2015-10-28 15:55:00

51ኛው የ 2016 ዓ.ም. ዓለም አቀፋዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ መርሃ ግብር


ቆላስይስ ምዕ. 1 ምዕ. ቍ. 27 “ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ የተስፋ ክብር ነው” በሚል አዲስ ኪዳዊ ቃል የሚመራው 51ኛው ዓለም አቀፋዊ የቅዱስ  ቍርባን ጉባኤ  እ.ኤ.አ. ከ ጥር 24 ቀን እስከ ጥር 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ፊሊፒንስ በምትገኘው ከተማ ሰቡ እንደሚካሄድ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኽ እቅድ የዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ቀደም ተብሎ በፊሊፒንስ ወንጌል የገባበት ዝክረ 500ኛው ዓመት ምክንያት በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የተሰጠ ውሳኔ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ ዓለም አቀፋዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን አቢይ ጸጋና መንፈሳዊ ገጠመኝ የምስክርነት በተለይ ደግሞ በኅብረት በሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ቅዱስ ቍርባን የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ምንጭ ብቻ ሳይሆን የዓለም ጭምር መሆኑ የሚመሰከርበት ቅዱስ ወቅት መሆኑ ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፣ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ኮሚቴ አባል አባ ቪቶረ ቦካርዲ፦ ይኽ በሰቡ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወዲህ ከገዛ እራሷ ወጥታ ወደ ሕዝብ ወደ ጥጋ ጥግ የምትል ቤተ ክርስቲያን መግለጫና ምስክርነት ሲሆን፣ ወደ የተከተኖቻችን ወደ መልክኣ ምድር ጥጋ ጥግና ወደ የህልውና ጥጋ ጥግ መውጣት የሚል ተልእኮ ቅዱስ ቁርባናዊ አድማስ ያለው ነው። እርሱም እኛ በጥጋ ጥግ የነበርን ሊገናኘንና ሊያድነን ወደ እኛ የመጣው የሚሰዋው የፍቅር ቅዱስ ኅላዌ ነው እንዳሉ ያመለክታል።

በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት በፊሊፒንስ የሰቡ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኾሴ ፓልማ፦ እስያ በውፉይ ሕይወት ጥሪ በክርስትና ተቀባይ ዜጋ ቁጥር ከፍ ብሎ የሚታይባታ ብቻ ሳትሆን በክርስትያን ምእመናንና በውፉይ ሕይወት አባላት እድገት ከፍተኛ ሥፍራ የያዘች መምጣትዋንም ጠቅሰው ቢሆንም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በእስያ አሁንም ሕዳጣን ነች። መካከለኛው ምስራቅ ኢየሱስ የተወለደበትና ሞቶ ሞትን አሸንፎ የተነሳበት ክፍለ ዓለም ሆኖ እያለ ክርስትያን በዚያ ክልል ሕዳጣን ነው። ይኽ 51ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ በፊሊፒንስ በእስያ መሬት እንዲካሄድ መወሰኑም በክፍለ ዓለሙ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚያንጸባርቅ የምታካሂደው የምትሰጠው መንፈሳዊና ሰብአዊ አገልግሎት የምታከናውነው አስፍሆተ ወንጌል የሚመሰክር ነው ብለው፣ በሚካሄደው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ 20 ብፁዓን ካርዲናሎች 50 ብፁዓን ጳጳሳትና በፊሊፒንስ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት በጠቅላላ እንደሚሳተፉና የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ መክፈቻ የሚያርገው መስዋዕተ ቅዳሴ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን በመወከል የሚመሩትም የምያንማር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የያንጎን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ማኡን ቦ መሆናቸው አስታውቀዋል። በመቀጠልም ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፒየሮ ማሪኒ፦ በሰቢ ለአንድ ሳምንት እርሱም እ.ኤ.አ. ከ ጥር 24 ቀን እስከ ጥር 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ከመላ እስያ አገሮች የተወጣጡ መንፈዊ ንጋድያን የሚያሳትፍ መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚያርግበት ጸሎትና አስተንትኖ አስተምህሮና ትምህርተ ክርስቶስ የሚቀርብበት ምስክርነት የሚሰጥበት እውነተኛው ቤተ ክርስቲያናዊ ውህደትና ትብብር የሚኖርበት ቅዱስ ወቅት ነው ብለዋል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.