2015-10-19 15:22:00

አባ ስፓዳሮ፦ ቤተ ክርስቲያንና ዓለም


ይኽው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጀመረው 14ኛው ይፋዊ መደበኛ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚጠናቀቅበት ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. እየተቃረበ ሲሆን፣ በሲኖዶስ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ካቶሊካዊት ስልጣኔ የተሰየመው የማኅበሩ በየሁለት ሳምንት የሚታተመው መጽሔት ዋና አስተዳዳሪ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባክሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ይኽ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ እየመከረ ያለው ሲኖዶስ  ኅብረ ተመክሮ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ተሳታፊ ሆነህ እዛው ስትገኝ መላ ዓለም የሚወክል ስለ መላ ዓለም ቤተሰብ ጉዳይ የሚመክር ጉባኤ መሆኑ ትገነዘባለህ፣ በተለያዩ አገሮች ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተወጣጡ እረኞች በአንድ ላይ ሆነው ኵላዊነት በሚያንጸባርቅ ሁነት ስለ መላ ዓለም ቤተሰብ ጉዳይ ሲመክሩ በተለያዩ አገሮች የሚኖረው የተለያየ ተመክሮ የሁሉም ተመክሮ እንዲሆን የሚያደርግ ኵላዊ ጉባኤ ነው። ቤተሰብ የሚያቀርበው ተጋርጦ በወንጌላዊ ዓይን በመመልከት የሚቀርቡት ጥያቄዎች በማዳመጥ ተገቢ ወንጌላዊ መልስ ለመለየት የሚጥር ነው።

ቤተ ክርስቲያን ከተጨባጩ ዓለም ፊት ምን ዓይነት ግኑኝነት ሊኖራትና እንዴት መወያየት እንዳለባትና ወቅታዊው ዓለም የሚያቀርበው ተጋርጦ አበይት ማኅበራዊ ለውጦች ዙሪያ ሁሉ የሚመክር ነው። ለተጨባጩ ዓለም መልስ ለመስጠት ተጨባጩን ዓለም ማዳመጥ ያስፈልጋል፣ ማንም ሰው ለወንጌል ባዳ አይደለም፣ ወንጌል ሰው ላይ ያነጣጠረ የሚወግር ድንጋይ የሆነ እጅ የሚቀስር  የረቂቅ ሥርወ እምነት ስብስብ አይደለም፣ ስለዚህ በወንጌል ብርሃን ዓለም የሚያቀርበው ተጋርጦ ማጤን የሚል ሲኖዶስ ነው ብለዋል።

በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ ሲኖዶስ ብቻ ሳይሆን ሲኖዶስዊ ማለትም ጉባኤያዊም ጭምር ነው። ይኽ ደግሞ ቀደም ተብሎ እ.ኤ.አ. 2013 ዓ.ም.  የሲኖዶሱ የማካሄጃ ሰነድ ለማጠናቀር ታልሞ በዓለም ወደ ሚገኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን የተላከው የጥያቄዊ ሰነድ ያረጋግጠዋል። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያዊነት ባህርይ እየተኖረ ነው፣ በዚህ የሚጠቃለል ሳይሆን በሚገባው የምኅረት ዓመት ጭምር የሚመሰከር ነው። ስለዚህ ድካም ውጥረት አለ መግባባት ሊታይ ይችላል፣ ሊያስገርመንም አይገባውም። ምክንያቱም በጋራ ታሪክ ለመገንባት የሚያደርግ ያ የሁባሬ ጉዞ የሚሰጠው አቢይ ደስታ ነው የሚጎላበት ነው። ወንጌል ምኅረት ነው፣ የጌታ ምኅረት ነው። ሲኖዶሱ ከዚህ የሚጀምር በዚህ የሚጠቃለል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ ፈጽመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.