2015-12-02 15:46:00

ቅዱስ አባታችን በኡጋንዳ ለውፉይ ሕይወት አባላትና ውሉደ ክህነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኡጋንዳ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ዑደት እ.ኤ.አ. ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም. የውፉይ ሕይወት የውሉደ ክህነት አባላትና ገዳማውያን እንዲሁም የዘረአ ክህነት ተማሪዎችን ካምፓላ በሚገኘው ካቴድራል ተቀብለው ለውፉይ ሕይወት ኣባላት በታማኝነት መጽናት ማለት አለ ምንም ድብብቆሽና ካለ ምንም አስመሳይ መንትያ ሕይወት አለ መኖር ለገዛ እራስ ኃጢአትም ምህረት መለመን ማለት ነው በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ ገልጠዋል።

ለሰማእታት ተዘክሮ ታማኝ መሆን

ተዘክሮና ምስክርነት በታማኝነትና በጸሎት። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በለገሱት ምዕዳን እነዚህን ሦስት የጥሪ ኃላፊነት ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች ለውሉደ ክህነት ለውፉይ ሕይወት አባላት በማብራራት ኡጋንዳ የአፍሪቃ እንቁ በማለት ገልጠው በደም ሰማዕነት የከፍሉት የቅዱሳን እምነት ላይ በማተኰር የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን የሰምዕታቱ ተዘክሮ የእነዚህ ስለ ኢየሱስ ፍቅር ሕይወታቸውን የሰዉ ታሪክ የሩቅ ተዘክሮ አድርጋ ልታስብ አይገባትም፣ የዝክረ ሰማዕታት ጸጋ እንለምን። የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ተዘክሮ ታማኝ ለመሆን በዝክረ ሰማዕታት ብቃትና ትርፍ መኖር ሳይሆን ምስክር ሆኖ መገኘት አለባት እንዳሉ አኵይላኒ አመለከቱ።

የካህናት እጥረት ወዳለባቸው ሰበካዎች ካህናት መላክ

የቅስት ማሪያም ካቴድራል እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛና እ.ኤ.አ. በ 1993 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መጎብኘቱ ያስታወሱት ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ በዚያ ካቴድራል የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ሊቀ ጳጳሳት የብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ኪዋንካ አጽም ያረፈበት መህኑም ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን የተዘክሮ መስካሪያን እንጂ አክባሪያን ብቻ እንሁን ብለው፣ የቅዱሳኑ ሱታፌ በመከትል ምስክርነቱ ለጥሪ ጸጋ ታማኝ በሐዋርያዊ ቀናተኛንነት እንዲገለጥ አደራ፣ ታማኝነት ማለት የካህናት እጥረት ወዳለበት ሰበካ ለማገልገል እሺ በሚል መንፈስ ለብፁዕ አቡን መታዘዝ ማለት ነው በርግጥ ቀላል አይደለም፣ ሆኖም ወንጌላዊ ጥሪ ነው እንዳሉ ገልጠዋል።

ኡጋንዳ የአፍሪቃ እንቁ

የካምፓላ ሰበካ በካህናት ጥሪ እጅግ ሃብታም ነው፣ ስለዚህ የካህናት እጥረት ወዳለበት ሰበካ በመላክ ማገልገል ለክህነት ጥሪ ታማኝ መሆንን እንዲመስክሩ አደራ። ለድኾች ለታመሙት ለተናቁት ታማኝ መሆን፣ ምክንያቱም በእነርሱ ክርስቶስ ህያው ነውና፣ የክህነት ጸጋ በአዲስ የተልእኮ መንፈስ በአዲስ ምስክርነት አዲሱን ተግዳሮት መግጠም ያስፈልጋል፣ ካልሆነ ያንን ጸጋ ማጥፋት ይሆናል። በቤተ መዘክር የሚኖር ይሆናል እንዳሉ አኵይላኒ አስታወቁ።

መንትያ አስመሳይ ሕይወት አለ መኖር፣ ካለ መታከት ምህረት መለመን፣

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወደ ካቴድራሉ ገብተው ለክብራቸው ለካምፓላ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት የካህናትና የውፉይ ሕይወት ሕንጸት ጉዳይ አለቃ ብፁዕ አቡነ ጆን ባፕቲስት ካግዋ ያስደመጡት የእንኳን ደህና መጡ መልእክትና እንዲሁም የአንዲት ድንግልና የአንድ የውፉይ ሕይወት አባል ምስክርነት መደመጡና ያስታወሱት ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ የካምፓላ ሰበካ 1,500 ካህናት እንዳሉትና 7 ሺሕ የሚገመቱ የተለያዩ የኡጋንዳ የውፉይ ሕይወት አባላት በህክምና በሕንጸት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማህበራዊ ጉዳይ ተሰማርተው በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ብፁዕ አቡነ ካግዋ የገለጡት ሃሳብ ቅዱስ አባታችን ጠቅሰው፣ ይኸንን ሃብት ለቅድስና አውሉት፣ በዚህ የምጽአትና የምህረት ቅዱስ ዓመት ዋዜማ በዚህ የውፉይ ሕይወት ዓመት ጸላያን ሁኑ፣ ብዙ ሥራ ሳላለብኝ በሚል ምክንያት ጥቂት ጸሎት ወይንም አለ መጸለይ የሚኖር ካህን ሊኖር  አይገባም፣ የሚኖር ካለ የኡጋንዳ ሰማእታት ተዘክሮና ታማኝነትን የዘነጋ ማለት ነው እንዳሉ አኵይላኒ አስታወቁ።

ጸሎት ማለት ትህትና ማለት ነው፣ አግባብ ባለው መንገድ በሚሥጢረ ንስኃ መሳትፍ ትህትና ነው፣ በሁለት እግር ማነከስ አይቻልም፣ አንድ ካህን አንዲት ድንግል መንትያ ሕይወት መኖር አይችልም አትችልም፣ ኃጢአተኛ ከሆንክ ምህረትን ለምን ኃጢአተኛ ከሆንሽ ምህረት ለምኚ። ጥሪ የወለም ዘለም ሕይወት አይደለም፣ እግዚአብሔር የማይፈልገው ሕይወት ደብቃችሁ አትኑሩ፣ ያለ መታመን ታማኝነትን ማጉደልም ደብቃችሁ አትኑሩ፣ ተዘክሮ በቁም ሳጥን ውስጥ አትዝጉ ያሉት ቅዱስ አባታችን የለገሱት ምዕዳን ሰላም የተጠሙት አገሮችና ሕዝቦች ቡሩንዲን ጠውሰው እግዚአብሔር በመሪዎችና በመንግስታት በሕዝቦች ልብ ውስጥ የሰላም ፍላጎት የመተባበርና የውይይት የእርቅ ፍላጎት ያሳድር በማለት ማጠቃለላቸው አኵይላኒ ገለጡ።
All the contents on this site are copyrighted ©.