2015-11-27 15:47:00

ቅዱስ አባታችን ከወጣቶች ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት ያስደመጡት ቃል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ናይሮቢ በሚገኘው ካሳራኒ የስፖርት ሜዳ ልክ በናይሮቢ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 ሰዓት ደርሰው እዛው ለተገኙት ወጣቶች ሁሉ በሜዳው በመዘዋወር ሰላምታን አቅርበው መዝሙሮችና በኅብረ ቀለም ያሸበረቀ ሽብሸባ ቀርቦ እንዳበቃም አንዲት ዓይነ ስውር ከሁለተኛው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ጢሞተዎስ ከጻፈው መልእክት ምዕ. 1 ከቁ. 3 እስከ 10 ያለው ተነቦ መዝሙር ቀርቦ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የዓለማውያን ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር በብፁዕ አንቶንይ ሙሀሪያ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ከተደመጠ በኋላ ከተለያዩ ወጣቶች የምስክርነት ቃል ቀርቦ እንዳበቃም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በለገሱት ምዕዳን፦

ኢየሱስን መቀበል በእምነት መጽናት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወጣቶቹ ላቀረቡላቸው የእንኳን ደህማ መጡ የመዝሙርና የኅብረ ቀለማዊ ባህላዊ ሽብሸባና ይኽ ሁሉ የቤተኛ መንፈስ እንዳሳደረላቸው በመግለጥ አመስግነው ይኽ ዓይነት የሞቀ አቀባበል ለእኔ ብቻ እንዳይሆን አደራ ለዚያ በእርሱ ስም እዚህ ለመጣሁት ለኢየሱስ ክርስቶስ ግለጡት፣ ምክንያቱም  አለ ምንም ፍርሃት በደስታና በሙላት እያንዳንዳችን እንደ የእግዚአብሐር ፈቃድ ለመኖር በሚያበቃን እምነት ለመጽናት ነው እዚህ የተገናኘነው፣ ስለዚህ ኢየሱስን ተቀበሉ ብለዋል።

በርግጥ ስለ ሕይወትና ስለ እምነት ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ አነጋገር መግለጥ የሚያዳግት ሊሆን ይችላል ምክንያቱም የቃል ምስክርነት ብቻ ሊሆን ስለሚችልም ነው፣ ስለዚህ በቅንነትና ያ የሆነውን እርሱም ክርስትያን መሆናችን ሌሎች እንዲያስተውሉት በሚያደርግ ተግባር የምንሰጠው ምስክርነት ወሳኝ ነው። ሌሎች ማንነታችን ያውቃሉ በመካከላችን ያለው ወዳጅነትም ይጸናል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ሐሴት የተሰየመው ዓዋዲ መልእክት ቁጥር ሦስት ጠቅሰው ብዙውን ጊዜ በዕለታዊ ኑሮ መዋከብ ያለ ቢሆንም እምነትን የምንዘነጋ እግዚአብሔር ራቅ ብሎ ተቀምጦ ይጠብቀናል በሚያስብል ሕይወት እንድንመራ ካደረገን፣ የሕይወት ጥዑም ወሳኝ የሆነው ነጥብ እርሱም መሪ መንገድ የሆነው ሳናስተውል እንድቀር ያደርገናል።

ዕለት በዕለት ኢየሱስን ማፍቀርና በእርሱ መታመን ይገባናል፣ ቅዱስ  አባታችን አንድ ጥበበኛ ካህን (እ.ኤአ. ከ1965 እስከ 1983 ዓ.ም. የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ በመሆን ያገለገሉት) አባ ፐድሮ አሩፐ ባንድ ወቅት እግዚአብሔር ከማግኘት እርሱን አለ ምንም ገደብ  በፍጹምነትና በወሳኝነት ከማፍቀር የበለጠ ምንም ነገር የለም በማለት የተናገሩት ቃል አስታውሰው፣ ኢየሱስ የመጀመሪያ የሕይወታችሁ ፍቅር እንዲሆን ፍቀዱለት።

ቤተ ክርስቲያንና ቤተሰብ

ወጣቶች በጉዞአቸው ለብቻቸው አይደሉም፣ ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳት ምስጢራት ኃይል አማካኝነት ከጎናቸው ነች፣ አብራ ከእናንተ ጋር ትጓዛለች፣ ከቤተሰብ ከካህናት ከገዳማውያን ከውፉይ ሕይወት አባላት ከትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ከቆሞሶች ዕለት በዕለት ዕለታዊ ኑሮ ከሚያቀርበው ተግዳሮት ሁሉ በእምነት የተካነ ሕይወት በቃልና በተግባር በሚሰጡት ምስክርነት እማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ከጎናችሁ ነች።

እውነት ነው ቁምስናዎችና ቤተሰቦች ፍጹማን አይደሉም ይኽ ደግሞ ዕለታዊ መለወጥ ይቅር መባባል ትእግሥት እርስ በእርስ መደጋገፍ ያለው አስፈላጊነት ያስገነዝበናል።

ተጨባጭ ጥያቄ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስደመጡት ምዕዳን፦ ከዚህ ከተሰበሰብንበት ሥፍራ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ቁርጥ ፈቃድ በማድረግ እንውጣ፣ ያ የእምነት ጸጋ ያደለን ሊገናኘን ይመጣል፣ በፍቅርና ለወንጌል በታማኝነት ስትኖሩ ለኬንያ ኅብረተሰብ የተስፋ ነጸብራቅ ትሆናላችሁ።

የኬንያ አቢይ ሃብት ሕዝብ ጥበብ የሚያቅቡ በእድሜ የገፉት ዜጎች የመጻኢ ነቢይ የሆኑት ወጣቶች ናቸው። በማለት የለገሱት ምዕዳን አጠቃለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ቲዚያና ካምፒዚ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.