2015-10-19 15:19:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለኢየሱስ ያለን ፍቅር ለሕዝብ የሚኖረን ፍቅር ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 18 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የተልእኮ ቀን ምክንያት “ለኢየሱስ ያለን ፍቅር ለሕዝብ የሚኖረን ፍቅር መግለጫ ነው” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት እያንዳንዱ ምሥጢረ ጥቅመት የተቀብለ ሁሉ ባለበት በሚኖርበት በተሰማራበት ለሁሉም ያንን የእውነተኛ ደስታ ምንጭ የሆነውን ወንጌል ያደርስ ዘንድ ተጠርተዋል፣ ወንጌላዊ ተልእኮ በአሁኑ ወቅት የተደቀነበት ተጋርጦ የሁሉም ሰው ዘር እናስርና መሠረታዊ ፍላጎት ማክበር የሁሉም ባህሎች ክብር እቃቤ የሚል ነው። ስለዚህ ወንጌል ለሚደረስለት ሕዝብ ቀርቦ ባህሉን ቋንቋውን ማወቅ እሳቤው መገንዘብ ይኽ ደግሞ የሕዝቦች እሳቤ የእግዚአብሔር ምስጢረ ጥበብና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌላዊ ጥበብ እንዲስተዋል ለማድረግ የሚያገለግል እንዲሆን የሚያግዝ ነው። ወንጌላዊ ልኡክነት ኢየሱስ ለባህሎች ብርሃን መሆኑ የሚመሰክርና ባህሎች ወንጌልን በመቀበል እንዲለወጡ የሚያደርግ የቃልና የሕይወት ወንጌላዊ አብነት ያለው አስፈላጊነት የሚያመለክት ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው ባሰላለፉት መልእክት በወንጌላዊ ልኡክነት የዓለማውያን ምእመናን ተሳትፎ ያለው አስፈላጊነት ያሰመሩበት ሲሆን ወንጌል ለከተሞቻችን ጥጋ ጥግና ለህልውና ጥጋ ጥግ ክልል ማበሰር የሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን ኃላፊነት ነው እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አክለው ወንጌል የተቀበለ ወንጌል ለማካፈል የተቀበለው ወንጌላዊ ደስታ እንደሚያነቃቃውም ማብራራታቸው ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.