2015-10-14 16:22:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ትብብር መኖር


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አት ፖንቲፊክስ በተሰየመው በትዊተር የማኅበራዊ ግኑኝነት ድረ ገጽ በኩል ባለው አድራሻቸው አማካኝነት፦ መተባበር ለመኖር እንማር፣ አለ መደጋገፍ እምነታችን ሙት ነው በማለት ያስተላለፉት መልእክት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወደ ሚከፈተው ኢዮበልዩ የምህረት ዓመት እንዲተኮር የሚያደርግ መሆኑ በኢጣሊያ የካምፖባሶ ቦጃኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጃንካርሎ ማሪያ ብረጋንትኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ለተራበው የሚበላ ለተጠማው የሚጠጣ መስጠት የእምነት ኅያውነት የሚያረጋግጥ እምነት ያለው ኃይል የሚያበስር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው  በማለት የሰጠው ትእዛዝ የሚከተል ነው። ይኽ ደግሞ ምኅረትን ተጨባጭ የሚያደርግ ተግባር ነው። ከእምነት በእምነት አማካኝነት የሚቀርበው ተጨባጭ ድጋፍና ትብብር አቢይ ትምህርተ ክርስቶስ ነው። እምነት ለማስተላለፍ የሚበጅ ልዩ ሥፍራ, እርሱ ነው። ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ቁርባን ገጽና የድኻው ገጽ በማጣመር ታስተጋባለች፣ ይኽ ደግሞ ማእድና መንበረ ታቦት የሚል ገጽታ የሚያመለክት ነው። ይኸንን ለመረዳትም ማድረ ተሬዛ ማስታወስ ይበቃል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት የምኅረት ዓመት የእምነት ኃይል መግለጫ ነው። ስለዚህ አዋጁ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ምኅረት የነገሮች ጣዕም፣ የተከፈተ በር (መሸጎሪያ የሌለው የክፍት ቤት ትእምርት፣ የልብ ተምሳሊት፣ ለዚያ ሌላው ከእርሱ የተለየውን የሚፈራ በሩን የሚዘጋ ስደተኛና ተፈናቃይ የሚያስፈራው ባጠቃላይ ችግር ያለበት ሁሉ ለሚያስፈራው ኅብረተሰብ የተከፈተ በር እንዲኖር የሚያነቃቃ የሚገፋፋ ኃይል ነው ብለዋል። በማያያዝ በግብረ ሐዋርያት የምትጠቀሰው ሊዲያ የተባለቸው ሴት የቤትዋና የኅብረሰብዋ በሮች ሓዋርያዊ ጳውሎስ ለማስተናገድ እንዲከፈት ያደረገች እንግዳ ተቀባይ የሆነቸች ሴት ያስታውሰናል።

የምኅረት ዓመት ይኸንን ዓይነት ምስክርነት እንድንኖር የሚያነቃቃ ነው። የተከፈተ በር እንዲኖረን ለማንም በሮቻችን ለሚያንኳኳ ሁሉ ለማስተናገድ የሚያበቃው የእምነት ኃይል የሚመሰክር ተጨባጩ ተግባር ለመኖር የሚያነቃቃ ቅዱስ አመት መሆኑ በማብራራት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.