2015-11-02 15:46:00

ቅድስት መንበር፦ የብሔራውያን ሕዳጣን ኅብረተሰብ ክፍል ኅልውና ነጻነት ዋስትና ማረጋገጥ


በመላ ኤውሮጳ አገሮች የጸጥታና የትብብር ድርጅት ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ያኑዝ ኡርባንችስክይ ባለፈው ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የብሔራውያን ሕዳጣን የኅብረተሰብ ክፍል መብትና ክብር ውሳኔ በኮፐንሃገን የዛሬ 25 ዓመት የተደረሰው የስምምነት ውል ምክንያት በማድረግ በኦስትሪያ ርእሰ ከተማ ቪየና በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር የማንኛውም ብሔራዊ ሕዳጣን የኅብረተሰብ ክልፍ መብትና ክብር ህልውና መስጠትና ቀጥሎም የእያዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ባህል ቋንቋም ጭምር ጥበቃና እድገት በሦስተኛ ደረጃም የአምልኮና ስግደት ነጻነት ያካተተ የሃይማኖት ነጻነት አክብሮትና ዋስትና እጅግ አስፈላጊና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ሥር የሚጠቃለል መሆኑ በማብራራት፦ ሕዳጣን የኅብረተሰብ ክፍል በሌላ አገር ከሚገኘው በባህል በቋንቋና በሃይማኖት አምሳያው ከሆነው ኅብረተሰብ ጋር የመገናኘት የወወያየት ሕጋዊ ነጻነት ያለው ነው። ስለዚህ ሕዳጣን በመሆኑ ተነጥሎ እንዲኖር መደረግ የለበትም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ኡርባንችስክይ ከባህል ከጎሳ ከብሐራዊና ከሃይማኖት ባሻገር የሰው ልጅ ማኅበራዊ መለያው የሁሉም ማሕበረሰብ እኵልነት የሚል ሕዳጣንም ይሁን ብዙኃን፣ የማኅበረሰብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል እኩልነት ማረጋገጥ እንጂ እንዱ በሌላው ላይ ተጽእኖ ሕዳጣን መሆኑ በብዙኃን መታፈን ወይንም ብዙኃን በባህል በሃይማኖት በቋንቋ የሕዳጣን አምባ ገነን መሆኑ የለበትም፣ በዜግነት ሁሉም እኩል ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ ከኮፐንሃገን ውል ወዲህ የማኅበረሰብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት መብትና ክብር ዋስትና በመስጠቱ ሂደት አወንታዊ ወጤት መገኘቱንም አስታውሰው ይኽ ደግሞ ለዴሞክራሲ ለሰላም ለፍትህ ብሎም ለመረጋጋት ሁኔታ መሠረት መሆኑ የሚመሰከር እውነት ነው። ስለዚህ ሕዳጣን የኅብረተሰብ ክፍል በአገር ጉዳይ በተገቢነት ማሳተፍ የሥልጣኔ ምልክት ነው። አቢዩ ተግዳሮትም በሁሉም በብሔራውያን  ማኅበራዊ መዋቅሮች ማንም የተነጠለ ሳይሆን ሁሉም ተዋኅህዶ የመኖር መብትና ክብር ዋስትና መስጠት የሚል ጉዳይ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕነታቸው ቅድስት መንበር የውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል መብትና ክብር እንዲከበር በማነቃቃቱ ዘርፍ አቢይ ሚና እንደሚትጫወት በቅርቡ በኤውሮጳ የሚኖሩት ዘላን ኅብረተሰብ ሰብአዊ መብትና ክብር ባህልና ቋንቋ እንዲክበር ለማሳሰብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከ 30 የኤውሮጳ አገሮች የተወጣጡ የሮምና የሲንቲ ጎሳ አባላት ተቀብለው ቤተ ክርስቲያን ለሕዳጣን የኅብረተሰብ ክፍል ቅርብ መሆንዋና የውሁዳን የኅብረተሰብ ክፍል መብትና ክብር ጥበቃ ማረጋገጥ የሁሉም ግዴታ መሆኑ የሚያመለክት ተግባር ነው በማለት ያስደመጡት ንግግር ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.