2015-11-25 16:19:00

የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሰላምን በመማጠን ለቅዱስ አባታችን እንኳን ደህን መጡ ይላሉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከህዳር 25 ቀን እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በኬንያ ኡጋንዳና ማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ የሚይካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ምክንያት የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በጋና ርእሰ ከተማ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እ.ኤ.አ. ከ ህዳር 16 ቀን እስከ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባኤ አማካኝነት ሰላምን በመማጠን ቅዱስ አባታችንን እንኳን ደህና መጡ ብለዋል።

የመላ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጠሩት ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ፍጻሜ ጥቂት ሳምታት በኋላ በአፍሪቃ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ዑደት በመሆኑም አስታውሰው ይኽ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የአፍሪቃ ቤተሰብ በእምነት የሚያጸና በአፍሪቃ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በቤተሰብ መንፈስ የምትመራ በመሆንዋ ቤተሰብአዊነቷን እንዲያጸኑ ብሎም በአፍሪቃ ያለው አፍሪቃዊና ክርስቲያናዊ እሴት እንደሚያበረታቱ ያላቸው እምነት እንደገለጡም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

አሸባሪነትና ጦርነትን መቃወም

የአፍሪቃ ብፁዓን አበው በቅርቡ በፈረንሳይ እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች አሸባሪያን የጣሉት ጥቃት በማስታወስ ማንኛውም ዓይነት ሽበራ፣ አሸባሪነትና የሽበራ ጥቃት የሚፈጽሙትን ሁሉ እንዳወገዙ የገለጠው ሚስና የዜና አገልግሎት አክሎ፣ በአፍሪቃ ሰላም እንዲረጋገጥ ጥሪ በማቅረብም በአፍሪቃና በዓለም በተለይ ደግሞ በብሩንዲ በደቡብ ሱዳን በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ በደሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጐ በናይጀሪያ በከንያና በሊቢያ ባጠቃላይ በመላ አፍሪቃ ሰላም እንዲረጋገጥ  ከሚጥሩ እርቅና መቀራረብ እውን እንዲሆን ከሚያገለግሉ ጎን መሆናቸውም በማረጋገጥ፣ በእግዚአብሔር ስም ጦርነትና አመጽ እንዲገታና ሁሉም ለሁሉም ብልጽግ የሚያጎናጽፈው የውይይትና የሰላም መንገድ እንዲሻም መማጠናቸው አስታወቀ።

ከእግዚአብሔር ምሕረት ጋር ለመገናኘት ሰላምና እርቅ

በመጨረሻም የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ያወጁት የመላ የአፍሪቃ አገሮች እ.ኤ.አ. ከባለፈው ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ የተገባው የአፍሪቃ የእርቅ ዓመት በማስታወስም፣ ሰላምና እርቅ ለእግዚአብሔር ምሕረት መሠረት መሆናቸው በቅርቡ በይፋ የሚጀመረው የምህረት ዓመት ጋር በማያያዝ ገልጠው ሁሉም እርስ በእርስ በመታረቅና ይቅር በመባባል ከእግዚአብሔር ጋር ምህረቱን በመለመን እንዲታረቅ ጥሪ እንዳቀረቡም ሚስና የዜና አገልግሎት ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.