2015-10-21 15:46:00

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም.


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ከጀምረበት ቀን ወዲህ በእያናንዷ ቀን ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ስላካሄዱት ውይይት በማስደገፍ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በተለያዩ የሲኖዶስ አበው ወይንም በአንዳንድ በሲኖዶሱ በታዛቢነት ከተገኙት ውስጥ ተሸኝተው የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል፦ ሲኖዶሱ በተናንሽ ቡድን ተከፋፍሎ የሚያካሂደው የውይይት መርሃ ግብር መጠቃለሉ ገልጠው፣ እነዚህ 13 የተለያዩ ተናንሽ ቡድኖች ከቀትር በኋላ እያንዳንዱ ቡድን የገዛ እራሱ የፍጻሜ ሰነድ እንዳቀረበ ከገለጡ በኋላ አክለው አብሯቸው በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኙትን የባርቸሎና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ልዊስ ማርቲነዝ ሲስታክ፣ በደቡብ አፍሪቃ የዱርባን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዊልፍሪድ ፎክስ ናፒየር በመክሲኮ የሞረላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አለበርቶ ሷረዝ ኢንዳ ለጋዜጠኞች ክስተዋወቁ በኋላ ብፁዕ ካርዲናል ሲስታክ ቤተሰብ ተጋርጦ ብቻ ሳይሆን ዕድልም ጭምር ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ በሰጡት መግለጫ ለምስጢረ ተክሊል የሚሰናዱት በተገባ መንገድ ለማሰናዳት የሚሰጠው ትምህርተ ክርስቶስ ያቋረጭ መሆን የለበትም ይኽ ደግሞ ፍች መለያየት እንዳይኖር ይደግፋል ብለው፣ የታሰረው ምስጢረ ተክሊል ይፈታ የሚል ብይን የመስጠቱ የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ከቤተ ክርስቲያን የምኅረት ጥሪ ጋር ውህደት ያለው ነው። ይኽ ደግሞ ያንን ምስጢረ ተክሊል አይሻርም ከሚለው ከሥርወ እምነት ጋር የተጣመረ ሂደት መሆኑ አብራርተው ስለዚህ ይኸንን ጉዳይ የሚመለከተው በተለያዩ አገሮች በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤቶች የሚቀመጡት አገልጋይ ዳኞች ተገቢና የበቃ ሕንጸት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመቀጠልም ብፁዕ ካርዲናል ስዋረዝ ኢንዳ፦ መንግሥታት ቤተሰብ የሚከላከሉ መሆን ይገባቸዋል ብለው፣ ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት ነው፣ በመሆኑም ይኽ መሠረት እንክብካቤ ካላገኘ ኅብረተሰብ ላደጋ ይጋለጣል። ቤተሰብ የኅብረተሰብ ሁነት መስተዋት ነው ካሉ በኋላ ቤተ ክርስትያን ለቤተሰብ በምትሰጠው አገልግሎት አማካኝነት ጤናማ ኅብረተሰብ በማነጽ ረገድ አቢይ ሚና ትጫወታለች፣ የጥሪ ሚና ነው። የተልእኮ ሚና ነው ብለው፦ ቤተክርስቲያን በብፁዓን ጳጳሳት አማካኝነት ምኅረትንና ርህራሄ ትመሰክራለች ሲሉ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መክሲኮን የመጎብኘት እቅድ አላቸው ወይ የሚል ካንድ ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፣ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለመክሲኮና ሕዝቧ አቢይ የደስታ ምክንያት ነው ምንም’ኳ መቼ ይከናወናል ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ባልችልም በርግጥ ጉብኝቱ እንደሚከናወን አምናለሁ ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ናፒየር፦ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ለሲኖዶስ ተስፈኝነትን ያቀርባሉ ብለው፣ ይኽ ሲኖዶስ የሚከተለው መንገድ የሚያመላክቱ አቢያተ ሰቦች ናቸው። ስለ ቤተሰብ ርእሰ ጉዳይ እየመከረ ያለው ሲኖዶስ የሚከተለው መንገድ በቤተሰብ በኩል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን የቤተሰብ ጥሪና ተልእኮ በቤተ ክርስቲያን ስለ ሚለው ጉዳይ ማተኰር እጅግ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ለምሥጢረ ተክሊል የተጠሩትን ቅድመ ቃል ኪዳንና ድኅረ ቃል ኪዳን ተገቢ ቀጣይ ህንጸት በማቅረብ ቤተሰብ ትሸኛለች፣ ቤተ ክርስቲያን በታደሰው ቤተሰብ ትታደሳለች። የቤተሰብ መታደስ የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴ ነው ብለው ብፁዕነታቸው ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የ13 ብፁዓን ካርዲናሎች ፊርማ የተኖረበት የተላለፈው የግል መልእክት ጉዳይ በተመለከተም ፈርመዋል ከተባሉት ውስጥ ናቸው የሚለው ጉዳይ ምን ይላሉ የሚለው ካንድ ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የመገናኛ ብዙኃን ስለዚሁ ጉዳይ ብዙ ተናግረዋል፣ በእውነቱ ጣልቃ ገብነትም ነው። ሆኖም መልእክቱ ቅዱስ አባታችን ግልጽነትና በትህትና መደማመጥ በማለት የገለጡት ሃሳብ የሚመሰክር ነው። ሲኖዶሱም ጉባእያዊነት የመሰከረ ነው። ጉባእያዊነት ለቤተ ክርስቲያን መልካምነት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ዙሪያ ማለት ነው፣ ስለዚህ ከዚህ በላይ ኅብረትና ውህደት መግለጫ የሚኖረው አይመስለኝም በማለት መልስ ከሰጡ በኋላ አባ ሎምባርዲ እንዲህ ባለ መልኩ ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄ መልስ ለመስጠትና የሲኖዶሱ ውሎው በማስደገፍ የተካሄደው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እዚህ ላይ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.