2015-11-16 16:19:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለፈረንሳይ ስቃይ ቅርበታቸውንና ጸሎታቸውን አረጋገጡ


እ.ኤ.አ. ሕዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም. 128 ሰዎች ለሞት የዳረገው ሌሎች 250 ለመቁሰል አደጋ ያጋልጠው ገዛ እራሱ እስላማዊ አገር ብሎ የሰየመው የምስልምና ሃይማኖት አክራሪው የሽበራ ኃይል ጠንሳሽነቱን የተበቀለው አሰቃቂው የአሸባሪያን ጥቃት የመላ ዓለም ሕዝብ ልብ በሐዘን የነካው ሁነት በማስመለከት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓርሊን ፊርማ የተኖረበት ለአገረ ፈረንሳይ ለፈረንሳይ መንግስትና ሕዝብ በፈረንሳይ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በኩል ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የቴለግራም መልእክት፣ ያንን ቀደም በማድረግ በቅድስት መንበር በኩል የገለጡት ይፋዊ የሐዘን መግለጫ መልእክት በማስተጋባት፣ አመጽ ፈጽሞ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፣ ፋይዳ የለውም በማለት የተጣለውን ጥቃት አሰቂቂ ተግባር ብለው በመግለጥ፣ ለመላ ሰው ዘር ሰላም በመመኘት የማጽናኛ ቃል ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቲቪ2000 ለተሰየመው የቴሊቪዥን ጣቢያ ዋና አስተዳዳሪ በስልክ ያስተላልፉት በስርጭቱ በኩል በቀጥታ የተላለፈው መልእክት፦ በእውነቱ እጅግ ልቤን በኃዘን ሞልቶታል፣ ለመረዳቱ የሚያዳግት አሰቃቂ ተግባር፣ የዚህ አይነቱ አሰቃቂው ተግባር በሰው ልጅ የተፈጸመ ነው ብሎ ለመረዳቱም ያዳግታል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አያይዞ፦

እየተገማመሰ የሚፈጸም ሦስተኛው የዓለም ጦርነት

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት የቴልግራም መልክትና በስልክ ጭምር ባስተላለፉት ቃል ያጎሉት የጥልቅ ሃዘን መንፈስና ምሬት፣ የዚያ በፈረንሳይ ያለውና ከፈረንሳይ ውጭ ጭምር እየተኖረ ያለው የመላ ብሔር መንፈስ የሚያንጸባርቅ ነው። በሰው ልጅ የሚፈጽመው አሰቃቂ የቅትለት ተግባር ከሕይወት ወደ ሞት የሚወስድ በተለያየ የዓለማችን ክልል የሚታየው ግጭትና ውጥረት እየተገማመሰ የሚፈጸም ሥስተኛው የዓለም ጥርነት በማለት ብዙውን ጊዜ ደጋግመው የገለጡት ሃሳብ ዳግም በማስተጋባት፣ ምንም ዓይነት ምክንያት የማይገኝለት በእውነቱ በሰው ልጅ የተፈጸመ ነው ብሎ ለማመን የሚያዳግት አሰቃቂ ድርጊት በማለት እንደገለጡት አስታውቀዋል።

በሰው ዘር ሰላም ላይ የተጣለ ጥቃት

በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የሽበራው ጥቃት በተጣለበት ወቅት ቅዱስነታቸው በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ በቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በኩል፦ የተጣለው የሸበራ ጥቃት እጅግ ከውታና ድንጓጤ እንዳሳደረባቸውና የዚህ አይነቱ የጥላቻ መንፈስ ቅዱስ አባታችንና ከሁሉም ሰላም ከሚያፈቅር ሕዝብ ጋር በመሆን ይኮንናሉ፣ በተጣለው የሽበራ ጥቃት ሰለባ ለሆኑት ሁሉ እንጸልያለን፣ ጥቃቱ በሰው ዘር ሰላም ላይ የተጣለ ነው፣ በመሆኑም ወሳኝ ምላሽ የሚያሻው ሁሉም በመተባበር እየተዛመተ ያለው በተለያየ መልኩ ለሚገልጠው የጥላቻ መንፈስ እንቃወም አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፓሪስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንድረ ቪንግት ትሮይስ በኩል ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የቴለግራም መልእክት፦ ለፈረንሳይ ሕዝብና ለአገሪቱ ያላቸው ፍቅር በመግለጥ፣ የሞት አደጋ ላጋጠማቸው እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው፣ ለሟቾች ቤተሰቦች ሁሉ ለእግዚአብሕር ምህረት እንዳወከፉም የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ የተሰማቸው ጥልቅ ኃዘን በመግለጥም ለዚያ እጅግ ለተፈቀረው ለፈረንሳይ ሕዝብ ያላቸውን ፍቅራዊ ቅርበት ገልጠው፣ ጸሎታቸውንም እንዳረጋገጡ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.