2015-11-30 16:07:00

ቅዱስ አባታችን፦ ድኾችን አትርሱ፣ በሚሰቃዩት ውስጥ ክርስቶስ ህያው ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከኡጋንዳ ወጣቶች ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት አጠናቀው በናልኮሎንጎ ወደ ሚገኘው እ.ኤ.አ. በ 1978 ዓ.ም. በካርዲናል ንሱቡጋ ወደ ተመሠረተው በደጉ ሳምራዊው እረኝ ደናግል ማሕበር ሥር ወደ ሚተዳደረው የግብረ ሠናይ ማእከል በመሄድ በለገሱት ምዕዳን፦ የጌታ ህላዌ የሚደመጥበት የሚነካበት ቤት ነው። ኢየሱስ በታመሙት በድኾች በተናቁት በታሰሩት ተስፋ በቆረጡት ውስጥ መሆኑ ካለ ምንም ጥርጥር ገልጦልናል፣ አደራ ድኾችን አንርሳ። አፍሪቃ ድኾችን አትርሳ።

ወንጌል ወደ የከተሞቻችንና ወደ የሕልውና ጥጋ ጥግ ክልል እንድንል ግድ ይለናል፣ አማራጭ አይደለም፣ ድኾችን ወጣቶችን አረጋውያንን መዘጋት የሚያስከትለው ፍርድ ጌታ ግልጥ አድርጎ ነግሮናል፣ በአለማችን ግለኝነት ለእኔ ባይነት ስግብግነት እየተስፋፋ ነው፣ ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የዚህ አሉታዊ ባህል ሰለባዎች ናቸው፣ ክርስትያን እንደ መሆናችን መጠን ይኸንን ጉዳይ ዝም ብለን መመልከት ሳይሆን በዚህ አሉታዊ ባህል በሚታይበት ዓለም የእግዚአብሔር ታጋሹና የመሃሪው ፍቅር ምልከት ሆኖ መገኘት ይጠበቅብናል፣ ሊገለገል ሳይሆን ሊያገለግል ለመጣው ጌታ ምስክር እንሁን፣ ሰዎች ከነገሮች በላይ መሆናቸው እንመስክር፣ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የምናደርገው መልካም ነገር ሁሉ ለጌታ እንዳደረግነውም የተረጋገጠ ነው ቃሉም የኢየሱስ ቃል ነው።

ወዳጆቼ ተራ በሆነው ተግባር አምላኪያን መሆናችን በሚገልጠው ኢየሱስን በሚያከብር ምልክትና ተግባር ወደ ዓለም ፍቅር እንዲገባ እናድርግ ይኽ የፍቅር ኃይል ዓለም የሚለውጥ ኃይል ነው ብለው የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.