2015-10-07 16:01:00

ሲኖዶስ፦ እ.ኤ.አ. የጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የሲኖዶስ የሦስተኛው ቀን ውሎ ጽማሬ


የጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ውሎ የሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ሎረንዞ ባልዲሰሪ የጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ውሎ በነጻው ውይይት አማካኝነት ያቀረበው አንዳንድ ጥያቄ መሠረት በማረግ በተለይ ደግሞ የሲኖዶሱ ጉባኤ በቡድን ተከፋፍሎ የሚይካሂደው ውይይትና በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚመረጠው የሲኖዶስ ጠቅላይ የፍጻሜ ሰነድ የሚያሰናዳው ድርገት ቅዋሜ ላይ ያነጣጠረ ባስደመጡት ንግግር ውሎውን ማስጀመራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በዚህ በሁለተኛው ቀን ውሎው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስደመጡት አጭር ንግግር የተከፈተ ሲሆን ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ የ 2014 ዓ.ም. ሲኖዶስ ቀጣይ መሆኑ አስገንዝበው፣ ይፋዊ የሲኖዶሱ ሰነድ፣ የሲኖዶሱ የፍጻሜ ሰነድ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሲኖዶስ መክፈቻና መዝጊያ ያስደመጡት ንንግር ብቻ ያጠቃለለ እንደሚሆን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር በካቶሊካዊ አንቀጸ እምነት ስለ ጋብቻ የሚገልጠው ቅውም ሃሳብ ለውጥ አልተደረግበትም፣ የአንቀጸ እምነት ትምህርት በመሆኑም ለለውጥ አይዳረገም። በመሆኑም የሲኖዶስ አበው ከሲኖዶስ ውጭ በተለይ ደግሞ ቃል ኪዳን በማፍረስ የተፋቱት ዳግም ትዳር መሥረተው የሚኖሩት ቅዱስ ቁርባን ይፈቀድላቸው ወይንም አይፈቀድላቸው የሚል ጥያቄ ላይ ያነጣጠሩ እየተሰነዘሩ ላሉት አስተያየት ጆር እንዳይሰጡ አደራ፣ ምክንያቱም እነዚህ ከሲኖዶስ ውጭ የሚሰነዘሩት አስተያየቶች የሲኖዶሱ ውሁድና ጥሙር ወንድማማችነት ለተካነው መንፈስ ድጋፍ እይሆንምና፣ በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር ሲኖዶሱ በንኡሳን ቡድኖች ተከፋፍሎ የሚያካሂደው ውይይት እጅግ አፍስፈላጊና ለሲኖዶሱ የፍጻሜ ሰነድ አስተንፍሶ መሆኑም እንዳብራሩ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ውሎው እንደ ተያዘው መርሃ ግብሩ መሠረት አንዳንድ የሲኖዶስ አበው ባቀረቡት አስተያየትና ሃሳብ ወይንም ጥያቄ አማካኝነት ቀጥሎ ውሎአል። የቀረቡት አስተያየቶች በጠቅላላ ቤተሰብ የኅብረተሰብ ኃብት ለቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት እዳሴ ምንጭና በእርሷም ዘንድ ማኅበራዊ እሴቶች ለአንድ ሰብአዊ ሥነ ምኅዳር መሠረት መሆኑና አለ ቤተሰብ ማኅበረሰብ የሚፈርስ መሆኑ ያስተጋቡ መሆናቸውም የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ከዚህ በመንደርደርም የፖለቲካው ዓለም ለቤተሰብ የሚከላከልና የቤተሰብ በአባላት ማደግ ክብር የሚሰጥ፣ የሴቶች የእናትንነትና እናት የመሆን በኑባሬ ያለው ክብርና በአባላት ቁርጥ እጅግ ከፍ ያለው ቤተሰብ የሚደግፍ እንዲሆን ጥሪ መቅረቡንም አስታውቀዋል።

