2015-10-14 16:19:00

የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም.


የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ከጀምረበት ዕለት ወዲህ በእያናንዷ ቀን ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ስላካሄዱት ውይይት በማስደገፍ በእያንዳንዷ ቀን በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በአናንድ ሲኖዶስ አበው ወይንም በአንዳንድ ታዛቢ አካላት ተሸኝተው የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አባ ሎምባርዲ አብሮአቸው የተገኙት የሩዋንዳ ዜጋ ፈደራላዊ የአፍሪቃ አቢያተ ሰብ ማኅበር አማካሪና የመርሃ ሕንጸት አባል ተረሰ ንዪራቡከየ፣ በካናዳ የሥነ ሕይወት ሥነ ምግባር ተቋም ዋና አስተዳዳሪ ሞይራ ምክክዊን እንዲሁም በቅዱስ ኦቲሊያ የበነዲክታውያን ገዳም አበ ምኒየት አባ ጀርሚያስ ሽሮደር በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለተገኙት በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካን ጋዜጠኞች በማስተዋወቅ፦ በቅድሚያ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በኩል እየተሰራጨ ስላለው እርሱም 13 ብፁዓን ካርዲናሎች ፊርማቸው ያኖሩበት ለቅድሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተላለፈ የሚባለው ምሥጢራዊ መልእክት፣ የመልእክቱ ይዞታና ፊርማቸውን ያኖሩ የ13 ብፁዓን ካርዲናሎች ስም ዝርዝር በማስደገፍ እየተባለ ያለው ጉዳይ ጠቅሰው ይኽ ተግባር የሲኖዶስ ሂደት ለማወክ ያለመ ነው የሚመስለው ሆኖም ብፁዓን የሲኖዶስ አበው በሁኔታው እንደማይታወኩና እንደማይወሰኑም ነው ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፐል ስለ ጉዳይ እንዳሉትም በርግጥ መልእክቱ ተላልፈዋል ሆኖም ለቅዱስነታቸው የተላለፈ የግል መልእክት፣ የግል ሆኖ መቅረት ነበረበት፣ የመገናኛ ብዙኃን ስለ መልእክቱ ይዞታና ፈራሚዎች ያኑር ብፁዓን ካርዲናሎች ስም ዝርዝር ዙሪያ እየሰጡት ያለው ዜና ከእውነት የራቀ ነው። ፍሪማቸውን አኑረዋል ተብለው ስማቸው ከተጠቀሱት ውስጥም ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ ብፁዕ ካርዲናል ቪንግት ትሮይስ ብፁዕ ካርዲናል ፒያቸንዛና ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ አስተባብለዉታል።

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. አንዳንድ የተቃውሞና የመጠራጠር ሁኔታ እንደነበር አባ ሎምባርዲ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀው እንደነበር በማስታወስ፣ እንዳውም የሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ባልዲሰሪ ከዛም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጥርት ባለ ሁኔታ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ለጉባኤው መልስ ሰጥተውበታል።

ጉዳዩ አጥጋቢ መልስ የተሰጠበት ሆኖ እያለ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተላልፎ የነበረው መልእክት ይዞታና የመልእክቱ ፈራምያን ብፁዓን ካርዲናሎች ብሎ በዜና መልክ ማቅረቡ የሲኖዶሱ ሁነት ለማወክ የሚቃጣቸው እንዳሉ የሚያስገነዝብ እንጂ ብፁዓን አበው በሚሰራጩት የተባለ ዜና እንደማይወሰኑ አባ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

ሲኖዶሱ ሙሉ ትብብርና አወንታዊ ሂደት የተካነ ነው

ሲኖዶሱ የሚከተለ አግባብ አዲስ መሆኑ ሊያስገርም አይገባውም፣ የሲኖዶሱ ሂደት ሙሉ ትብብር የተካነው እወንታዊ መሆኑም አባ ሎምባርዲ ገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ናፒየር ካንድ የመገናኛ ብዙኃን ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ካሉትና ካሰቡት ውጭ የሆነ ትርጉም የተሰጠው እርሱም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሲኖዶሱ ጠቅላይ የፍጻሜ ሰነድ አጠናቃሪ ድርገት በራሳቸው እንደመረጡና ይኽ ሂደት እንደማይደገፉ የሚያስመስል የተላለፈው የተሳሳተ ዜና መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ናፒየር ድርገቱ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመመረጡ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት መብት እጥያቄ ውስጥ እንዳላስገቡ አባ ሎምባርዲ አብራርተው፣ ይኽ የማረሚያ መግለጫ እንዲሰጥም እራሳቸው ብፁዕ ካርዲናል ናፒየር መጠየቃቸውም ሎምባርዲ ገልጠዋል።

በጥሪና በቤተሰብ ሕይወት መካከል ያለው ግኑኝነት

በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት አባ ጀርሚያስ ሽሮደር ሲኖዶሱ በጥሪና በቤተሰብ ሕይወት መካከል ያለው ግኑኝነት በስፋት የተወያየ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ የክህነት የገዳማዊ ሕይወት ጥሪ ተቀብለው ገዳም በመግባት ካህናት ገዳማውያን የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ለመሆን የበቁት የጥሪ ጸጋ የተቀበሉት በአሁኑ ወቅት ብዙውን ጊዜ ከአማኝ ከቶሊካዊ ቤተሰብ ሳይሆን እምነት ጋር ከመገናኘትና እምነትን ከሚኖር ሕይወት የሚገኝ ጥሪ ሆኖ ነው የሚታየው። ይኽ ደግሞ ለጥሪ መሠረት የሆነው ማኅበራዊ ጉዳይ እየተለወጠ መሆኑ የሚያመለክት ነው፣ ስለዚህ ለጥሪ መሠረት ቤተሰብ ነው ይባል የነበረው አገላለጥ የሚሰርዝ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በስፋት ከእምነት ብስለት የሚገኝ ጥሪ መሆኑ በስፋት እየታየ ነው ብለዋል።

ሴቶች ለዱቁና ማእርግ የሚለው ጥያቄ

ለሴቶች የድቁና ማዕርግ ይፈቀድ የሚለው ጥያቄ በሲኖዶሱ የተነሳ ቢሆንም ስለዚሁ ጥያቄና ርእስ በተመለከተም በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ ውይይት ገና እንዳላካሄደበት አስታውቀዋል።

የተረሰ ንዪራቡከየ ምስክርነት

ቤተሰብ በአገራዊ እርቅ ጎዳና አቢይ ሚና አለው፣ ይኸንን ያሉትም የሩዋንዳ ሁኔታ በማስታወስ ሲሆን፣ ይኸንን ጉዳይ እራሳቸው የኖሩት ተመክሮ መሆኑ ገልጠው፣ ቤተሰብ የፍቅርና የእርቅ ምስክርነት ተገቢ ሥፍራ ነው ብለዋል። በመቀጠልም ካናዳዊት ሞይራ ማክክዊን በዚህ በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ ለታዛቢ አካላት የሚሰጠው ትክረት እጅግ ደስ የሚያሰኝ መሆኑ ገልጠው፣ ሲኖዶሱ በታዛቢነት በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የሚያስደምጡት ንግግር በጥልቀት እያዳመጠው ነው። ይኽ ደግሞ በእውነቱ ቤተ ክርስቲያን የምትኖረው ለየት ያለ እምነት ማእከል ያደረገ ዴሞክራሲያዊነት የሚመሰክር ነው ካሉ በኋላ አባ ሎምባርዲ እንዲህ ባለ መልኩ ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የቀረበው የዕለቱ ጋዜጣዊ መገልጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.