2015-11-09 16:11:00

በካሪታስ ለሚጠራው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ በፊረንዘ


እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ቶስካና ክፍለ ሃገር ሐውጾተ ኖልዎ በማካሄድ፣ በፊረንዘ የቶስካና ክፍለ ሃገር ርእሰ ከተማ በሚካሄዳው ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ተገኝተው መሪ ቃል እንደሚለግሱና ከቶስካና ክፍለ ሃገር ማሕበረ ክርስቲያንና ከማኅበረ ፍትኃ ጋር እንደሚገናኙም ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው በዚህ በሚያካሂዱት ሐውጾተ ኖልዎ በፊረንዘ የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫ ከሚረዱት የእኛ ቢጤዎች ጋር የምሳ መአድ ለመቋደስ እንደሚሹ ከወዲሁ የገለጡ ሲሆን ስለዚሁ ጉዳይ በማስመልከት በፊረንዛ የካሪታስ ቅርንጫፍ አስተዳዳሪ አለሳንድሮ ማርቲኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባክሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በእውነቱ ድኾችን ከፍ ከፍ የሚያደርግ በዚያ የተራድኦ ማኅበር ለሚያገለግሉት አክብሮትና ብርታት በእውነቱ ለሁሉም አቢይ ደስታ የሚጸግው ውሳኔ መሆኑ አብራርተው፣ በማእድ አብሮ መቀመጥ ወንጌላዊ ትርኢት ነው። ብዙ ጊዜ ኢየሱስ አብሮአቸው በማእድ ተቀመጠ የሚል ወንጌላዊ ቃል የሚያስተጋባ ሁሉም የሚበላና የሚጠጣ ማጣት እንደማይገባው የሚያሳስብ የቃልና የሕይወት አብነት የሆነ ቅዱስ ተግባር ነው ብለዋል።

በድኾች መአድ መቀመጥ አብሮ ምሳ መቋደስ ገዛ እራስ ክእነዚህ ወንድሞች ጋር እኵል ማድረግ ማለት ነው፣ ስለዚህ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል የማያስቀድም ስለ ድኻው የማያስብ ኅብረተሰብ ለተለያዩ አደጋዎች የተጋለጠ ይሆናል። እንዲህ ለመሆኑም ታሪክን መለስ ብሎ ማጤን ነው ብለው በዚያ ፊረንዘ በሚገኘው የካሪታስ ቅርንጫፍ በድኽነት የተጠቁት መጠለያ የሌላቸው አረፍ የሚሉበት የሚጸዳዱበት የገላ መታጠቢያ ቤት ያለው፣ ምሳ የሚቋደሱበት ማእከል ነው። የተነጠለው እንደ ውዳቂ የሚታየው ለብቻቸው የተተዉ አረጋውያን የጎዳና ተዳዳሪዎች በከተሞቻችንና በህልውና ጥጋ ጥግ ሁሉ የሚኖሩት የሚደገፉበት መሆኑ ማራቲኒ ገልጠው፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጉብኝት ቤተ ክርስቲያን ለድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ምንኛ ቅርብ መሆንዋ የሚመሰክር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.