2015-11-30 15:56:00

ቅዱስ አባታችን ለኡጋንዳ ትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ የኡጋንዳው ሐዋርያዊ ዑደታቸው መርሃ ግብር መሠረት በካምፓላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሰፕሪኣን ኪሲቶ ልዋንጋ የእንኳን ደሃን መጡ መልእክት ከተደመጠ በኋላ በሙንዮንዮ የአንድ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የመሠረት ድጋይ ባርከው ካኖሩ በኋል ከሁሉም የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መንፍሳውያን መሪዎች ጋር በመሆን እዛው ለሰላም ትእምርት በጋራ ዛፍ ተክለው ውሃም በማርከፍከፍ የተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት ያለው አስፈላጊነት መስክረው፣ የሙንዮንዮ ሰበካ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎችና የሕንጸት አስተማሪዎችን ተቀብለው፦ ቀዳሚውና አቢይ መምህር ኢየሱስ ክርቶስ  መሆኑ በማሳሰብ፣ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ተልእኮ ያለው አስፈላጊነት ገልጠው፣ ከብፁዓን ጳጳሳት ከካህናት ከዲያቆናት እርሱም ወንጌል እንዲያበስሩ የማዕርግ ምሥጢር ከተቀበሉት ጋር በመተባበር የእግዚአብሔር መንጋ ለመንከባከብ የጠሩ መሆናቸው እንዳብራሩ  የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቱ ገልጠው፣ አዲስ ዜና ወደ ሁሉ የአገራችሁ መንደሮችና መኖሪያ ቤቶች የማበሰሩ ጥሪ የተቀበላችሁ ናችሁ፣ ይኽ ደግሞ በጽናትና በውፉይነት ተግባር ቤተሰቦችና ወላጆች ልጆቻቸውን በእምነት እንዲያሳድጉ ቃልና ሕይወት በተካነው ምስክርነት ወንጌል በማበሰር በተለያየ ዘርፍ ለሕዝበ እግዚአብሔር ቅርብ በመሆን በአገራችሁ መሬት የእምነት ዘር የምትዘሩና የምትኮተኩቱ ናችሁ፣ ለሕፃናትና ለወጣቶች ጸሎት የምታስተምሩ ናችሁ።

ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት ለትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች በቤተ ክርስቲያን የአንቀጸ ትምህርት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና በመንፈሳዊነት ጎዳና ሕንጸት በማቅረብ ረገድ በመደገፍና በማነጽ እንዳይለዩዋቸው ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን፣ በቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ያለው ሐሴት አካፍሉ ብለው ዮሓንስ ወንጌል ምዕ. 1 ቁ. 5. ብርሃን በጨለማ ያበራል ጨለማም ብርሃንን ከቶ አያሸንፈውም የሚለውን ቃል ጠቅሰው ሙንዮንዮ በዚያ ክልል የነበረው ንጉሥ የክርስቶስ ተከታዮችን ለሞት የዳረገበት የኡጋንዳ ሰማዕታት ያፈሰሱት ደም ቦግ ብሎ የሚያበራበት ስፍራ መሆኑ ገልጠው፣ የእነርሱ የእምነት ጽናት በክርስቶስ በተገባው የተስፋ ቃል ላይ ያላቸው እማኔ የሚያረጋግጥ ነው ብለው በስዋሂሊኛ ቋንቋ ኦሚካማ አባወ ኦሙኪሳ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ብለው ቡራኬ ሰጥተው የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ መኒከቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.