ጉባኤው በወጣቶች ሕንጸት ላይ በማተኮርም፣ በተለያየው ትውልድ መካከል ግኑኝነት እንዲኖር ለማድረግ ለወጣቱ ትውልድ በሥነ እውቀት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ከእምነት ርቆ እንዳያድግ በመንፈሳዊ መስክ ጭምር እንዲያድግ የሚደግፈው ሕንጸት እንዲያገኝ ያለው አስፈላጊነት በማበከር በዚህ ዘርፍ አዛውንቱ የኅብረተሰብ ክፍል አቢይ ሚና እንዳለው በማስተጋባት በዚህ ሂደት ቤተ ክርስቲያን ያለባት አቢይ ኃላፊነት ላይ እይታ በማኖር በወጣቶችና በአዛውንት የኅብረተብ ክፍል መካከል የምስክርነትና የገጠመኝ ልውውጥ እንዲኖር ማነቃቃት እንደሚያስፈልግ ይኽም በኅብረተሰብ እየተስፋፋ ያለው የግለኝነት መንፈስ እንዲወገድ ለማድረግ መሆኑ ተብራርቷል። ቤተሰብ አገናኝን ተገናኝ እንጂ የወፍ ጎጆ ባለ መሆኑም ግብረ መስተንግዶ የሚኖርበትና የኅብረተሰብ ኅያውነት መግለጫ ነው።

ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም የምታቅፍ ነች፣ ስለዚህ የአብ ቤት በመሆንዋም የተከፈቱ በሮች ያሉዋት፣ ሌላው የተሰናከለው ችግር ሳይሆን ወንድም መሆኑ የሚስተዋልባት የሚመሰከርባት የሁሉም ቤት ነች።

የእረኛው ደስታም ያንን የተሰናከለውን ወንድም በመደገፍ ህልውናው ዳግም እንዲያስተካክልና የእዝግዚአብሔር መንገድ ለይቶ እንዲያወቅ በመደገፍ ላይ ነው። ይኽ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቆሰለው ቤተሰብ በማተኮር በብፁዓን ጳጳሳት ተመርታ የውህደት ጉዞና እርቅ የሚከናወንባት ቤት ነች። ቤተ ክርስቲያን የቆሰለው በችግር ላይ ያለው ቤተሰብ ለሚያቀርበው ጩኸት የእግዚአብሔር ተጨባጭ ፍቅር አለ ምንም ፍርድ በማዳመጥ ማቅረብ ይኖርባታል፣ ይኽ ደግሞ የእግዚአብሔር ምኅረት መግለጫ መሆኑ ውሎው እንዳሰመረበት የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

በድኽነት የተጠቃው ቤተሰብ፣ ያጋጠመው ድኽነት የሚያባባስ ምግብረ ብልሽትና ብዝበዛ በተሰኙት ግድፈቶች ዙሪያ ጉባኤው በማስተንተን ከዚህ በመቀጠልም የሥነ ጾታዊ ትምህርት፣ አክራሪው ምስልምና ቤተሰብ  ለከፋ አደጋ የሚያጋልጡ እክሎች ሁሉ እግዚአብሔር ስለ ትዳርና ስለ ሰው ልጅ ሕይወት የሚያቀርበው እውነት የሚቀናቀኑ ናዚነትና ፋሺስታዊነት እንዲሁም ኮሙኒዝማዊነት ጋር በእኩል የሚቀመጡ ተጋርጦዎች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን የክርስቲያናዊ ፍቅር ውበት የማነቃቃት ኃላፊነት አለባት፣  ለተለያዩ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ማኅበራት እና እንቅስቃሴዎች ምስጋናም ይሁን ይኽ ውበት እየተመሰከረ ነው። ከዚህ ጋር በማያያዝም እምነት በማስተላለፉ ተልእኮ ቤተሰብ ማእከል መሆኑ ውሎም በማስተጋባት ይኽ ተልእኮም ማኅበረ ክርስቲያን ለአመጽና አድልዎ አደጋ በተጋለጠበት ክልል ሁሉ የሚታይ መሆኑ ውሎው ይመሰክረዋል።

