2015-11-04 16:16:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሐዘን መግለጫ መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማኒያ ርእሰ ከተማ ቡካሬስት በአንድ የመዝናኛ ሥፍራ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያስከትለው የሞትና የመቁሰል አደጋ ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት የሐዘን መግለጫ የተለግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሳቢያ 30 ወጣቶች የሞት አደጋ ሲያጋጥማቸው ሌሎች 180 የሚገመቱ ወጣቶች የመቅሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልእክት ለሟቾች ቤተሰብና ለመቁሰል አደጋ ለደረሰባቸው ቤተሰብ ለአገሪቱ መንግሥት በጠቅላላ ለአገሪቱና ለአገሪቱ ሕዝብ በመንፈስ ቅርብ መሆናቸው በማረጋገጥ፣ የሞት አደጋ የደረሰባቸው ጌታ በምህረቱ እንዲቀበላቸው፣ የመቁሰል አደጋ ለደረሰባቸውም ፈጣን ፈውስ ይጸገው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.