2015-10-14 16:26:00

የሥነ ኤኮኖሚ ኖበል ተሸላሚ


የብሪጣኒያና የተባበሩት የአመሪካ መንግስታት ዜግነት ያላቸው ኣንጉስ ደኣቶን እ.ኤ.አ. የ 2015 ዓ.ም. የሥነ ኤኮኖሚ ኖበል ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። ስለ ፍጆታ ስለ ድኽነትና ልማት በተመለከተ ያካሄዱት ጥልቅ ጥናትና ድኽነት ለመዋጋት በኤኮኖሚው ዘርፍ መርህ መሆን የሚገባው የኤኮኖሚ ሂደት ያመለከቱ፣ ድኽነት በማጎደል የሁሉም በኤክኖሚ መስክ የተስተካከለና የበለጠ ሕይወት ለመኖር የሚያግዝ የኤኮኖሚ ፖሊቲካ ለመወጠን የሚያበቃ ያብራሩት የሥነ ኤክኖሚ መሠረተ እሳቤ ለዚህ ሽልማት ብቁ ካስባሉዋቸው ምክንያቶች ውስጥ ለመጥቀስ ይቻላል።

ደአቶን የ 69 ዓመት እድሜ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥት ፕሪስቶን መንበረ ጥበብ መምህር ከደረስዋቸው መጽሓፎውች ውስጥ የመጨረሻው አቢይ ሽሽት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ የሚዘከር ሲሆን፣ በዚህ መጽሓፍ ዘንድ የድሆች ብዛት ቆጠራ ለማከናወን የሚደግፍ የሥነ አኃዝ አግባብ የፈለሰፉና፣ በዚህ ስልት አማካኝነትም ዜጎች በገዛ አገራቸው የምጣኔ ኃብት እድገት ተጠቃሚ ከመሆን የተገለሉ መሆናቸው ሰፊ ትንተና እንደሰጡና፣ እነዚህ ከአገር ምጣኔ ኃብት ተጠቃሚነት ውጭ የሚሆኑ ዜጎች ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱንም ያመለክታሉ።

የጸአት ክስተት፣ በዓለም የሚታየው የእኩልነት አልቦ እድገት መስፋፋት የሚወልደው ነው

እኚህ የኤክኖሚ ሊቅ በዓለም በድኽነት የተጠቁት ብዛት ለማወቅ የሚደግፍ በዓለም እግብር ላይ እየዋለ ያለው ስልት፣ ስለ ድኽነትና የድኽነቱ ብሎም የድኽነት መስፋፋት ምክንያት በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት የማያሰጥ መሆኑ በስፋት ያስገነዘቡ፣ የስደተኛው ጸአት ዋናው ምክንያት  ድኽነት መሆኑ የሚያብራሩ፣ በድኽነት የሚገኘው ለከፋ ድኽነት የሚዳረግ በዓለም የሚታየው የኑሮ ልዩነት ከፍ እያለ መምጣቱና ባጠቃላይ የእኩልነት አልቦ ኤኮኖሚያዊ ሂደት የሚያስከትለው መሆኑ ብዙውን ጊዜ በተለያየ ወቅት እዳሰመሩበትም ይንገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.