ቤተ ክርስቲያን በምሥጢረ ተክሊል የጸናችው ቤተሰብ የመከላከል ኃላፊነት አለባት፣ ለማስተማር ብቻ ሳይሆን ከቤተሰብ ለመማርና ቤተሰብ ችግሮችን ለመወጣት ከሚያከናውነው ትግልና ከሚከተለው መፍትሔ ጭምር ብዙ ትማራለች፣ ችግር አልቦ ሳይሆን ችግር የሚጋፈጥ ቤተሰብ ደስተኛ ነው። ቤተሰብን በእግዚአብሔር ዓይን መመልከት፣ ይኽም ችግሮቹ በተመለከተ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ በወቅታዊው ጨለማ በተካነው ዓለም የብርሃን ቦግታ የሚያሰራጭ መሆኑ እንዲስተዋል ነው።

በጋብቻና በእምነት ቀውስ የተጠቃው ቤተሰብ ላይ በማተኮርም ለቤተሰብ ያቀና ብቃት ያለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖሎው ያለው አስፈላጊነት በማስገንዘብ፣ ለጋብቻ የሚያሰናድ ከጋብቻ በኋላ የሚሰጥ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቤተሰብ እንደ የእግዚአብሔር እቅድ እንዲያድግ የማድረግ ብቃት ያለው መሆን አለበት። ከዚህ አንጻር የሚወጠነው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተሟላ ቅድመ ዝግጅት የሚያስፈልገው መሆኑም አያጠያይቅም። በዚህ መስክ የቃል ኪዳን ውበትና ውህበት ፍቅርና እውነት የሚኖር ቤተሰብ በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ እንዲነቃቃ መደገፍ፣ ይኽ ደግሞ እምነት ግብረ ገብ ከማኅበራዊና ከባህላዊ መድረክ የሚያገል ባህል በብቃት ለመዋጋት ደጋፊ መሆኑ ውሎው አንዳስገነዘበ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ከጦርነት ከአመጽ ከመከራ ከመሳሰሉት ችግሮች የሚያመልጥ ወይንም ለከፋ አደጋ የታጋለጠው ቤተሰብ ማስተናገድ ሰብአዊ ክብራቸውና መብታቸውም ይጠበቅ ዘንድ መቆም ድጋፍ ማቅረብ ማስተናገድ።

ጦርነት ባለበት ክልልም ይሁን በቤተሰብ ውስጥም ከቤተሰብ ውጭም በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ዓመጽና በደል የሴቶች መብትና ክብር እንዲሁም የሴቶች እኩልነት በማረጋገጥ መስክ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ ሆና ስለ ሴቶች የተሟል እድገት በማገልገል፣ የሴቶች ተሳትፎ በቤተ ክርስቲያንም በሚገባ ማነቃቃትና እግብር ላይ እንዲውል ደጋፊ ሆና መገኘትና በሰበካም ይሁን በሮማዊት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ የመሥተዳድር ቅዱሳት ማኅበራትም ጳጳሳዊ ምክር ቤቶች ውስጥ በተገባ ኃላፊነት እንዲሳተፉ ማድረግ ይኖርባታል።

በመጨረሻም ውሎው አንዳዊ ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል ትዳር ስለ ሚባለው በዓለም የሚቀርበው ባንዳንድ ክልል የተፈቀደው ጉዳይ ላይ በማተኮር፣ ይኽ ጉዳይ የእግዚአብሔር እቀድ የሚጻረር ነው። በመሆኑም በምንም ዓይነት መንገድ የተፈቀደ ሊሆን አይችልም፣ ይህ ሲባል በአንዳዊ ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች ላይ የጥላቻ ስሜት ማንጸባረቅ ወይንም መኖር ማለት ሳይሆን ባንጻሩ ስለ እነዚህ የሚሰቃዩት ወንድሞች መጸለይ እንደሚያስፈልግ ለማሳሰብ መሆኑ ከተብራራ በኋላ በዚያ በተካሄደው ጉባኤ የተገኙት ሁለት ባለ ትዳሮች የሰጡት ምስክርነት ተደምጦ የሲኖዶስ የውይይት ማካሄጃው ሰነድ አንደኛውን ክፍል በማስደገፍ የተካሄደው የሁለት ቀናት ውይይት ተጠናቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.