2015-10-28 15:49:00

ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ፦ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚላኖ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ.  ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚላኖ ሰበካ ሐውፆተ ኖልዎ እንደሚያካሂዱ የሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በሳቸው በተመሩት የሰበካቸው ካህናትና በሊባኖስ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል በቻራ ቡትሮስ ራይ መካከል በተካሄደው ግኑኝነት ወቅት ባሰሙት ንግግር ይፋ ማድረጋቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ ባስደመጡት ንግግርም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሚላኖ ሰበካ የሚከናወነው ሐውፆተ ኖልዎ ለሚላኖ ሰበካ ጸጋና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተ ክርስቲያን በእውነትና በፍቅር አማካኝነት ለእያንዳንዱ አለ ምንም የኃይማኖት የጾታ የባህል ልዩነት ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ቅርብ መሆንዋ ለመመስከር ባወጁት በቅዱስ የምህረት ዓመት ወቅት የሚከናወን በመሆኑም፣ በሚላኖ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አቢይ ጸጋና የእግዚአብሔር ምኅረት አገልጋይ በመሆን ጥሪ የሚያበረታታ ነው እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፦ እያንዳንዱን ሰው በእውነትና በፍቅር መሸኘት የሚለው ጥሪ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጠናቀቀው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው 14ኛው መደበኛ ጠቅላይ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በጥልቀት ያብራራው ሃሳብ መሆኑም ብፁዕነታቸው እንዳስታወሱትና ይኽ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በሚላኖ የሚያካሂዱት የሐውፆተ ኖልዎ መርሃ ግብር እንደተሰማም የሚላኖ ሰበካ ምእመናን ውሉደ ክህነትና የከተማይቱ የመንግሥት ተወካዮችና የከተማይቱ የመሥተዳድር አባላትና ተጠሪዎች የተሰማቸውን ደስታ ገሃድ ማድረጋቸውም ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.