2015-11-04 16:26:00

መክሲኮ፦ ምንባብ ይሴባሕ አዋዲ መልእክት በሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት


እ.ኤ.አ. ህዳር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በመክሲኮ የተፈጥሮ የአየር ንብረት መለዋወጥ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት፣ የቤተ ክርስቲያን ዓንቀጸ እምነት የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት የጥናት ማእከልና የኮንራድ አደናዉር ማኅበር በመተባበር፦ ድኽነትና የተፈጥሮ የአየር ንብረት መለዋወጥ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት በይፋ ለንባብ በሚል ርእስ ሥር ብሔራዊ ዓቀፍ ዓውደ ጉባኤ በአገሪቱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፦ ዓውደ ጉባኤው በዋና አስተባባሪነት የመክሲኮ መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የተፈጥሮ የአየር ንብረት መለዋወጥ ጉዳይ ተከታታይ ልዩ ድርገት ሊቀ መንበር የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሲልቪያ ጋርዛ ጋልቫን መካሄዱ አስታውቀዋል።

የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ለመጀመሪያ ጊዜ በአገራቸው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት

የመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት፦ በመክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት በአገሪቱ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ሕንፃ ተገኝተው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት በይፋ በማቅረብ ንግግር ሲያደምጡ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ጠቅሶ፣ በመክሲኮ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በመወከል በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ንግግር ያስደመጡት የሞንተረይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሮገሊዮ ካብረራ ሎፐዝ የዚሁ ሰበካ ተባባሪ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኹዋን ኣርማንዶ ፐረዝ ታላማንተስ የመክሲኮ የሥነ ምኅዳርና የተፈጥሮ የሥነ አየር ንብረት መለዋወጥ የጥናትና የምርምር ተቋም ዋና አስተዳዳሪ ማሪያ አምፓሮ ማርቲነዝ አሮዮ መሆናቸው በማመልከትም ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ምንባብ በሥነ ምርምር ላይ ያተኰረ ዓውደ ጉባኤ እንደነበርም አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመክሲኮ የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት እንዲጎበኙ ይፋዊ ጥሪ

በታሪክ የመክሲኮ መንግሥት ጽኑ ሃይማኖት አግላይ ዓለማዊ ርእዮተ ዓለም ተከታይና ጸረ ክህነት አመለካከት የሚከተል መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም ቅሉ፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን የአገሪቱ መንግሥት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመክሲኮ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዲያካሂዱ በሚል ርእስ ዙሪያ በሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት በኩል ውይይት በማካሄድ ጥሪውንም በምልአተ ድምጽ እንዳጸደቀው የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አያይዞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. አገረ መክሲኮ እንደሚጐበኙም አስታቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.