2015-10-16 15:47:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ተቆጣጣሪ የለውም፣ ፍቅሩ በነጻ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁለ ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል የእግዚአብሔር አድማስ የሚያጠቡና ፍቅሩን ትንሽ ከሚያደርጉ ከሕግ ሊቃውንት እንጠንቀቅ የሚል ሃሳብ ማእከል ያደረገ በፍቅር ትእዛዝና የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ተቆጣጣሪ የመሆን ፈተና ዙሪያ በለገሱት ስብከት፦ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነጻው የማዳን እቅድ ብዙ ክርስቲያኖች ለመረዳቱ ያዳግታቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ ለነበረው ሕዝብ በክርስቶስ ስለ ታደለው ድኅነትና ጽድቅ ለማስረዳት እጅግ ያዳገተው ነበር። እውነተኛው ሥርወ እምነትም ድህነት በነጻ መታድል የሚል ነው። ብዙዎቻችን ኢየሱስ የእግዚአብሔር አንድይ ልጅ ነው። እኛን ሊያፈቅር መጣ፣ ሊያድነን መጣ፣ ስለእኛ ሞቶ ሞትን አሸንፎ ተነሣ የሚለውን ሥርወ እምነት ማዳመጡና መድገሙም በሚገባ የተላመድን ነን፣ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ምሥጢር ስንገባ እርሱም ፍቅሩ ወሰን ወይንም ገደብ የሌለው መሆኑ የሚገልጥ እውነት ስንሰማ እንገረማለን ወይንም አለ መረዳቱን እንመርጣል።

የእግዚአብሔር አድማስ አናሳጥር፣ ፍቅሩ ገደብ የለውም

ኢየሱስ ያለውን ማድረግ፣ በነጻ ለታደለኝ ድህነትና ፍቅር የምሰጠው ተገቢ መልስ ኢየሱስ ያለውን መፈጸም ነው። ኢየሱስ የሕግ ሊቃውንቶችን ይቃወማል፣ እናንተ የእውነተኛው እውቀት ቁልፍ ለራሳችሁ ብቻ አደረጋችሁ፣ እናንተ አትገቡ ሌላውንም የማታስገቡ መሰናክል ትሆናላችሁ፣ ለምን ያንን የእውነተኛው እውቀት ቁልፍ ነጠቃችሁ? ያንን በነጻ የታደለው የጽድቅና የድኅነት ቁልፍ ለመቆጣጠር ለምን ቃጣችሁ? እነዚህ የሕግ ሊቃውንት ትእዛዞችን ብቻ በመፈጸም የድኅነት ባለቤት ለመሆን እንደሚቻልና እንዲህ ባለ መንገድም የድኅነት ይገባኛል ባለቤት ለመሆን ይቃጣቸዋል። ትእዛዛት የማይፈጽም ሁሉ ውጉዝ ነው ይላሉ። እንዲህ ባለ መንገድም የእግዚአብሔርን አድማስ ለማጥበብ ይሞክራሉ። የእግዚአብሔር ፍቅር በገዛ እራሳቸው የሚለኩ፣ በገዛ እራሳቸው የሚመዝኑ። የማዳኑ እቅድ ሕግ በማክበር የሚመዝኑ ናቸው። ኢየሱስም ቅዱስ ጳውሎስም የድህነት መመዘኛው ሕግ መፈጸም ነው የሚለው አይነት ሥርወ ትምህርት ነው የተቃወሙት።

የድህነት ተቆጣጣሪ አለ መሆን

እርግጥ ነው ትእዛዛት አሉ፣ ሆኖም የሁሉ ትእዛዝ ጽማሬ እግዚአብሔርን ማፍቀርና ጎረቤትን ማፍቅር የሚለው ትእዛዝ ነው። እንዲህ ባለ መልኩም እኛ ለዚያ በነጻ ለታደለው ድህነት የበቁ እንሆናለን። በስተ ጀርባው ሌላ ህቡእ ጥቅም ያላዘለ ነጻ ፍቅር፣ የላቀውና ሁሉን ትእዛዝ የሚያጠቃልለው እግዚአብሔርን በሙሉ ሕይወትህ በሙሉ ልብህ በሙሉ ኃይልህ ማፍቅርና ባለ እንጀራህንም ማፍቀር የሚለው ትእዛዝ ነው። ይክ ኢየሱስ የሰጠው ትእዛዝ የተቀሩት ሁሉ ትእዛዛት ያጠቃለላሉ፣ የትእዛዛት ፍጻሜም ፍቅር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን በሙሉ ሕይወትህ በሙሉ ልብህ በሙሉ ኃይልህ ማፍቅርና ባለ እንጀራህንም ማፍቅር የሚለው ትእዛዝ  ነው።  የሕጎች ምንጭና አድማስ ፍቅር ነው። ለፍቅር በሩን የሚዘጋ ገዛ እራሱ ከድህነት ያገላል።

በዚህ በያዝነው ዓመት ቅድስት ተረዛ ዘአቪላ የተወለደችበት ዝክረ አምስት መቶኛው ዓመት እየተከበረ ነው። የፍቅር አድማስ የማስተዋሉ ጸጋ የታደለች ቅድስት ነች። ስንቱ ይኸንን በነጻ የታደለንውን ፍቅር ለማድረስና ለመከላከል የእምነት ሰማዕት ሆኗል፣። ሥርወ እምነቱ በነጻ የታደለን የድህነት እቅድ ነው።

የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመወሰን በሚሞክር እንዳንታለል ገዛ እራሳችንን እንጠብቅ

ዛሬ እኔ ጌታ በነጻ እንዳዳነኝ አምናለሁ ወይ? ለድህነቱ የተገባሁኝ እንዳልሆንኩኝ አምናለሁ ወይ? ለድህነቱ የተገባሁኝ መሆኔም በኢየሱስ መሆኑ አገነዘባለሁ ወይ?  እርሱ ስለ እኔ ባደረገው ሁሉ ለመዳኑ የተገባሁኝ ሁኛለሁ? የሚሉትን ጥያቄዎች እስቲ ዛሬ ለገዛ እራሳችን እናቅርብ። የአብና የእናት ፍቅር፣ እግዚአብሔር አባትና እናት ነው። መለኪያ የሌለው ፍጹም ፍቅርም እርሱ ነው። በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.