2015-10-23 16:16:00

ብፁዕ አቡነ ፍራቲላ፦ የእግዚአብሔር ምህረት ሕይወትን ለመለወጥ የሚያበቃ ኃይል ነው


በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው በ 14ኛው ይፋዊ መደበኛ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት በሮማኒያ የቡካሬስት የቅዱስ ብሲሊዮስ አቢይ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚሓይ ካታሊን ፋቲላ ስለ ሲኖዶሱ ሂደት በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በሲኖዶስ መሳተፍ አቢይ ዕድልና እጅግ ኃብታም ገጠመኝም ነው። እያንዳንዱ የሲኖዶስ ተሳታፊ ብፁዕ ጳጳስ በክልል ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተጨባጭ ሁነት የሚውክል ቢሆንም ካቶሊካዊነት አንድ የሚያደረገው የኵላዊነት መሠረት የሆነው ባህይር በጋራ የሚኖርና ይኸንን እውነት የሚመስክር ነው። ስለዚህ በዚህ ሲኖድስ የሚታየው ገጠመኝም ይኸንን ይመስላል ብለዋል።

የቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እየመከረ ያለው ሲኖዶስ በተደጋጋሚ የእግዚአብሔር ምኅረት ጉዳይ ብዙ ተወያይተዋል፣  ስለዚህ ምኅረት ሲባል ሃዘኔታ ማለት ሳይሆን ሕይወት የሚለውጥ ከጌታ የሚሰጥ ኃይል ነው፣ በሲኖዶስ የተጠቀሰው ምህረት የሚል ቃል ይኸንን የሚያስተውል ነው።

ቤተ ክርስቲያን የእምነት ብርታት የክርስቶስን ብርታት የምትከተል እንጂ በገዛ እራሷ ላይ ጸንታ በገዛ እራሷ የምትራመድ አይደለችም፣ ስለዚህ የክርስቶስ መንገድም የመስቀል የጎልጎታ መንገድ ነው። የምቾት የድሎት ጎዞ አይደለም ካሉ በኋላ የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለ 41 ዓመት የሚያክል እርሱም ከ 1948 እስከ 1990 ዓ.ም. በዓለም መንፈስ አማካኝነት እንድትዘጋ ተደርጋ መቆየትዋንም ገልጠው፣ ሆኖም በዚያ የስግደትና የአምልኮ ነጻነቷ ተረግጦ በነበረበት ዓመታት በስውር አግልግሎት ከመስጠት አልተቆጠበችም፣ እንዳውም በዚህ መስቀል ማለፏም በሁሉም መስክ እንድታድግ በጅቷታል፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት ባህላዊ አምባገነን አስተሳሰብ በተስፋፋበት ዓለም ወንጌልን ማነቃቃት በቃልን በሕይወት መመስከር ቃለ እግዚአብሔር በምእመናን ዘንድ ኅያው እንዲሆን ማነቃቃት ወሳኝ ነው። በኮሚኒስቱ ሥርዓት ምክንያት ለስደት ለመከራ ለስቃይ ተዳርጋለች፣ ሆኖም አንድም ቀን ከመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ያላት ኅብረትና ለዚህ መንበር ያላት ታዛዥነት አላገለለችም፣ የመንግስተ ሰማይ እሴቶች ከዕለታዊ ችግሮቻች ማዶ ወደ ላይ እንድናቀና ይገፋፉናል፣ ክርስቶስ እንዳለውም እምነት ለመመስከር በማንፈልገው መንገድ በስቃይና በመከራ መንገድ ለመጓዝ የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ ከዚህ እውነት የሚለየን አንድም ነገር የለም፣ ብፁዓን አበው ይኸንን እውነት በተለያየ መንገድ እያስተጋቡ ናቸው፣ አብሮ ስለ ቤተሰብ እርስ ዙሪያ በመመስከርም ይኸው ስለ በቤተሰብ ጉዳይ እውነት እየመሰከሩ ናቸው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.