2015-10-05 15:19:00

ኬንያ፦ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ቅዱስ አባታችንን በመጠበቅ


በመሥዋዕተ ቅዳሴ ቀጥሎም በጸሎተ ፍኖተ መስቀልና በቅዱስ ቁርባን ፊት የአስተንትኖ ጸሎትና ቡራኬ አማካኝነት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ በኬንያ በሚገኘው ዘሱቡኪያ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በይፋ መከፈቱ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ አባ ቻርለስ ኦዲራ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከህዳር 25 ቀን እስከ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በኬንያ

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ኣባ ኦዲራ፦ ይኽ የኬንያዊ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ዘንድሮ ለየት የሚያደረገው እ.ኤ.አ. ከህዳር 25 ቀን እስከ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት የሚታደል በመሆኑ ነው ብለው፣ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ እንዳመለከተውም ቅዱስ አባታችን በኬንያ ቀጥለውም ከህዳር 27 ቀን እስከ ህዳር 29 ቀን በኡጋንዳ፣ ከዛም ከህዳር 29 እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በማእከላዊቷ ረፓብሊክ አፍሪቃ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንዲያካሂዱ ከመንግሥታት በቀረበላቸው ጥሪ መሠረት የሚያከናውኑት ዑደት መሆኑ ሲታወቅ፣ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ለመላ አፍሪቃ ጸጋ ነው ብለዋል።

ቅዱስ ቍርባን የክርስትና ሕይወት ማእከል

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የዛሬ አንድ ዓመት በፊት የ 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ መርሃ ግብር ባወጀበት ወቅት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ዑደት ጉዳይ ምንም የታወቀ ነገር አልነበረም፣ ሆኖም በዚህ ቅዱስ ቁርባን ጉባኤ አማካኝነት በኬንያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ዙሪያ በመሆን በሁባሬ ያንን የክርስትና ማእከል የሆነው ቅዱስ በማሳረግ እንደምትጸልይ ቀደም ተብል የተገለጠ ቢሆንም ቅሉ ይኽ በመንፈስ የሚለው በግብር እንዲከናወን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መሆኑ አባ ኦዲር በሰጡት መግለጫ ገልጠዋል።

ይኽ የቅዱስ ቁርባን ብሔራዊ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ካወጁት የውፉያን ዓመት ጋር ተያይዞ የሚሄድ ነው ያሉት አባ ኦዲር አያይዘውም እ.ኤ.አ. ከጥር 25 እስከ ጥር 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በፊሊፒንስ ቸቡ ከተማ ቆላስይስ ምዕ. 1 ቍ. 27 “.. ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ የምንጠባበቀው ክብር ነው” በሚል መርህ ቃል ሊካሄድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጠሩት 51ኛው ዓለም አቀፋዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ላይ ያተኰረ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.