2015-10-05 15:03:00

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቤተሰብ ርእሰ ጉዳይ እንዲመክር የጠሩት ከመላ ዓለም የተወጣጡት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ባስጀመሩበት ዕለተ ሰንበት እኩለ ቀን እንደ ተለመደው ከውጭና ከውስጥ የተወጣጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ምእመናን የተለያዩ አቢያተ መንፈሳዊ ማኅበር አባላት ካህናት ደናግል በተገኙት ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በለገሱት አስተንትኖ፦ በጦርነት ከአመጽ የሚያመልጡት የተተዉት ለብዝበዛ የተዳረጉት ከጦርነትና ከድኽነት በመሸሽ ዛሬ መስተንግዶ ድጋፍና ትብብር ለመጠየቅ በሮቻችንን በተለይ ደግሞ በልባችን በሮች እያንኳኵ ናቸው፣ አነዚህ ለትካዜና ለተለያየ ስቃይ የተዳረጉት ሕፃናት ለሚያቀርቡት ጥያቄ ብቃት ያለው መልስ መስጠት ያስፈልጋል።

በግንብ አጥር የተከተለለ ሕብረሰብ ሳይሆን ብቃት ባለው ደንብና ሥርዓት አማካኝነት ለማስተናገድ ብቃት ያለው በፍቅር የሚያስተናግድ ቤተሰብአዊነት የተካነ ሕብረተሰብ እንሆን ዘንድ ጌታ ይርዳን ብለው፣ ሃሳባቸው በቀጥታ በይፋ ወደ ተከፈተው ሲኖዶስ በማቅናት እግዚአብሔር በኦሪት ወንድና ሴት አድርጎ በመፍጠር የገለጠው የቤተሰብ ውበትና ኃይል ዛሬ በዓለም ይኖርና ይመስከርም ዘንድ እንጸልይ፣ መንፈስ ቅዱስ ለሲኖዶስ አበው ለአስተንፍሶው መሣሪያ ሆነው እንዲገኙምም እንጸልይ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እናትነት አማላጅነትዋም በፖምፐይ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ዘሮዛርየም ጸሎተ ልመና ለማርያም በመድገም ላይ ከሚገኙት ጋር በመተባበር እንማጠን።

ቤተ ክርስቲያን ለቤተሰብና ስለ ቤተሰብ ብቃት ያለው ትጋት እንዲኖራት የሚያደርጋት መንገድ ትለይ ዘንድ እያትችንን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ የእውነትና የምህርት ትምህርት ላይ ያጽናን።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ከኦሪት ዘፍጥረት የተወሰደውን አንደኛ ምንባብ ወንድና ሴት ተሟይነታቸው ለፍቅርና ለውህደት በእግዚአብሔር የመፍጠራቸው ተግባር በእግዚአብሔር ፍቅርና ውህደት ተሳታፍያን ያደርጋቸዋል፣ ቤተሰብ በእርሱ ሥራ ተሳታፊነት ከርእሱ ጋርና እንደርሱ በማፍቅር ተግባር ላይ የጸና መሆን አለበት ብለዋል።

በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን የሚፈሰው ፍቅር ያ በሚስጢረ ተክሊል ቃል ኪዳን ለሚያስሩት የሚሰጥ ፍቅር ነው። ይኽ ፍቅር ቃል ኪዳን ባሰሩት በደስታና በስቃይ ወቅት አንድነታቸውን ውህደታቸው ያበረታል። በእነርሱ ውስጥ ያለው ፍቅር ወላጅ የመሆን ፍላጎት የሚያነቃቃ ልጅ ወልዶ አቅፎ ለመሳም ለማስተማርና ለማሳደግ የሚበቃ ፍቅር ነው ብለው፦ ሁሉም ወላጆችና አስተማሪዎች በጠቅላላ ሕብረተሰብ የዚያ የአስተናጋጅና አፍቃሪው ኢየሱስ ተናናሾችን በእቅፉ በማኖር የሚገልጠው የእናትነትና የአባትነት ርህራሄ ተግባር እንዲኖር እንጸልይ።

ቅዱስ አባታችን የለገሱት አስተንትኖ አጠቃለው እ.ኤ.አ. መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በስፐይን የሲታውያን ገዳማውያን ማኅበር አባላት የሆኑት 18 ባህታውያን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት የደም ሰማዕነት ለከፈሉት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና እንዳወጀችላቸው በማስታወስ ስለ እነርሱ ጽኑ የደም ምስክርነት ጌታን እናመስግን፣ ካሉ በኋላ በፈረንሳይና በጓተማላ የጣለው ሃይለኛው ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት የሞት አደጋ ያጋጠማቸው ጌታ በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው ተመጽነው አለ ቤትና ንብረት ለቀረው ሁሉ ለድጋፍና ትብብር እንትጋ ብለዋል።

ሁሉንም እዚያው በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ከተለያየ አካባቢ የመጡት የተለያዩ ማህበራትና ምእመናን ሁሉ ሰላምታን አቅርበው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.