2015-11-11 15:08:00

ፊረንዘ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከህሙንና ከድኾች ጋር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳራ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በፊረንዘ ከተማ ባካሄዱት ሐውጾተ ኖልዎ በቅድስተ ማርያም ዘብሥራተ ገብርኤል ባዚሊካ ከህሙማንና ከድኾች ጋር መገናኘታቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ከእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል አባላት ጋር ተገናኝተው፦

ሰላምታ በማቅርብ እኩለ ቀን አብረው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ለሁሉም እዛው ለተገኘትና ላልተገኙት ህሙማንና ድኾች ቅርብ መሆናቸውና ለየት ባለ መልኩም በጾሎታቸውም ኅልዋን መሆናቸው እንዳረጋገጡ የባዚሊካው ካህን የገብረ ለማርያም ማኅበር አባል ኣባ ላምበርቶ ክሮቻኒ  ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የዛሬ 29 ዓመት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተመሳሳይ ግኑኝነት ማካሄዳቸው አስታውሰው ቅዱስ አባታችን በፊረንዘ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ በተገኙበትም ከሁሉም ጋር በአንድ ማእድ ተቀምጠው ምሳ መቋደሳቸው ገልጠዋል።

አብሮአቸው በማእድ የተቀመጡት ድኾችም ቅዱስ አባታችንን የእኛ ወገን በማለት እንደገለጡዋችውና በእውነቱ ለድኾች ለታመሙት ለሚጨቆኑት ለተነጠሉት ባጠቃላይ በተለያየ ችግር ምክንያት ከኅብረተሰብ ተነጥለው በህልውናና በከተማ ጥጋ ጥግ የሚገኙት ሁሉ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅርበት የታደሉና በቤተ ክርስቲያን ተልእኮና ልብ ቀዳሚ ለመሆናቸው ለማረጋገጥ እንደቻሉም ተመስክረዋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.