2015-12-07 16:12:00

ኢዮቤልዩ የምህረት ቅዱስ ዓመት


የምህረት ቅዱስ ዓመት መንፈሳዊ ሓሳብ የመጨረሻ የሆኑትን ማገልገል፣ ድኾች የተናቁት የተረሱት የተነጠሉትን በከፋ ድኽነት የሚገኙትንን ኅሙማን፣ ወላጅ አልባ የሆኑትን መበለቶችን አረጋውያንን ማገልገል የሚል መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ምክትል አስተዳዳሪ አንጀሎ ሸልዞ ኢዮቤልዮ፣ ምሕረት ቅዱስ ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሐፍ በይፋ ለንባብ በበቃበት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ኢዮቤልዮ፣ ምሕረት ቅዱስ ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሚል ርእስ ሥር የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ምክትል አስተዳዳሪ አንጀሎ ሸልዞ የደረሱት መጽሓፍ በይፋ ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የተገኙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን፦ በዚህ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን ወደ ከተሞቻችንና  በህልውና ጥጋ ጥግ ወደ ሚገኙት እንድትል የሚያሳስብ ጥሪ የሚያመለክት መሆኑ ባስደመጡት ንግግር ገልጠው፣ የማንም ሃይማኖት ተከታይ የማያገል ቅዱስ ዓመት ነው እንዳሉ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ስለዚህ ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራ የሰላም ጎዳና የሚገነቡበት በመተባበር በዓለም የሚታየው ሽበራ ቂም በቀል ሌላውን የማግለል ወጋኝነትን የመሳሰሉት በሃይማኖት ስም ሳይቀር የሚከሰቱት ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሁሉ እንዲቀረፍ በጋራ መጠመድ ያለው አስፈላጊነት የሚያሳስብ ቅዱስ ዓመት መሆኑ ሲያብራሩ፣ በመቀጠልም በዓውደ ጉባኤው የተገኙት ለሮማ ክፍለ ሃገር የመንግሥት ምሰሊየነ ፍራንኮ ጋብሪኤሊ ቅዱስ ዓመት ለሮማ ከተማ ችግር የሚፈጥር ሳይሆን እድል ነው። የነጋድያና የቅዱሳት ሥፍራዎች ሁሉ ጸጥታና ደህንነት በሚገባ ዋስትና ለማሰጠት ብቃት ያለው ቅድመ ዝግጅት መከናወኑ ሲያብራሩ። የመጽሓፉ ደራሲ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ምክትል አስተዳዳሪ አንጀሎ ሸልዞ በበኩላቸውም፦ የሁሉም ሰው ልጅ የመብትና የክብር እኩልነት የሚያበክር ለተናቁትና በከፋ ሰብአዊና ቁሳዊ ድኽነት ሥር ለሚገኙት ሁሉ ማገልገል፣ ከገዛ እራስ ወጥቶ ከሌላ ጋር ለመገናኘት ያለው አስፈላጊነት የሚያሳስብ ሁሉም ለዚህ ቅዱስ ተግባር የሚያነቃቃ ቅዱስ ዓመት ነው ብለው የደረሱት መጽሓፍ የምሕረት ዓመት በሚገባ ለመከታተል የሚያግዝ የመመሪያ መጽሓፍ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
All the contents on this site are copyrighted ©.