2015-12-02 15:50:00

ፍራንቸስኮ ሰይሙኝ


በታኦድወፊልም የተቀረጸው በመዱሳ የፊል አሰራጭ ድርጅት ለትሪኢት የሚቀርበው ፍራንቸስኮ ሰይሙኝ በሚል ርእስ ሥር የተደረሰውና የተቀረጸው ፊልም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ለቀዳሜ ትርኢት እንደቀረበ ጳጳሳዊ የምጽዋት ጉዳይ የሚከታተል ቢሮ ካሰራጭው መግለጫ ለመርዳት ሲቻል፣ ፊልሙ እ.ኤ.አ. ከታህሳ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለያዩ ሲነማ ቤቶች ለትርኢት እንደሚቀርብ ያመለክታል።

በፊልሙ ቅድመ ትርኢት ፊተኞች ድኾችና መጠለያ የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች

ጳጳሳዊ የምጽዋት ጉዳይ የሚከታተለው ሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤት ባስራጨው መግለጫ እንዳመለከተውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊልሙ ቅዳሜ ትርኢት ቀዳሚ ታዳሚዎች ድኾችና መጠለያ አልባ የሆኑት የጎዳና ተዳዳሪዎች ስደተኞች ተፈናቃዮችና ስለ እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል የሚጣብቁትና እነርሱን በማገልገል ተልእኮ የሚጠመዱት የበጎ ፈቃድ ማኅበራት የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ዕለት በዕለት በግብረ ሰናይ ተልእኮ የሚያገለግሉት እንዲሆኑ በማለት የሰውጡት ውሳኔ መሠረት 7 ሺሕ ቲኬት ለተሳተፉት ድኾችና መጠለያ አልባ አነርሱን በግብረ ሠናይ ተልእኮ ለሚያገለግሉት ሁሉ መልካም ፈቃድ ባላቸው ሰዎች ግዥ መታደሉና አነዚህ በጎ አድራጊዎች መልካም ፈቃድ መሠረትም የእራት መዓድ መቅረቡ ሲታወቅ፣ ጳጳሳዊ የስዊዘርላድ ጸጥታ ኃይል የሙዚቃ ቡድን ለተጋባእያኑ ጥዑም የመሣሪያ ሙዚቃ ያስደመጡ ሲሆን፣ በእራት ማዕድ ግብዣም የፊልሙ ደራሲና ቀራጭ ዳኔለ ሉከቲ እንዲሁም በተደረሰው ፊልም ተወናያን በመሆን ያገለገሉት ከሁሉም ጋር በመተዋወቅ ሰላምታ እንድቀረቡና በመጨረሻም ለሁሉም በአዳራሹ ለተገኙት የእኛ ቢጤዎች መልካም ፈቃድ ባላቸው ሰዎች የተለገሰ ገጸ በረክትም መታደሉ ጳጳሳዊ የምጽዋት ጉዳይ ተንከባካቢ ጽ/ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.