2015-11-06 16:53:00

የኤውሮጳ ምክር ቤት፦ ማኅበረ አማንያን በጸረ አክራሪነት ተግባር ሚና


በኤውሮጳ ምክር ቤት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ፓውሎ ሩደሊ በሳራየቮ የኤውሮጳ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከህዳር 2 ቀን እስከ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ዓውደ ጉባኤ ተገንተው፣ አክራሪነት በመቃወም ተግባር የሁሉም ማኅበረ አማንያን ሚና ርእስ ዙሪያ ባሰሙት ንግግር፦ በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ያለው አሰቃቂው አክራሪነት ጸንፈኛነት ከወዲሁ ለመከላከል በትምህርት ቤቶች በሁሉም ሥፍራ ይኸንን ጸረ ሰብአዊ ተግባር የሚቀናቀን የሕንጸት ባህል በማቅረብ በተለይ ደግሞ የባህል አካላትና ወጣቶች ማነጽ ወሳኝ መሆኑ እንዳሰበሩበት ሲር የዜና አገልግሎ አስታወቀ።

በዚያ በጋራ ማንም የማይነጥል ሕብረተሰብ፣ የሁሉም ሃይማኖቶችና ኢሃይማኖተኛ እማኔዎች ጽንፈኛነትና አክራሪነት ከወዲሁ መከላከል በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ብፁዕነታቸው ባስደመጡት ንግግር፣ ባህላዊ ሃይማኖታዊ ልዩነት ኅብረአዊነት እንጂ ለግጭቶችና ለአክራሪነት ምክንያት ሊሆን አይችልም፣ ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶችና ኢሃይማኖታውያን እማኔዎች ጭምር አክራሪነት መዋጋት ያለው አስፈላጊነት ማስፋፋት ይጠበቅባቸዋል  በማለት የገለጡት ሃሳብ ዓውደ ጉባኤው በምልአት በማስተጋባት፣ ሁሉም ሃይማኖቶች የእያንዳንዳቸው ሃይማኖት በሉአላዊነት በመኖር በጋራ ለአወንታዊ ውጤት በመወያየትና በመተባበር ለጋራ ጥቅም ሊተጉ ይገባቸዋል እንዳሉም ሲር የዜና አገልግሎት ገለጠ።

በሃይማኖት ስም የሚከወነው አሸባሪነት ሃይማኖትን  የሚያዛባ ተግባር ነው

ሃይማኖተኛነት ቅዋሜው ባህርያዊና በኑባሬ በሰብአዊ መሆን ላይ የጸና እንጂ ታካይ ባህርይ አይደለም፣ ስለዚህ ይኽ ደግሞ በሁሉም ሰው ዘር መታወቅ የሚገባው ሓቅ መሆኑ ያብራሩት ብፁዕ አቡነ ሩደሊ አክለው፣ ብፁዕ ካርዲናል ፑሊጅች በዓውደ ጉባኤው በሃይማኖት ስም የሚፈጸመው ሽበራና ሃይማኖት ላሸባሪነት ምክንያት ማድረግ ሃይማኖትን ማዛባትና ጸረ ሃይማኖት ተግባር ነው በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ በማስተጋባት፣ ሆኖም ይላሉ ብፁዕነታቸው በሰው ዘንድ በኑባሬ ያለው ሃይማኖተኛነት አድማስ፣ ለሚደረገው የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ግኑኝነትና የጋራ ውይይት መሰርትና ለሚፈጠረው ችግር መፍትሔ እንጂ ችግር ተደርጎ መታየት የለበትም እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.