ ንግግር በማሣመርም ሳይሆን በእውነተኛው ሰብአዊና ክርስቲያናዊ መንፈስ ማነጽ ይገባቸዋል። ስለዚህ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ምንም’ኳ የተለያየ ቀውስ ምክንያት አበይት ችግሮች ቢከሰቱም መለያቸው የሚሸጡ እንዳይሆኑ በማለት ማሳሰባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

ካቶሊካዊነት ብዙ ተደማጭነት እንዲኖረው ለማድረግ እንደ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብ ሳይሆን ልዩ የሚያደርገው የሚሰጠው የሕንጸት ብቃትና ጥራት ነው። በመሆኑም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አቢያተ ትምህርት በርእዮተ ዓለም የሚነዳ ሕንጸት የሚቃወሙ ናቸው ያሉት ቅዱስ አባታችን፦

የተማሪዎች ወላጆች ልጆቻቸው በካቶሊክ አቢያተ ትምህርት እንዲታነጹ የሚወስዱት ውሳኔ ቀዳሚውና የማይካደውን የኅሊና ነጻነታቸውን በመጠቀም ነው። በመሆኑም ማንም የማይነጥል ሕንጸት ማነቃቃት በቤተሰብና በትምህርት ቤት፣ በትምህርት ቤትና በክልል በትምህርት ቤትና በብሔረ ተቋማት መካከል አገናንኝ ድልድይ ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል። በአሁኑ ወቅት የሕንጸት ውል  ላደጋ ከመጋለጡም አልፎ ተጥሰዋል፣ ስለዚህ ዳግም መልሶ ክብሩን ለማጎናጸፍ የሁሉም ተሳትፎ ያስፈልጋል፣ ይኽ ርብርቦሽ መከፋፈል በማስወገድ ጥዑም ውህደት እንዲኖር የሚያደርግ መሆን ይገባዋል፣ ማለትም ለምርጦች ብቻ የሚል ከፋፋይና ነጣይ አመክንዮ ማግለል ግድ ይሆናል እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

ካቶሊካዊ መምህር የሚለው ቅጽል ስም አደራ እንደ ተራ ነገር እንዳይታሰብ፣ ከሌላው ለየት የሚያደርግ ቅጽል ስም ነው። በመሆኑም ጌታ እምለምነው ይኸንን መለያ በሚገባ እንዲከበር ነው። ያለው ልዩነት አጣጥሞ መምራትና ማስተዳደር፣ ይኽ ደግሞ ለካቶሊክ አቢያተ ትምህርት አቢይ ተግዳሮት ነው። ስለዚህ የዓለም ሳይኰን ነገር ግን በዓለም በመኖር እርሾ ሆኖ መገኘት ያስፍልጋል ያሉት ቅዱስ አባታችን በማያያዝ፦

ሰውን ማእከል ማድረግ እንጂ ንግግር ለማሳመር አለ መጠጣር

ስለዚህ የሚለያችሁ እምነታቸሁ ብቻ ሳይሆን ያላችሁ ጥራት ጭምር መሆን አለበት፣ ይኽ ደግሞ ሰውን ማእከል ማድረግ እንጂ ንግግር ማሳመር መሆን የለበትም፣ በተግባር የሚኖር ክብር ማስተላለፍ ማለት ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።

ሰብአዊና ክርስቲያናዊ እሴቶች አለ ማዋዋል

ብዙ የካቶሊክ አቢያተ ትምህርት በተለያየ ችግር ምክንያት የሚዘጉ እንዳሉ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን፣ ብዛት ላይ ማተኰር ሳይሆን ጥራት ላይ ማነጣጠርም ያስፈልጋል ብለው ሰብአዊና ክርስቲያናዊ እሴቶች በቃልና በተግባር የሚመሰከርባቸው ከሆነ የሚያጋጥም ማንናው ዓይነት ተግዳሮት ሁሉ ይሸገራል በማለት የሰጡት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
All the contents on this site are copyrighted ©.